ከአልሸባብ ጋር በተያያዘ መልኩ ሽብር ተፈጠረ እያለ መንግስት የራሱን ህዝብ በገሃድ በመግደል አሸባሪዎች ናቸው በማለት የአፈናውን ሁኔታ ቀጥሎበታል ።ከዚህ በፊት በትግራይ ሆቴል እና እንዲሁም በመገናኛ አካባቢ በታክሲዎች ላይ በተፈጠረው ጥቃት መንግስት የኦነግ አባላቶች እና እንዲሁም የአልሸባብ አሸባሪዎች ሲል የገለጸበት ሽብር በወቅቱ የህዝቡ ድንጋጤ ከተፈጠረው እውነታ ጋር ተያይዞ አመኔታን ፍጥሮለት የነበረ ቢሆንም ከቆይታ በኋላ ያዝኳቸው በማለት በመገናኛ ብዙሃን አቅርቦ ሲጠይቃቸው የነበሩትን ወንጀለኛ ተብዬዎች ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሸኛቸው
እና የጥቃቱ ተሳታፊ የነበሩትን የወያኔ ደጋፊዎችን ዱካቸው እንዲጠፋ ማድረጉን እና እውነታው እንዲደበቅ መሞከሩ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው ሆኖም ግን ወያኔ የህዝቡን አመለካከት እና የወቅቱን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለመለወጥ ሲል በአሸባሪዎች በማሳበብ ብዙ ሽብሮችን እየፈጠረ የፖለቲካውን ሂደት እንዲለወጥ በማድረግ ይሞክራል ። ሆኖም ግን በተደጋጋሚ በመደረጉ በህዝቡ አመኔታን ከማጣቱ የተነሳ ተቀባይነትን ሊያገኝ አልቻለም ።
እና የጥቃቱ ተሳታፊ የነበሩትን የወያኔ ደጋፊዎችን ዱካቸው እንዲጠፋ ማድረጉን እና እውነታው እንዲደበቅ መሞከሩ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው ሆኖም ግን ወያኔ የህዝቡን አመለካከት እና የወቅቱን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለመለወጥ ሲል በአሸባሪዎች በማሳበብ ብዙ ሽብሮችን እየፈጠረ የፖለቲካውን ሂደት እንዲለወጥ በማድረግ ይሞክራል ። ሆኖም ግን በተደጋጋሚ በመደረጉ በህዝቡ አመኔታን ከማጣቱ የተነሳ ተቀባይነትን ሊያገኝ አልቻለም ።
በአለም አቀፍ አሸባሪ ቡድን እና በኤርትራ መንግስት እገዛ የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖች በሃገራችን ውስጥ የተለያዩ ስፍራዎች የሽብር ጥቃት ለመፈፀም እየተዘጋጁ መሆናቸውን የሚያሳይ አስተማማኝ መረጃ ያለው መሆኑን የብሄራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎትና የፌደራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል አስታወቀ” ሲል መግለጫ ማውጣቱን ተከትሎ አስተያየት ሰጪዎች “መንግስት አሁንም ድራማ ለመሥራት ሰው ሊገድል ነው ወይ?” በሚል አስተያየት ሲሰጡ ነበር – በተለያዩ መድረኮች። ዛሬ የተፈራው ደረሰና የመንግስት ሚድያዎች “በሸርቆሌ ከተማ አቅራቢያ የተቀበረ ፈንጂ ፈንድቶ በደረሰዉ አደጋ ሶስት ሰዎች ሲሞቱ በዘጠኝ ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ” ሲሉ ዘግበዋል። ይህን የታዘቡ ወገኖች ከዚህ በፊት የሆኑትን በማስታወስ “መንግስት ሆን ብሎ ያደረገው ነው” ሲሉ ይተቻሉ። የመንግስት መገናኛ ብዙሃን የዘገቡት የሚከተለውን ዜና ያቀረቡ ሲሆን በደህንነት እና የሃገራዊ ሚስጥራዊ ድህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ እንዲህ አይነት መረጃ ቀድሞ የደረሳቸው ከሆነ በየትኛውም አገር ቀድሞ ወንጀለኛውን ድርጊቱ ከመፈጸሙ በፊት አንፍንፎ የመያዝ ግዴታ እንዳለባቸው የዘነጉት እና ስራቸው ምን እንደሆነ ያላወቁት የደህንነት መስሪያቤት ሰራተኞች ህዝብን ለማሸበር የሽብር መንፈስ በሃገሪቱ ላይ ለመዝራት ግንባር ቀደሙን ቦታ እንደያዙት ለማወቅ ተችሎአል ።
በሸርቆሌ ከተማ አቅራቢያ የተቀበረ ፈንጂ ፈንድቶ በደረሰዉ አደጋ ሶስት ሰዎች ሲሞቱ በዘጠኝ ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ
በሸርቆሌ ከተማ አቅራቢያ የተቀበረ ፈንጂ ፈንድቶ በደረሰዉ አደጋ ሶስት ሰዎች ሲሞቱ በዘጠኝ ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ
አሶሳ ጥቅምት 27/2006 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሸርቆሌ ከተማ አቅራቢያ በመንገድ ላይ የተቀበረ ፈንጂ ፈንድቶ ባደረሰዉ አደጋ ሶስት ሰዎች ሲሞቱ በዘጠኝ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ ። በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት የስራ ሂደት ባለቤት ኮማንደር ታከለ ማሞ ዛሬ እንዳስታወቁት አደጋው የደረሰው ከሸርቆሌ ወደ አሶሳ አቅጣጫ 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒ ባስ በመንገድ ላይ የተቀበረ ፈንጂ ላይ በመዉጣቱ ነዉ ። በዋናው የመኪና መንገድ በተለምዶው ሰኞ ገበያ በጉንሳ ጎጥ በተባለው አካባቢ ትናንት ከቀኑ አምስት ሰዓት ላይ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 ቤጉ 00203 የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ለጊዜዉ ማንነታቸዉ ባልታወቀ በተቀበረ ፈንጂ ላይ በመዉጣቱ በሰዉ ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳትደርሷል ። በሚኒባሷ ውስጥ ከተሳፈሩት 12 መንገደኞች መካከል የሶስቱ ህይወት ወዲያዉኑ ሲያልፍ በአምስቱ ላይ ከባድ ፣በአራቱ ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት መድረሱንና ተጎጂዎቹ በአሶሳ ሆስፒታልና ሸርቆሌ ጤና ጣቢያ ህክምና እየተደረገላቸዉ መሆኑን ኮማንደር ታከለ ገልጠዋል ። በአደጋው ህይወታቸው ካጡት ሰዎች መካከል እድሜው ከአስር ዓመት በታች የሆነ አንድ ህፃንና አንዲት ሴት እንደሚገኙበት ኮማንደሩ ሊኢዜአ አስረድተዋል ። አደጋውን ያደረሰው ማንነት እስካሁን በውል ያልታወቀ ቢሆንም የጸረ ሰላም ቡድኖች ድርገት ሳይሆን እንደማይቀር አንዳንድ ጠቋሚ መረጃዎች እንደሚያመላክቱ ኮማንደሩ ተናግረዋል ። በአሁኑ ጊዜ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎችና ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ወንጀለኞችን ለመያዝ የተጠናከረ ክትትል እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡ ከአደጋው ተጎጅዎች መካከል ስሙን መግለጽ ያልፈለገው አንድ ግለሰብ በአደጋው ወቅት ከመንገዱ በቅርብ ርቀት የሚኒባሷን እንቅስቃሴ የሚከታተሉ ከ10 የሚበልጡ ሰዎች መመልከቱን ተናግሯል ፡፡ ከግለሰቦቹ መካከል የጦር መሳሪያ የታጠቁ እንደነበሩ ጠቅሶ አደጋው እንደደረሰ ወዲያውኑ ከአካባቢው መሰወራቸዉን አስተያየት ሰጪው ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አስረድቷል፡፡ ከአሶሳ በ90ኪሎ ሜትር ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ደግሞ በ160 ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ላይ በምትገኘው ሸርቆሌ ከተማ በአሁኑ ወቅት የፀጥታው ሁኔታ እንደቀድሞው የተረጋጋና ህብረተሰቡን ስራዉን በሰላም እያከናወነ መሆኑን ኢዜአ በዘገባዉ አመልክቷል ።
No comments:
Post a Comment