በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ‹‹የዜጎቼ ሰብአዊ ክብር ተደፍሯል›› ሲል የሳውዲ ሚዲያዎችንና አንዳንድ ግለሰቦችን ሊከስ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተገለፀ፡፡
ሪያድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አምባሳደር ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ በአገሪቱ የሚፈፀሙ ማናቸውም በመሳሪያ የታገዙ የዘረፋዎች፣ የውንብድናና የማጭበርበር ድርጊቶች ‹‹ኢትዮጵያውያን ፈፀሙት›› እያሉ ማውራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ከመሆኑ በተጨማሪ በአገሪቱ የተለያዩ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችና በሌሎች ጋዜጦች ላይ ይህንኑ ስሜት ማንፀበረቅ እየተለመደ መጥቷል፡፡ ይህንን ተከትሎ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንደሌባና አጭበርባሪ እየታየ መሆኑንና ዜጎችም ስራ ለመቀጠር አስቸጋሪ ሁኔታዎች እየገጠማቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በሳውዲ አረቢያ ላሉ ሚዲያዎች ገለፁት ሲል ዢንዋ ጨምሮ ባስነበበው ዜና እንደገለፀው በህገወጥ መንገድ ወደ ሳውዲ አረቢያ ገብተው እና በውንብድና ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ምንም አይነት ራሳቸውን የሚገልፅ መታወቂያም ሆነ ፓስፖርት የሌላቸው ዘራፊዎች በተገኙ ቁጥር ‹ኢትዮጵያውያን ናቸው› እያሉ መግለጫ መስጠት እየተለመደ መምጣቱ ኤምባሲውን እንዳስቆጣና ይመለከታቸዋል ያላቸውን አካላትም ለመክሰስ ምክንያት እንደሆነው አምባሳደሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
‹‹በህገ ወጥ መንገድ የገባና በወንጀል ድርጊት ላይ ተሳትፎ የተገኘ ኢትዮጵያዊ ቢኖር እንኳ እንደ ግለሰብ ሊጠየቅ ይገባል እንጂ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ሊወክል አይገባም›› ያሉት አምባሳደር መሐመድ ሀሰን ሚዲያዎች በንፁህ ኢትዮጵያውያን ላይ ከፍ ያለ በደል እየፈፀሙ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
‹‹በዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለው የስም ማጥፋት ዘመቻ ለህግ ተገዢ የሆኑና ሰርተው ለማደር የሚጥሩ ኢትዮጵያውያን ክብር ያጎደፈ ነው›› ያሉት አምባሳደሩ በሚዲያዎች ዘገባ የተሳሳተ ግንዛቤ የያዙት የአገሪቱ ዜጎችም ኢትዮጵያውያኑን ሲያንጓጥጡ መታየት በሳዑዲ አረቢያ የተለመደ ጉዳይ ሆኗል፡፡
እግዚአብሔር ህዝቦቿን ከስደት ይታደግ!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ከሰብአዊ
No comments:
Post a Comment