Friday, March 1, 2013

ለምንድን ነው የምንፈራው?



አንተን ነው የምናገረው....... አዎ አንተ........ ጥግ ላይ ፈርተህ እና ተኮራምተህ የተቀመጥከው:: ለምን ትፈራለህ? መብትህን መጠየቅ ለምን ትፈራለህ? የመናገር ነፃነትህን ማሥከበር ለምን ትፈራለህ? የተወለድክባት እትብትህ የተቀበረባት ሀገርህ እኮ ናት ኢትዮጵያ ማለት :: መብትህን በሀገርህ ላይ ካላሥከበርክ የት ሄደህ ልታሥከብረው ነው? ልብ አድርግ መብትህን ነው እንጂ የጠየከው ምንም ከህግ ውጪ የሆነ ነገር አልጠየክም :: ሠዉ "አርፈህ ተቀመጥ" ብሎ አስፈራርቶሀል? እርግጥ ነው ላንተ ደህንነት እስበው ነው ::
ግን አትሥማቸው መናገር ያለብህን ተናገር ; መፃፍ ያለብህን ፃፍ ; ሀሣብህን ግለፅ :: ደግሞ መናገር እየፈለክ አስመሳይ አትሁን ህሊና የሚባል ነገር እንዳለ ዘነጋኸው እንዴ? አደራ ታዲያ ሥትናገር የሌሎችንም መብት ጠብቅላቸው :: እኔን ብቻ ሥሙኝ እኔ ብቻ ነኝ ትክክል አትበል :: የራሥህን ሀሣብ እንደምታከብር የሌሎችንም እንደዛው አድርግ :: አለበለዚያ ከመንግስት በምን ልትለይ ነው? ህግ እስካልጣሥክ የሌሎችን መብት እስካልረገጥክ አሁንም ቢሆን ተናገር ሀሣብህን ግለፅ :: እየተሸማቀክ አትኑር :: ከምንም ነገርቀድሞ ሀሣብን በነፃነት የመግለፅ መብት ይቀድማል :: አይዞህ ብቻህን አይደለህም ብዙ ኢትዮጵያውያን ለመብቶች መከበር ሠላማዊ ትግል እየታገሉ ነው ያሉት :: አንተም ነገ መብትህ ተከብሮ ማየት ትፈልግ የለ? እንግዲያውሥ ዛሬ ነገ ሳትል  ትግሉን ተቀላቀል ::
 መታገል  ባለብህ ነገር ሁሉ መታገል ይቻላል አትፍራ ከራስህ በላይ ሌላ አታጋይ አትፈልግ! ትግል ከራስ ነው የሚጀምረውና!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ከዘካሪያስ አሳዬ

No comments:

Post a Comment