Monday, March 25, 2013

ሰብኣዊነት ይቅደም!!!



  አሁንም ደግመን ደጋግመን እንበል ሰብኣዊነት ይቅደም!
ትግርኛ ተናጋሪ በመሆናችን ብቻ ወሃትን አቀንቃኝ መሆን የለብንም፣ እንደ ጥሩንባ ነፊ ፕሮፓጋንዳ ነፊ መሆን የለብንም! ትግርኛ ተናጋሪ መሪዎች ስላሉበት የህውሃት ደጋፊ መሆን የለብንም! ከነችግራቸው፣ከነበደላቸው፣ከነሐጢያታቸው መደገፍ ያለብ ይመስለኝም።ቆም ብለን እናስብ እንጂ እንደ ሰው! ያለበለዚያ ነገ ደግሞ ዋጋ እንደሚያስከፍል ማወቅ ተገቢ ነው አንድ ሰው ዘመድህ ወይም ያ ሰው ድርጅቱ መሪ፣ አባል፣ ደጋፊ ያንተ ሰው ከሆነ በሰው ልጅ ላይ መጥፎ ነገር እንዳይፈፅም መምከር ሲገባ በስጋ ወይም በዘር ስለተቆራኘን ብሎ መደገፍ፣ ማበረታታት ነገ ከወንጀል አድራጊው የተለየ ስራ አለመስራታችን ማወቅ ተገቢ ነውበደል ፈፃሚው ድርጊቱን ካላስተካከለ ተግባሩን በመቃወም ማሳየት

 ባንተ ላይ እንዲፈፀም የማትፈልገውን ነገር በሌሎች እንዲከወን ከቶ ትፍቀድ። የሥጋ እናቴና አባ ለሰው ልጅ ጥሩ እንዲሆን እመኛለው፣እሻለሁ። ካልሆነ ግን እናቴ ወይም አባቴ ስለሆነ ብቻ መጥፎ ተግባራቸው ልደግፍም።እኔ የሚገባኝ በሰው አእምሮ ሳስበው እውነቱ ሳይናገር፣ሰው ሲበደል ስታይ አድራጊውን ማውገዝ ነው
የሰው ልጅ ማንም ይሁን የትም ይኑር ሰብኣዊ ፍጡር መሆኑ ብቻ የኛ ሞራላዊና ሰብኣዊ ድጋፍ ለማግኘት በቂ ምክንያት ነው።
የሰው፡ ልጅ፡ ሁሉ፡ ሲወለድ፡ ነጻና፡ በክብርና፡ በመብትም፡ እኩልነት፡ ያለው፡ ነው። የተፈጥሮ፡ ማስተዋልና፡ ሕሊና፡ ስላለው፡ አንዱ፡ ሌላውን፡ በወንድማማችነት፡ መንፈስ፡ መመልከት፡ ይገባዋል። 
ከሰብኣዊ


No comments:

Post a Comment