ዝም ማለታችን የግፍ ዋጋ እያስከፈለን ነው!!
በጋንቤላ የዘር ማጥፋቱና ጭፍጨፋው ቀጥሏል አረመናዊው ስርዓት እንዳለፈው ሁላ በወያኔ ተደግሟል
እንዲሁም በደቡብ ክልል ቤንሻጉል ያሉ አማሮች እንዲወጡ በመንግስት ትህዛዝ ተሰጧል ከጋንቤላ አማራን ማፅዳት በሚል መርህ።ህዝቡ
ዝም ማለቱ አነጋጋሪ ነው።ህዝቡ ዝም ማለቱም ዋጋ እያስከፈለው ነው!ኢትዮጵያ ውስጥ እዚም እዛም፣ከመሀል እስከ ጥግ የመልካም አስተዳደር
እጦት መባሱ ለይቶለታል።
ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብኣዊ ረገጣ፣ሙስናው፣ፍትህ ማጣት፣ከዳር እስከ ዳር አላፈናፍንም እያለው እያማረረው ነው። ጭቆና ብሷል,,,,,
ጭቆና አመጽን ይወልዳል። ያለ አመጽ፣ ያለ እንቢትኝነት፣ ያለ አሻፈረኝ ባይነት ጭቆና በራሱ ፈቃድ መንገድ ለቆ አያውቅም። ሰው በአገሩ ባይተዋር ሲሆን ለእስር፣ ለችግር፣ ለሰቆቃ፣ ለስደት፣ ለሞት፣ ለውርደት… ሲዳረግ ኢትዮጵያዊ ዜግነቱ ተክዶ ማንነቱ ተፍቆ በአገሩ በሰላም መኖር ካልቻለ ትእግስቱ እንደፍርሃት ይቆጠርበታል። ኢትዮጵያን የሚያህል ታላቅ ምድር ነጻነቷን ጠብቆ አገር አድርጎ ለትውልድ ለማውረስ የጥንት አባቶቻችን የደምና ያጥንት ዋጋ ከፍለዋል። እነርሱ በእግር እና በፈረስ ተጉዘው ችግርና መከራ ቸነፈርና ሞት አሸንፈው ከእነክብሯ ያስረከቡንን አገር ለውስጥ ወራሪዎችና የታሪክ ጠላቶች፣ ከጣሊያን ሰራዊት በላይ ለከፉብን ፋሽቶች አስረክበን ማንቀላፋት እንዴት ይቻለናል?
አመጻና ስር ነቀል አብዮት ብቸኛው መፍሄ መሆኑ አያጠያይቅም። ስለዚህም ነው በተደራጀና በተቀናጀ ሁኔታ መታገል የግዜው አንገብጋቢ ጥያቄ የሆነው። እንዴት? ሁሉም በያለበት ሊያስብበትና ሊወያይበት የሚገባ መሰረታዊ ጥያቄ ነው። በአግባቡ ካሰብንበት ብልሃት እና መፍሄ አይጠፋም።ለኢትዮጵያ ሕልውና መኖር!!
አመጻና ስር ነቀል አብዮት ብቸኛው መፍሄ መሆኑ አያጠያይቅም። ስለዚህም ነው በተደራጀና በተቀናጀ ሁኔታ መታገል የግዜው አንገብጋቢ ጥያቄ የሆነው። እንዴት? ሁሉም በያለበት ሊያስብበትና ሊወያይበት የሚገባ መሰረታዊ ጥያቄ ነው። በአግባቡ ካሰብንበት ብልሃት እና መፍሄ አይጠፋም።ለኢትዮጵያ ሕልውና መኖር!!
ያለበለዚያ በግፍ መታሰር፣ መደብደብ፣መገደል፣በመሰደድ ዋጋ ያስከፍለናል!! ዛሬ የሰሜን ሰው
አልተነካውም ብሎ ለደቡብ ሰው ዝም ካለ እንዲሁም የምስራቅ ሰው አልተነካውም ብሎ ለምዕራብ ሰው ዝም ማለት ነግ በኔ ነውና ዝም
ማለታችን ነግ ዋጋ ያስከፍላል !
ከጎሳ ይልቅ ለሰብአዊነት ቅድሚያ
የምንሰጥበት ግዜ አሁን ነው።
ምክንያቱም ሁላችንም ነፃ ካልወጣን
ማንም ነፃ ሊሆን አይችልም!!
ከጎሳ ይልቅ ለሰብአዊነት ቅድሚያ
የምንሰጥበት ግዜ አሁን ነው።
ምክንያቱም ሁላችንም ነፃ ካልወጣን
ማንም ነፃ ሊሆን አይችልም!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ከዘካሪያስ አሳዬ
No comments:
Post a Comment