Sunday, March 17, 2013

ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም እና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች ዛሬ ታሰሩ የኢህአዴግ አፋኝ አስተዳደር የአፓርታይድ ቅርጽ እየያዘ ነው!

ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም እና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች ዛሬ ታሰሩ
የኢህአዴግ አፋኝ አስተዳደር የአፓርታይድ ቅርጽ እየያዘ ነው!
ዛሬ መጋቢት ስምንት ቀን 2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ማህበር፤ ሰማያዊ ፓርቲ እና ባለራዕ ወጣቶች ማህበር በጋራ በመሆን “ለፋሽስቱ የጦር ወንጀለኛ ለማርሻል ግራዚያኒ ክብር መስጠት የአባቶቻችን መስዋዕትነት ማራከስ ነው” በሚል የተጠራውን ሰልፍ አምባገኑ የኢህአዴግ መንግስት በርካታ የፌደራል ፖሊስ፣ የደህንነት አባላትን እና የአዲስ አበባ ፖሊሶችን በማሰማራት ሲበትን፤ የተቋማቱን ከፍተኛ አመራሮች፤ ታዋቂ ግለሰቦች እና በርካታ ወጣቶች ጨምሮ ቢያንስ 34 ሰዎች አስሯል የታሳሪዎች ቁጥር አሁንም በመጨመር ላይ ነው፡፡
እንዲሁም በትላንትናው እለት ለተቃውሞ ሰልፉ የቅስቀሳ ስራ ሲሰሩ ከነበሩት ውስጥ 2 የሰማያዊ ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ አባላትን እንዲሁም የባለራዕይ ወጣቶች የስራ አስፈጻሚ አባላትን ጨምሮ 8 ሰዎችን አስረዋል፡፡

ከኢህአዴግ ጋር የሚያገናኝ የጋራ አገራዊ አጀንዳ ይኖር ይሆን?
በእርግጥ “ጓደኛህ ሲታማ፤ ለኔ ብለህ ስማ” እንዲሉ ግራዚያኒን መቃወም ከመርህ አንፃር ኢህአዴግን መቃወም ለመሆኑ ግልጽ ነው። ሰልፉን ያዘጋጁትም ሰዎች ይሄን ይስቱታል ብዬ አልገምትም።ሰዎቹ ለፋሽስቱ ግራዚያኒ የተሠራውን ሐውልት ለመቃወም የተነሱት እነሱም በጭቆና አስተዳደር ስር በወደቁበት ሁኔታ እንደሆነ ጠንቅቀው እንደሚረዱት የታወቀ ነው።
ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ፤ዳዊት ዮሐንስ አፈ-ጉባኤ ከነበሩበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የሰማዕታት ሐውልት ስር በየ ዓመቱ የካቲት 12 ቀን የአበባ ጉንጉን ሲቀመጥ እመለከታለሁ።አንድ አንድ ግለሰብ፣ ፓርቲም ሆነ መንግስት በግፍ በተጨፈጨፉ ዜጎች መቃብር ላይ የአበባ ጉንጉን እያስቀመጠ ሲዘክራቸው፦ “እኔ የዚህን ዓይነት ግፍ አልፈጽምም” በማለት ቃል እየገባ ነው። ይሁንና በፋሽስቶች በተጨፈጨፉት ሰማዕታት ስር በየዓመቱ የአበባ ጉንጉን የሚያስቀምጠው ኢህአዴግ፤ ህፃናትን ሳይቀር ገድሎ “ቅጽል ስም” ከመስጠት የማይመለስ ፓርቲ መሆኑን ነው ያየነው።ይህም፤ ኢህአዴግ የሞራል ልዕልናም ሆነ ወጥ መርህ የሌለው ፓርቲ መሆኑን የሚያመለክት ነው። 
እንግዲህ የዚህ ዓይነቱ ገዥ ፓርቲና ጭፍን ደጋፊዎቹ ናቸው፦ “ጠንካራ ተቃዋሚ ልናይ አልቻልንም፤ተቃዋሚዎች በሚያመሳስሉን እና አንድ በሚያደርጉን አገራዊ ጉዳዮች እንኳ ከእኛ ጋር ተቀራርበው ሊሠሩ አልቻሉም።” የሚል ክስ ሲያሰሙ የሚደመጡት። ለኢትዮጵያውያን ግራዚያኒን መቃወም የጋራ አገራዊ አጀንዳቸው ካልሆነ፤ሌላ ምን አጀንዳ ነው የሚያገናኛቸው?
በአሁኑ ሰአት በእስር ላይ የሚገኙት እና ስማቸው የተገኘ
1. ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም
2. አቶ ታዲዎስ ታንቱ
3. አቶ ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ሊቀመንበር)
4. ስለሺ ፈይሳ (የሰማያዊ ም/ሊቀመንበር)
5. ይድነቃቸው ከበደ (የሰማያዊ የህግ ጉዳይ ሀላፊ)
6. ሀና ዋለልኝ (የሰማያዊ የሴቶች ጉዳይ ሀላፊ)
7. ጌታነህ ባልቻ (የሰማያዊ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ)
8. ብርሀኑ ተክለያሬድ (የባለራዕይ ወጣቶች ተ/ምክትል ሊቀመንበር)
9. ያሬድ አማረ (የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ጸሀፊ)
10. ኤልሳቤጥ ወሰኔ
11. ሰለሞን ወዳጅ
12. ወይንሸት ንጉሴ
13. እየሩሳሌም ተስፋው
14. ለገሰ ማሞ
15. ትዕግስት ተገኝ
16. አማኑኤል ጊዲና
17. አለማየሁ ዘለቀ
18. አገኘሁ አሰገድ
19. ሻሚል ከድር
20. አሸብር ኪያር
21. ጌታቸው ሽፈራው
22. ግሩም አበራ
23. አቤል ሙሉ
24. ዩሀንስ ጌታቸው
25. ስማቸው ተበጀ
26. ፍቃዱ ወንዳፍራው
27. ባህረን እሸቱ
28. ሄኖክ መሀመድ
29. እንቢበል ሰርጓለም
30. አለማየሁ በቀለ
31. ዩናስ
32. የመኪናው ሹፌር
33. ዮዲት አገዘ
34. ጥላዬ ታረቀኝ
                       
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment