Sunday, March 31, 2013

የኢህአዴግ ጉባኤና የተቃዋሚዎች አስተያየት “ አቶ ‹‹X›› ወጥቶ አቶ ‹‹Y›› ቢወርድ ለኢትዮጵያ ፋይዳ ያለው ነገር ነው ብዬ አላስብም" አቶ አሮን ሰይፉ አንድ ክፍል ውስጥ የሆኑ ሰዎችን አስገብተህና በር ዘግተህ ከሚደረግ ጉባኤ ምንም አይጠበቅም “ “አቶ ተመስገን ዘውዴ


የኢህአዴግ ጉባኤና የተቃዋሚዎች አስተያየት “ አቶ ‹‹X›› ወጥቶ አቶ ‹‹Y›› ቢወርድ ለኢትዮጵያ ፋይዳ ያለው ነገር ነው ብዬ አላስብም" አቶ አሮን ሰይፉ አንድ ክፍል ውስጥ የሆኑ ሰዎችን አስገብተህና በር ዘግተህ ከሚደረግ ጉባኤ ምንም አይጠበቅም “ “አቶ ተመስገን ዘውዴሰሞነኛው የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ዘጠነኛ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባኤ የሀገሪቱ አበይት የፖለቲካ ሁነትነበር፡፡ ከውጪ ሀገራት የመጡ የ13 ፓርቲ ልዑካናት፣ ከልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍል የተወከሉና የፓርቲውአባላት በጥቅሉ 2000 ዕድምተኞች በተገኙበት የተካሄደው የአራት ቀኑ ጉባኤ ሀገሪቱን የሚመለከቱ በርካታውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡ አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ሊቀመንበር፣ አቶ ደመቀ መኮንን ደግሞ ምክትል ሆነውእንዲሰሩ ያስወሰነው ጉባኤ ባለ አስራ አንድ አንቀፅ የአቋም መግለጫ በማፅደቅ ብቻ የተደመደመ አልነበረም፡፡ጉባኤው ድርጅቱ የቀድሞ መሪውን እጅግ የዘከረበትና የእሳቸውን ስራ የተመለከተ የጉባኤ ሰነድ ያቀረበበትምጭምር ነበር፡፡ከዚህ የኢህአዴግ ጉባኤ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ የግንባሩ አባል ድርጅቶች ህወሀት፣ ብአዴን፣ ደኢህዴግእና ኦህዴድ የየራሳቸውን ድርጅታዊ ጉባኤ በየክልሎቻቸው ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ ድርጅቶቹ በዚህጉባኤዎቻቸው ላይም በርካታ የአመራር ሹም ሽሮች ማድረጋቸውና መነጋገሪያ ሆኖ መሰንበቱም አይዘነጋም፡፡እኒህን የጉባኤ ሳምንታት አስታከንም በጉባኤያቱ ላይ የተከሰቱ ነገሮችን በተመለከተ በተቃውሞ ጎራ ያሉየፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን አስተያየት ለማሰባሰብ ሞክረናል፡፡ ጉባኤዎቹን ተከትሎ በሀገሪቱ ሊመጣ የሚችልፖለቲካዊ ለውጥ ይኖር እንደሁ ሀሳባቸውን እንዲሰጡን ላቀረብንላቸው ጥያቄ ተቃዋሚዎቹ የተቀራረበምየተለያየም አይነት ምላሾችን ነበር የሰጡን፡፡ የተለያዩ ፓርቲዎችን የሚወክሉት እነኚህ የተቃዋሚ ሰዎችበኢህአዴግ ውስጥ ተካሄደ ሲባል የሰነበተውን የስልጣን መተካካት በተመለከተ አንዳንዶቹ ከጡረታ መውጣትጋር ሲያያይዙት ሌሎቹ የ‹‹ሪሳይክል›› ስራ ነው ብለው ገልፀውታል፡፡ ከዚህ የተለየ ሀሳብ ያላቸው ደግሞመተካካቱ የድርጅቱ የራሱ የውስጥ ጉዳይ እንደሆነ ሲጠቅሱ፣ የውሸት ለውጥ ነው፣ ከበስተኋላው ሌላ ነገርያለበት ይመስላል... በማለት በጥርጣሬ የተመለከቱትና በተለያየ መንገድ ያብጠለጠሉትም አልጠፉም፡፡ካሰባሰብነው አስተያየት መገንዘብ እንደሚቻለው ከሆነ የተቃዋሚ አመራሮቹ የኢህአዴግ መተካካትን በተመለከተያላቸው ሀሳብ እንዲህ የተለያየ ይሁን እንጂ በአንድ ሀሳብ ላይ ግን የሚስማሙ ነው የሚመስለው፡፡ ከጉባኤውበኋላ ምን ይጠበቃል? ወይም የተደረገውን መተካካት ተከትሎ በዚህች ሀገር ላይ ፖለቲካዊ ለውጥ ይታይይሆን? የሚለውን ጉዳይ በተመለከተ የሁሉም ግምት ‹‹በፍፁም አይመጣም›› የሚል አይነት አንድምታ ያለውነበር መልሳቸው፡፡ ለምን? ይህንን ያሉበትን ምክንያት በተመለከተና ስለ አጠቃላዩ የኢህአዴግ ጉባኤዎችበተቃዋሚ ፓርቲ ሰዎች በኩል የተሰጡ ምጥን አስተያየቶችን ይዘናል፡፡የምንጀምረውም በውጪ ሀገር ከርመው በቅርቡ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት የኢዴፓው አቶ ልደቱ አያሌውእና የቀድሞ የህወሀት ታጋይና ያሁኑ የአረና ትግራይ ስራ አስፈፃሚ አቶ አስገደ ገ/ሥላሴ ለvoa ከሰጧቸውአስተያየት በመቀንጨብ ይሆናል፡፡አቶ ልደቱ አያሌውመተካካቱ የተፈለገው ይህን ገዢና አውራ ፓርቲ ለመጪዎቹ 40 እና 30 ዓመታት አገዛዙን ይዞ እንዲቀጥልለማድረግ ነው፡፡ ከሀገራዊ ፖለቲካ አንፃር የዴሞክራሲ ስርዓቱ እንዲያብብ የህብረተሰቡ አመለካከት በተለያዩፓርቲዎች ተወክሎ በምርጫ መስተናገድ እንዲችል ኢህአዴግ መስራት ከሚገባው ነገር አንድ በመቶውንእንኳ እየሰራ ነው ብዬ አላምንም፡፡መተካካት በአንድ ፓርቲ ውስጥ የሚደረግ የሰዎች ለውጥ ብቻ ሳይሆን በመንግስት ስልጣን ላይ ፓርቲዎችየሚያደርጉት መተካካትም ጭምር ነው፡፡ ኢህአዴግ የታገልኩለት ትግል መልካም ፍሬ አፍርቷል ወይ ጥሩቦታ ደርሷ ብሎ ማመን ካለበት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ እሱ በሌላ ፖለቲካ ፓርቲ ሲተካ ሊታይ ይገባል፡፡ፓርቲው እኔ ከሌለሁ ሀገሪቱ አትኖርም ከሚል አስተሳሰብ ራሱን አውጥቶ ማየት መቻል አለበት፡፡ ለምሳሌግለሰቦች (እንደ መለስ ያሉ) ሳይኖሩ ፓርቲው መቀጠል እንደቻለው ሁሉ ፓርቲው ተሸንፎ ከስልጣን ወርዶኢትዮጵያ እንደ ሀገር መቀጠል መቻሏ ሲረጋገጥ ነው የኢህአዴግ ታሪክ ጥሩ ታሪክ ነው ብዬ የማምነው፡፡ይህን ማድረግ ካልቻለ የመተካካቱ ጉዳይ በጣም ቁንፅል ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡ገዢው ፓርቲ ነፃ ምርጫ ለማካሄድ፣ ፓርቲ በፓርቲ እንዲተካ ለማድረግና ምቹ ሜዳ ለመፍጠር ፍቃደኛአይደለም፡፡ በወረቀት ላይ ባያሰፍረውም ኢህአዴግ በተግባር ከሚያራምደው ፖለቲካ አንፃር በሀገሪቱ ውስጥየብዙሃን ፓርቲ ኖረው የህዝቡ አመለካከቶች በተለያዩ ፓርቲዎች ተወክሎ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ተካሂዶአንዱን ፓርቲ ሌላው የሚተካበት ሁኔታ እንዲፈጠር ፍላጎቱ አለው ብዬ አላምንም፡፡ ይሄን በተደጋጋ በተግባርያየነው ነው፡፡ ሂደቱም ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ ወደ 22 እና 23 ዓመት በሆነው የአገዛዝ ዘመኑኢትዮጵያ ውስጥ አንድም ቀበሌ በሌላ ፓርቲ ተመርቶ የሚያውቅበት ሁኔታ የለም፡፡ አሁን ከ547 የፓርላማመቀመጫ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ የያዘው አንድ ብቻ ነው፡፡ ይህ የሚያሳይህ ስርዓቱ እንደስርአት እምነትየለውም፡፡ እምነት ቢኖረው ኖሮ በኢኮኖሚው ረገድ እያሳየ ያለው ውጤት በዴሞክራሲ ሂደቱም ላይ ይታይነበር፡፡አቶ አስገደ ገ/ሥላሴረጅም ዓመታት በስልጣን የመቆየት ፍላጎት በኢህአዴግ ውስጥ የቆየ አላማ ነው፡፡ አላማው ካወጣቸውፖሊሲዎችና ከሰበሰባቸው ድርጅቶች የመነጨ ነው፡፡ ከሱ ውጪ ሌላ ፓርቲ በዚህች ሀገር መኖር የለበትምይላል፡፡ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የሚባሉትን እናውቃቸዋለን፡፡ የህወሀት ስሪት ናቸው፡፡ ህወሀት ይዞትከመጣውና ከሚያራምደው የተለየ አመለካከት ኖሯቸው አያውቅም፡፡መተካካቱ ከልብ ያልሆነና የፓርቲ ታማኝነትን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ ትግራይ ውስጥ ብዙ መስራት የሚችሉሰዎች አሉ፡፡ በህዝብ የሚታወቁና ለሀገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ብዙ ሊሰሩ የሚችሉሰዎች በየመስሪያ ቤቱ አሉ፡፡ የመለስን ሌጋሲ እንከተላለን በሚል ፈሊጥ የተደረገ መተካካት እንጂ ለሀገሪቱይጠቅማል ተብሎ፣ የህዝብን ችግር እንዲፈታ ታስቦ የተተካ አመራር የለም፡፡ አማራ ክልል ላይ ከሁለትዓመት በፊት ከበአዴን ወተው የነበሩ አባላቱን ድርጅቱ ደግሞ ሾሟል፡፡ ምን ማለት ነው ይሄ? ያ ህዝብእነዚህን ሰዎች ሊተካ የሚችል ሰዎችና አመራሮች የሉትም ማለት ነው?የህወሀት መተካካት ጤናማ አይደለም፡፡ ከህወሀት ብዙ ሰዎች ተገልለዋል፡፡ አርከበ እቁባይ፣ ስዩም ሌሎችም፡፡ ይህ ግን በፍላጎታቸው የሆነ አይመስለኝም፡፡ በውስጡ አንድ ነገር ያለበት ነው፡፡ በተጨባጭ ከጠቅላይሚኒስትር መለስ ሞት በኋላ በፓርቲው ውስጥ ብዙ መፈጋፈግ ነበረ፡፡ ያ መፈጋፈግ የወለደው መገለል ይሁንአይሁን ወደ ፊት የሚታይ ነገር ነው፡፡ በኢትዮጵያ በስነ ምግባራቸውም ሆነ አመራር ችሎታቸው ብቁ የሆኑሰዎች ቦታ እየተሰጣቸው አይደለም፡፡የዝግጅት ክፍላችን በስልክም በአካልም የሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን አስተያየት ያሰባሰበ ሲሆንየተባበሩንን ሁሉ በቅድሚያ እያመሰገነ እንዲህ ያስነብባችኋል፡፡ፖለቲካዶ/ር መራራ ጉዲናእኛ ለውጥ እያየን አይደለም፡፡ መተካካት የሚሉት የራሳቸው የውስጥጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህ እሱ የነሱ ጭንቀት ነው፡፡ እንጠብቅ የነበረውየፖሊሲና የአመራር ለውጥ ነበር፡፡ ነገር ግን እሱ ሲሆን እያየንአይደለም፡፡ ማን በማን ተተካ? የሚለው ጉዳይ እኛን አይመለከተንም፡፡የተያያዙት ‹‹ሪሳይክል›› የማድረግ ስራ ነው፡፡ እንደውም እኮ ‹‹ሌጋሲንእናስቀጥላለን›› በሚል አባዜ ወደኋላ እየተመለሱ በውርስ ሊገዙንእየሞከሩ ነው፡፡ ይህ ነገር በአፄ ምኒልክ አገዛዝ ወቅት ንጉሱ ሞተውለአምስትና ስድስት ዓመታት ሲገዙ ነበር ከሚባለው የታሪክ ሁነት ጋርየሚለያይ አይደለም፡፡ እናም በአጠቃላይ የሚባለው ለውጥ የለም፡፡ሰዎች በሰዎች የተተኩ በመሆኑ አንዱ ሄዶ ሌላው ሲመጣ የሚጠበቅየፖለቲካ ለውጥ ሊኖር አይችልም?እንግዲህ ይሄ የተተኩት ሰዎች የሚያመጡት ለውጥ ምን እንደሆነጊዜውን ጠብቆ ማየት የሚሻል ይሆናል፡፡ ነገር ግን እንደምናየው ሰዎቹወደኋላ ሲመለሱ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ያለፈበት የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለምንሳይቀር ማኦኢዝም፣ ሌኒንዝም እያሉ ማስተማርና የማጥመቅ ስራ እኮነው የተያያዙት፡፡ ወደኋላ እየተመለሱ ነው፡፡ ስለዚህ ለውጥ የሚመጣመስሎ አይታየኝም እኔ፡፡አቶ ተመስገን ዘውዴሰሞኑን የተደረገውን የኢህአዴግ ጉባኤን የስልጣን መተካካት ሂደትበተመለከተ የሚሰጡት አስተያየት ካለ?አንድ ክፍል ውስጥ የሆኑ ሰዎችን አስገብተህና በር ዘግተህ ከሚደረግጉባኤ ምንም አይጠበቅም፡፡ ይህ ነገር ልክ እንደኩሬ ውሃ ሆኖ ነውየሚታየኝ፡፡ የኩሬ ውሃ ደግሞ አዲስ ውሃ የማይገባበትና በሌላየማይለወጥ ከሆነ ይሸታል፡፡ የተደረገው ጉባኤም ሆነ መተካካት ለውጥየማያመጣ ነገር ነው፡፡በዘውዳዊው ስርዓት ጊዜ ለውጥ የጠየቁ ተማሪዎችን ተከትሎ ንጉሱስልጣን አተካክተው ነበር፡፡ በጊዜው ግን ተማሪዎቹ ‹‹ጉልቻ ቢቀያየርወጥ አያጣፍጥም›› ሲሉ ነበር ትግላቸውን የቀጠሉት፡፡ ይህኛውምከዛ የተለየ ሆኖ አይታየኝም፡፡ ለዚህ አይነቱ ትርዒት ደግሞ ማንምየሚዘናጋ ሰው የለም፡፡የተደረገው መተካካት የተወሰኑ ሰዎችን ‹‹ሪሳይክል›› የማድረግ አዝማሚያነው የታየበት፡፡ የተተኩት ሰዎች እነማን ናቸው? ተተኪዎቹስ?የሚለው ጥያቄ የሚታወቅ ነው፡፡ እነኚህ ሰዎች የነበራቸው የፖለቲካብስለትም ሆነ አቅም ይታወቃል፡፡ እናም ከዚህ ቀደም ያልነበራቸውንዴሞክራሲያዊነትም ሆነ የአመራር ችሎታ ከየት ያመጡታል?ስለመተካካት የምናወራ ከሆነ ያልኩትን ዝግ በር መክፈት ያስፈልጋል፡፡ ሰዎች አዲስ አይነት የፖለቲካ አስተሳሰብ ይዘው እንዲመጡ ነፃማድረግም ይጠይቃል፡፡ ሀሳብ ተንሸራሽሮ ነፃ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊበሆነ ምርጫ መተካካቱ ሊወሰን ይገባል፡፡ ከዚህ ውጪ ግን ሰዎችን‹‹ሪሳይክል›› በማድረግ የሚመጣ ለውጥ አይኖርም፡፡የተተኩት በአመራር ደረጃ ያሉ የፖለቲካ ሰዎች እንደመሆናቸው መጠንበሀገሪቱ የፖለቲካ ለውጥ ይመጣል ብለው ይገምታሉ?በፍፁም! ያለው መንግስት እኮ ለመጪዎቹ 40 እና 50 ዓመታት እገዛለሁእያለ በየቀበሌው ሳይቀር የሚፎክር መንግስት ነው፡፡ አገዛዙ ለፖለቲካዊለውጦች ምንም ዝግጁነት የለውም፡፡ ለዴሞክራሲ በሩን ዝግ እንዳደረገመቀጠል ነው የሚፈልገው፡፡ እናም በዚህ ፓርቲ ውስጥ የሚደረግየሰዎች መቀያየር ትርጉም ያለው የፖለቲካ ለውጥ ያመጣል ተብሎአይታሰብም፡፡ ከዚህ ይልቅ ተተኪው ያለፈውን እየደገመ መቀጠል እንጂአዲስ ነገር አይመጣም፡፡ ስለዚህ በኛ በኩል የፖለቲካ ለውጥ ይመጣልብለን አናስብም፡፡አቶ ሙሼ ሰሙበሰሞኑ የኢህአዴግ ድርጅቶች ጉባኤና ባደረጉት የስልጣን መተካካትሂደት ላይ ያለዎት አስተያየት ምንድን ነው?መተካካት ምንድነው? በቅድሚያ በዚህ ነገር ላይ መግባባት ይኖርብናል፡፡ አንድ ተተኪ መስራት ሲያቅተውና ዕድሜውን ሲጨርስ ከሆነ በሌላየሚቀየረው ይህ ዴሞክራሲያዊ ሊሆን አይችልም፡፡ ከዛ ይልቅ ጡረታየማስወጣት ሂደት ነው ነው ሊባል የሚችለው፡፡መተካካት ዴሞክራሲያዊ ሂደት ይኑረው ከተባለ አንድ መስራት የሚችልሰው ከሌላው አቅም ካለው ጋር ተፎካክሮና የተሻለ ሆኖ ሲገኝ ሊሆንይገባል ኃላፊነት የሚሰጠው፡፡ ለምሳሌ ህወሀት ውስጥ ተደረገ የተባለውንመተካካት ካየን ወሳኝ የሆነው የድርጅቱ የስራ አስፈፃሚ አካል አይደለምየተተካው፡፡ ተተክተው በክብር ተሸኙ ከተባሉት ውስጥ እኮ የድርጅቱየስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የነበሩት ጥቂቶች ናቸው፡፡ ስለሆነም መተካካትወሳኝ የሆነው አካል በሌላ የተደረገ ለውጥ መሆን ይኖርበታል፡፡እዚህ ጋር መተካካት ከመስራት አቅም ጋር የተያያዘ መሆን አለበትዴሞክራሲያዊ እንዲሰኝ?አዎን በዴሞክራሲያዊ መተካካት የመስራት አቅም ተወዳድሮ አንዱከሌላው ብልጫ ሲወስድ የሚደረግ መሆን ይኖርበታል፡፡ ሌላው ወሳኝነገር ደግሞ ማን ነው በማንኛው የተተካው? የሚለው ጥያቄም መመለስይኖርበታል፡፡ለምሳሌ የኔ ድርጅት ኢዴፓ ከአንድም ሁለት ጊዜ ነው ይህን ዴሞክራሲየዊየመተካካት ሂደት ያደረገው፡፡ ድርጅታችን ወሳኙን የድርጅት ሃላፊነትስልጣን ለውጥ ያደረገው በዚህ መንገድ ነው፡፡ ከኮረኔል ሳህሌ እስከ አቶልደቱና እኔ እስካለሁበት ድረስ የድርጅቱ አመራር ለውጥ ሲደረግናያን የመሰለ ታላቅ ችሎታ የነበራቸው ሰዎች ሲለወጡ የተከተልነውይህን መንገድ ነው፡፡ ወደ ፊትም የምንከተለው ይህንኑ ነው፡፡ አሁንይህ በኢህአዴግ ድርጅቶች ውስጥ እያየን ያለነው መተካካት ግን ለኔዴሞክራሲያዊ መተካካት ሳይሆን አንድ ፍፁም በዕድሜ የገፋና መስራትየማይችልበት ደረጃ ላይ የደረሰን ሰው ወይም በድርጅት ውስጥ ተፅዕኖፈጣሪ ያልሆነ ቦታን ይዞ የነበረን ሰው በሌላ እንደመለወጥ አድርጌ ነውየምመለከተው፡፡በአንዳንድ የኢህአዴግ ድርጅቶች ለምሳሌ በብአዴን የቀድሞ ስራአስፈፃሚና በኋላም ከድርጅት ተሰናብተው የነበሩ አባላትን ደግሞ ወደስራ አስፈፃሚነት የመመለስ ሂደት ተመልክተናል፡፡ ይህን እርሶ እንዴትያዩታል?ይህ ነገር እንዲህ አድራጊው ድርጅት ያለበትን የሰው ኃይል ውስንነትናእንደገናም ግለሰቡ በድርጅቱ ውስጥ ያለውን ‹‹የገናናነት›› ስብዕናየሚያሳይ ሆኖ ነው የሚታየኝ፡፡ድርጅቱ ያን ግለሰብ በትክክል ሊተኩ የሚችሉ ብቁ አባላትን ማፍራት አቅቶታል፤ አልያም ግለሰቡበድርጅቱ ውስጥ ያልተቋረጠ የበላይነት (ገናናነት) አለው ልንል ነው የምንችለው ሌላ ሳይሆን፡፡አቶ አስራት ጣሴየኢህአዴግን ሰሞነኛ ጉባኤና በውስጡ የተካሄደውን የስልጣን መተካካት በተመለከተ ያሉት አስተያየትምንድን ነው?እኔ እንደ መሪ ሀሳብ አድርጌ የማስቀምጠው ‹‹ችግሩን በፈጠረው አስተሳሰብ ችግሩን መፍታት አይቻልም››በሚለው የአልበርት አንስታይን ንግግር ነው፡፡ ‹‹የማይለወጥ ነገር የለም፡፡ ከለውጥ ህግ በስተቀር››በሚለው ጥቅስም ወደ ሀሳቤ ልንደራደር እችላለሁ፡፡ የአቶ መለስ ራዕይ፣ አብዮታዊ ዴሞክራሲንማስቀጠል ይሉናል፡፡ ስለዚህ እነሱ መተካካትን ያዩት መስመርን እንደማስቀጠል አድርገው ነው፡፡ማንኛውም አስተሳሰብ፣ ራዕይም ሆነ አመለካከት የተወሰነ ዘመን ነው ያለው፡፡ ሁሉንም የታሪክ ዘመንተሻጋሪ የሚሆን ራዕይም ሆነ አስተሳሰብ ብሎ ነገር የለም፡፡ ሁሉም ነገር ይለወጣል ከለውጥ ህግበስተቀር፡፡እነኚህ ሰዎች አሁንም ችግር የሚፈቱ አይነት አይደሉም፡፡ ፓርቲው እንደ ፓርቲም እንደመንግስትምከጉባኤውና ከአቋማቸው አንፃር የኢትዮጵያን ችግር ከመፍታት ይልቅ ይበልጥ እንደሚያወሳስቡት ነውየምገነዘበው፡፡ምክንያቱም አንደኛ በለውጥ ህግ አያምኑም፡፡ አንድ ቦታ የተቸከለ አይምሮ ነው ያላቸው፡፡ መተካካትትርጉም የሚኖረው ተተኪው ወገን አይን፣ እግር፣ እጁንና ግዑዝ አካሉን ይዞ ፀጥ ብሎ እንዲቀመጥበማድረግ ሳይሆን አዲስ አስተሳሰብ፣ መፍትሄ፣ ግንዛቤና አቅጣጫን ጭምር ይዞ እንዲመጣ ሲደረግነው፡፡ ያን ዕድል ከተከለከለና እነሱ እያደረጉት እንዳለው ይሁን ከተባለ ግን መተካካት ሳይሆን ለውጡ‹‹የዱላ ቅብብሎሽ›› ነው ወይም ‹‹ሜካኒካል›› ነው፡፡ እውነቱን ለመናገር ተተኪዎቹ አይምሮአቸውንየማይጠቀሙ ከሆነ ወደ ሮቦትነት ነው እየተለወጡ ያሉት፡፡አቶ መለስ እኮ ሞተዋል፡፡ ለሳቸው ቢፈለግ ታሪክ ይፃፍላቸው፡፡ ነገር ግን የሳቸውን ራዕይ እናስቀጥላለንማለት ምን ማለት ነው? እሳቸው ምናልባትም በህይወት ቆመው ቢሆን ኖሮ እኮ ራዕያቸውን ዛሬ ላይላይከልሱትና ላይለውጡት ይችላሉ ብለን እርግጠኛ ልንሆን አንችልም፡፡ እነኚህ ሰዎች ግን ወደፊትምቢሆን የመለስ ራዕይ አይነቃነቅም እያሉ ነው፡፡ ሊጠይቋቸውም ሆነ ሊመልሱላቸው የማይችሉትን ሰውራዕይ ይዘን እንጓዛለን ማለት በራሳቸውም ሆነ በህዝብ ላይ ያለው ውጤት ጥሩ አይሆንም፡፡ይህች ሀገር በቀውስ ላይ ነች ስንል ቀልድ ይመስላል፡፡ ሆኖም ጥናቶችም ሆነ እውነታዎች የሚያሳዩትበአደገኛ ሁኔታ ላይ የመገኘታችንን ሀቅ ነው፡፡ በማኒፌስቶአችን ያሳየነው ይህንኑ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታላይ እያለንም እንኳ እነሱ ትላንትና ‹‹የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካል ኢኮኖሚ የበላይነት እንዳለው ግንዛቤተይዟል፡፡ መቀነስም ሆነ ማሸነፍ አልቻልንም›› ሲሉ ነበር ቃል በቃል፡፡ ኪራይ ሰብሳቢነት ማለትምንድነው? ኪራይ ሰብሳቢነት በሙስና መዘፈቅ ማለት ነው፣ የህዝብ ስልጣንን ለራስ ወይ የተወሰነወገን መጠቀሚያ ማድረግ፣ ኪራይ ሰብሳቢነት በኢንቨስትመንት ስም የፈረንሳይን የቆዳ ደስፋት የሚያክልመሬት በማይታወቅና በድብቅ ውል ለማንም መጤ እየሰጡ በምት ደህና ወገን ገበሬውን ለከተማ ለማኝነትመለወጥ ማለት ነው፣ ኪራይ ሰብሳቢነት ከ11 ቢሊዮን ብር ከሀገር ማሸሽም ነው፡፡እነኚህ ሰዎች አሁንም በዚሁ መንገድ እንሂድ ማለታቸው ጥፋቱን ወደለየለት ገደል መሰደድ ነው፡፡እነኚህ ሰዎች ቆምብለው ሊያስቡ ይገባል፡፡ ለ21 ዓመታት ለውጥ ያላመጣ አስተሳሰብ ይቀጥል ማለትከአደጋ ውጪ ውጤት አይኖረውም፡፡ ለዚህ ነው የአንስታይንን ችግርን በፈጠረ አስተሳሰብ ችግርአይፈታም የሚል አነጋገር የተጠቀምኩት፡፡እኛ ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግ ስልጣን መካፈል ወይ ሌላ ነገር ሳይሆን ብቸኛው የሚያሳስበን ጉዳይ ሀገርንእንደ ሀገር የማስቀጠሉ ነገር ነው፡፡በኢህአዴግ ውስጥ የሰዎች በሌሎች ሰዎች የስልጣን መተካካት መደረጉ በሀገሪቱ የሚያመጠው ፖለቲካዊለውጥ ምን ይሆናል ብለው ያስባሉ?እሱ ነው እኔም የቸገረኝ፡፡ እንደዛ እንዳናስብ ነው ያደረጉትና በሩን የዘጉት፡፡ መተካካቱን ሜካኒካልአደረጉት፡፡ የአስተሳሰብ የራዕይ ወይ አመለካከት መተካካት አላረጉትም፡፡ ያ እስካልሆነ መተካካቱ ትርጉምሊሰጥ አይችልም፡፡ ሰዎች ስብጥሮሹ እጅግ የበዛ አስተሳሰብ ነው ያላቸው፡፡ እያንዳንዳችን እኮ ባለንአስተሳሰብ ደረጃችን ፍፁም እንለያያለን፡፡ በአመራር አቅማችን በፖለቲካ ብስለታችን እያንዳንዳችን ልዩአቅም አለን፡፡ ይህ በተግባር እንዲታይ ካልተፈቀደለትና ተተኪው ኤክስና ራይት ብቻ ነው ስልክ ከተባለምንድነው መተካካቱ ፋይዳው?እነኚህ ሰዎች ቡደናዊነትን ይዘው፣ ሰብአዊ መብት እየረገጡና እየመዘበሩ በአምባ ገነንነት ነው መቀጠልንየመረጡት፡፡ ስለዚህ እኛ እስካሁን ካለፈው ሁሉ ይልቅ የሀገሪቱ መፃኢ ነው የሚያሳስበን፡፡ በግትርነትእነሱ ያሉትን ብቻ ይዞ መሄድ አደገኛ ስለሆነም ሁሉም ያገባኛል የሚል ወገን የብሔራዊ መግባባትላይበውይይት ሊደርሱ ይገባል፡፡ የተሻለ መንገድን መፈለግን አማራጭ መቀየስ እጅግ ያስፈልጋል፡፡ የዓለምታሪክ ይህንኑ ነው የሚያሳየን፡፡ እንደ ወቅት የሆነ ርዕዮተ ዓለም ይሞከራል አልሰራ ሲል ደግሞይከለሳል፡፡ ህይወት ደግሞ እየተሻሻለች የምትሄድና የአይነት ለውጥ የሚደረግባት ነች፡፡ በህይወት አለንየሚሉ ሰዎች በሙታን ራዕይ ሀገር አንገዛለን ሲሉ ማየት እኔ እንደዜጋ በጣም ያሳፍረኛል፡፡አቶ አሮን ሰይፉ (ከሰማያዊ ፓርቲ)የኢህአዴግ ጉባኤና የስልጣን መተካካት ተከትሎ የተቃዋሚዎችን አስተያየት ምን ይመስላል ብለንእየጠየቅን እንገኛለን፡፡ ይህን በተመለከተ በናንተ በኩል ምን የምትሉት አለ? መተካካቱ በሀገሪቱላይ የፖለቲካ ለውጥ ያመጣል ብላችሁ ታስባላችሁ? እነኚህን ሁለት ጥያቄዎች ጠቅለል አድርገውቢመልሱልኝ?እነሱ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ነባሩን አመራር በአዲስ አመራር እንቀይራለን ብለው ጥቂትሰዎችን ሲተኩ አይተን ነበር፡፡ ግን በዚህ ዓመት ነገሩን ይበልጥ ይገፉበታል ብለን ብንገምትም ያንሲያደርጉ አልታየም፡፡ ለምሳሌ እንኳ አንዳንድ የግንባሩ ድርጅቶች በፍፁም የአመራር ለውጥ ሳያደርጉነው የቀጠሉት፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ጭራሽ የአመራሩን ቁጥር ከመጨመርና ወንበር ከማብዛት በቀር ሲተካኩአልታየም፡፡ ጉዳዩ የህወሐት እስኪመስል ድረስ የአንድ ሁለት ሰዎች ለውጥን ካደረጉት በቀር ህወሐትብቻ ነው ሲተካካበት ያየነው፡፡እኔ እንደዛም ሆኖ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊና የአንድ ፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባል ሆኜ ነሩን ሳየውለኢትዮያ ዴሞክረሲ ምንም የሚረዳው ነገር አለ ብየየ አላምንም፡፡ የሰዎቹ መተካካት ሳይሆን አመለካታቸውነው ለዚህ ወሳኙ ነገር፡፡ ፓርቲው ለረዥም ጊዜ ኢትዮጵያን በብቸኝነትና በበላይነት ለመግዛት የቆረጠእስከሆነ ድረስ አቶ ‹‹X›› ወቶ አቶ ‹‹Y›› ቢወርድ ለኢትዮጵያ ፋይዳ ያለው ነገር ነው ብዬ አላስብም፡፡ለምሳሌ የብአዴን ሁኔታን ካየን ከሁለት ዓመት በፊት ከድርጅቱ ለቀው የነበሩት አቶ አዲሱ ለገሰ ልክእሳት እንዲያጠፋ እንደተጠራ እሳት አደጋ ደግሞ ወደ አመራርነት እንዲመጡ ተደርጓል፡፡ እነኚህናሌሎች ነገሮች መተካካቱ ከራሱ ከኢህአዴግ ጋር ብቻ እንጂ በፍፁም ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዘ እንዳልሆነየሚያሳይነው፡፡ከዚህ ጉባኤ በኋላ በዚህች ሀገር ይመጣል ብላችሁ ምትመገምቱት ፖለቲካዊ ለውጥስ ምንድን ነው?ቅድም እንዳልኩህ ነው፡፡ የኢህአዴግን አመራር እናውቀዋለን፡፡ ላለፉት ጥቂት ዓመታት እንዴትእየተለወጠ እንደመጣ፡፡ በተለይ ከ97 ምርጫ በኋላ ምንም አይነት የተለየ ሀሳብ ከየትም አቅጣጫሳይሰማ ጆሮውን ደፍኖ ለመሄድ የወሰነ እንደሆነ አውቀናል፡፡ ከዚህ ጉባኤም ቢሆን ከዚህ የተለየ ነገርይወጣል ብዬ አልጠብቅም፡፡ሀገሪቱን እየጎዳ ያለውን ይህን አስተሳሰባቸውን ለውጠው ለዴሞክራሲው ጠቀሜታ ያለውና አገዛዛቸውንየሚያለዝብ ነገር በጉባኤው እንዳነሱም አልሰማንም፡፡ ይዘው ይወጣሉም ተብለው አይገመቱም፡፡ በራሳቸውጉዳይ ላይ በቻ የተጠመዱ ነው የሚመስሉት፡፡ አገዛዙን እንዴት እናስቀጥላለን እንጂ የዴሞክራሲስርዓቱን ለማሰተካከልና ለማደላደል መዘጋጀታቸውን እጠራጠራለሁ፡፡ ስለዚህ እኔ ጉባኤው ለኢትዮጵያፍሬ ያለው ጉባኤ ነው ለማለት አልችልም፡፡

No comments:

Post a Comment