Wednesday, March 20, 2013


የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ነፃነት ኮሚሽን ካለፈው ታኅሳስ 6 እስከ 10 የሃይማኖት ነፃነትን ሁኔታ ለመገምገም በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርጎ የጉብኝቱን ውጤት የያዘ ዘገባ ይፋ አድርጓል።
ባለፈው ሰኞ መጋቢት 2 የወጣው ይህ ዘገባ የኢትዮጵያ መንግሥት የሃይማኖት አክራሪነት ሥጋት ቢኖርበትም በነፃነት ማምለክንና ሌሎችም መሠረታዊ መብቶችን ማፈኑ ችግሩን ከመፍታት ይልቅ ሊያባብስ ይችላል የሚል ሃሳብ ያቀርባል።
ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደርና በዋልታ የመረጃ ማዕከል ይፋ የሆነ አንድ የሕዝብ ሃሳብ መለኪያ ጥናትም በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የሃይማኖት አክራሪነት እንደሚሰተዋል በመግለፅ ማሳሰቢያ አውጥቷል።

የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ነፃነት ኮሚሽን ከመንግሥት ተጽዕኖ የሌለበት፣ የገንዘብ እርዳታ የማያገኝ፣ በራሱ የሚተዳደር ነፃ ኮሚሽን ሲሆን በነፃነት የማምለክ ችግር የተከሰተባቸው አገሮችን በመጎብኘት ሁኔታዎችን ገምግሞ ለዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ለፕሬዚዳንቱና ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ዘገባ ያቀርባል።
በዚህ ተልዕኮ በዚህ ዓመት ብቻ ኮሚሽኑ ወደ ሳዑዲ አረቢያ፣ ግብፅ፤ ባህሬን፤ ታጂኪስታን ተጉዞ እንደነበር፣ ኮሚሽኑ የሁሉንም ሃይማኖቶች ማለትም የክርስትና፣ የእስልምናና የሌሎችንም የአምልኮ ነፃነት እንደሚከታተል የኢትዮጵያውን ጉዞ ግምገማም የሚመለከት ሪፖርት የፊታችን ግንቦት ይፋ እንደሚሆን የልዑካኑ መሪ ዙዲ ያሰር ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ የብዙ ብሔረሰቦች ሃገር ስለሆነችና የባህልና የሃይማኖት መቻቻል ታሪክም ይዛ ስለኖረች የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ኮሚሽን ለምርመራ ወደ ኢትዮጵያ ሲሄደ በታሪክ የመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ተናግረዋል።
“የኢትዮጵያንና የምትገኝበትን አካባቢ ታሪክ ብንመለከት በሚደነቅ ሁኔታ የከበረ ብዝኅነት ያለውና እሥልምና ወደተፈጠረበት ወደ ሰባተኛው መቶ ክፍለዘመን ተመልሶ የፀና በጣም በሚደነቅ ሁኔታ የኖረ የክርስትናና የእሥልምና ግንኙነትም አለ፡፡ እንዲሁም ከአጠቃላዩ ዘጠና ሚሊየን ሕዝብ ሰላሣ ሚሊየኑ፤ ሲሦው ማለት ነው ሙስሊም የሆነበት ኅብራዊ ኅብረተሰብ ነው፡፡” ብለዋል የቡድኑ መሪ ዙዲ ያሰር ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ፡፡

“ሆኖም እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከነኀሴ 2 / 2011 ዓ.ም ጀምሮ ግን መንግሥት በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ መግባት መጀመሩን ሰማን” ይላሉ ዶ/ር ያሰር፡፡
እርሳቸው እንደገለፁት ኢትዮጵያ ያለችው እንደአልሸባብ ያሉ አሸባሪዎች ባሉባቸውና ከአሸባሪ መረቦች ጋርም ግንኙነት ባላቸው አገሮች፣ በሶማሊያ በሱዳንና በኤርትራ መካከል ስለምትገኝ የአክራሪነት መስፋፋትና በተለይም   ከሳዑዲ አረቢያ የወሃቢ እሥልምና ፅንሰ ሃሳብ ወደ አገሪቱ መግባት መንግሥትን እንደሚያሳስብ ገልፀዋል።
“በዚህም ምክንያት - ይላሉ ያሰር - መንግሥት በሙስሊም ማኅበረሰቡ በነፃነት የማምለክ ሥርዓት ውስጥ ጣልቃ መግባትና አፈና ጀመረ።” የጉዟቸው ዓላማም ይህን በቅርብ ለመከታተል እንደመሆኑ ችግሩ የሚመለከታቸውን ሁሉ ማነጋገራቸውን ገልፀዋል፡፡
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment