Saturday, March 9, 2013

ዝም ባለ አፍ ዝንብ አይገባም ብለን ዝም ስንል ዝም ባልንበት አፍ ወንጀለኛ ተባልን።


ዝም ባለ አፍ ዝንብ አይገባም ብለን ዝም ስንል ዝም ባልንበት አፍ ወንጀለኛ ተባልን።
አማራ መሆን ወንጀል ነው? የሌሎች ብሔረሰብ አባላት በፈለጉበት ክልልና ስፍራ ይኖራሉ። አማራ ክልል ውስጥ ሰፊ መሬት ወስደው የሚኖሩ አሉ፤ የሚነካቸው የለም። አማራው እየተመረጠ ለስደት፣ ለመከራ፣ ለእንግልት ይዳረጋል? እስከመቼ በዚህ ይቀጥላል?  የአማራ ክልሉን እንመራለን፣ የአማራ ህዝብ ወኪል ነን የሚሉ የት ናቸው? ያሳዝናል! ግን ወኪሉም ተብዬው ለካ የወያኔ ስራ አስፈፃሚሆች ናቸው ለካ ምን ይደረግ ለአማራው አልቅሱ፣ ለአማራው አንቡ፣ አማራው አለቀ፣ልጆቻችን የሚቀበለን በጉዲፈቻ እያሉ …”  በስልክ ለተለያዩ ሬዲዮ ጣቢያ በስልክ ሲቃ ልሳናቸው አንቆ  አስተያየታቸው የአማራ ተወላጆች ሲናገሩ አልሰማንም የሚል የለም ካንም እኔ አይመለከተኝም ሊሆን ይችላል ግን ነገ ደግሞ በሌላው ብሔረሰብ መደገሙ የማይቀር ነውና ዛሬ ይኽን የወያኔን ስራ መቃወም አለብን
ሰሞኑን በቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል አማራውን የማፅዳት ዘመቻ ወይም የማፈናቀል ዘመቻ መጀመሩ ይፋ ሆነ እንጂ ችግሩ የቆየና ማዕከላዊ አገዛዙም ሆነ የክልሉ መስተዳድር ጠንቅቀው የሚያውቁት ጉዳይ እንደሆነም ይታወቃል የካቲት 282005  የተላለፈው ኢሳት አማርኛ ክፍል ያነጋገራቸው የችግሩ ሰለባ አሁን ያለውን ችግር የሚገልጹት በተማጽኖ ነበር
 ከዚህ በፊትም ከዓመታት በፊት መተከል ዞን ፓዌ የተካሄደውን ማስታወስ ይቻላል 1984 – 85 ፓዌ መንደር አራት በሚባለው የገበያ ቦታ እየገበዩ የነበሩ የአማራ ተወላጆች ያላሰቡት ደረሰባቸው።በድንገት ገበያው ታወከ። የቻሉትን በቀስት፣ ሌላውን በጥይት ለቀሙት። 56 ሰዎች በቅጽበት ሲረሸኑ ይህ ሁሉ ሲደረግ አገር የሚመሩት ባለስልጣኖች ድምጻቸውን አላሰሙም ነበር ሆን ብለው ያደረጉት ስለነበረ።
በጉራፈርዳ በክልሉ መንግስት ትዕዛዝ የከፋ ወንጀል ሲሰራ፣ አንደኛ ክፍል ለሚማር ህጻን ጭምርክልሉን ልቀቅና ውጣየሚል ደብዳቤ ሲሰጥ ተቆጣጣሪና ተቆርቋሪ አለመኖሩ መጨረሻ የሌለው ግፍ አማራው ላይ እንዲካሄድ ስምምነት ያለ የሚገልጹ ጥቂት አይደሉም።
በቤንሻንጉል መተከል ዞን ቡሎን ወረዳ የሰፈሩና 20 ዓመት በላይ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች በረሃውን አልምተው፣ ወልደው ከብደውና ንብረት አፍርተው ይኖሩ የነበሩ አምስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከየካቲት19 እስከ 30 ቀን 2013 ዓም መኖሪያቸውን ለቀው እንዲወጡ ታዝዘዋል የሚገርመው ግን 20 በላይ የአማራ ተወላጆች የሚኖሩ ሲሆን ቀስ በቀስ የማጣራት ዘመቻም እንደሚደረግ ይታወቃል
 የአማራ ተወላጆቹ ሰሚ አጣን”  ድምጻ የሚሰማን አጣን በአገራችንለክልሉ መንግስት ሲናገሩ፣ ሲያመለክቱ አመለከታችሁ በሚል ስለምንታሰር፣ስለምንደበደብ እባካችሁ ለፌደራሉ መንግስት አሳውቁልንሲሉ በተለያዩ መገናኛ ተደምጠዋል። አገር ቤት የመንግስትም ሆነየግልየሚባሉት የመገናኛ ዘዴዎች ጆሮ የነሷቸው ይመስል ሰምተው ዝም ብለዋል። ጥያቄ ያቀረቡት ሰዎችፈልሶ የመጣ፣መጤ፣ውጣ አማራእየተባሉ የውጭ አገር ዜጋ እንኳን በማይጠራበት ሁኔታ ክብረ ነክ ስድብ እንደሚሰደቡ ተናግረውም ነበር ተበዳዮቹየሚያሳዝነው ባፋጣኝ ክልሉን ለቀው ካልወጡ የክልሉ መንግስት ባለስልጣናት ምን ሊከሰት እንደሚችል የዛቱባቸውን ሰዎች በሚዲያም ተናግረውም ጭምር ነበር‹በአማርኛ ተናጋሪነታችን ሠርተን የመኖር ልጆቻችንን የማሳደግ ህልውና ያጣን ነን፡፡›› የሚሉት እነዚህ ዜጎች “በተደጋጋሚ ጥቃት እየተሰነዘረብን ነው፤ ከ20 ዓመት በላይ ከኖርንበት መሬት ተፈናቅለናል፡፡ ከአውሬ ጋር እየታገልን ያለማነውን መሬት ተነጥቀናል፡፡ እነሱ የሚሉን እናንተ አማራ ስለሆናችሁ በዚህ ክልል መኖር አትችሉም፡፡ ወደ ክልላችሁ ሂዱ ይሉናል፡፡ አማራ ክልልን እንኳን ሰርተን የምንበላበት መሬት ቀርቶ ጎጆ ቀልሰን የምንኖርበት ቦታ ሊሰጡን ፈቃደኛ አይደሉም፡፡” ባስቸኳይ ክልሉን ለቀው ካልወጡየፌደራል ፖሊስ ደብድቦ ያስወጣሃልየሚል ማስፈራሪያ የደረሳቸው ሰዎች ጭምር ነበሩ።
የአማራ ክልል ለምና ሰፊ መሬቱን ለሱዳን አሳልፎ በመስጠት፣ ሁመራንና ወልቃይት ገባውን ለትግራይ ክልል አሳልፎ በማስረከብ የሚታወቀውን ብአዴን ዛሬ ዝም ቢል አይገርምም እኮ ከዝንብ ማር ይጠበቃል እንዲ?  አቶ ደመቀ መኮንን በአማራው ወያኔ ስምቅምጥ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርሆነው በውለታ መሾማቸው የሚታወስ ነው።
ግን ይዄ ሁላ ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ዝም ማለቱ ነገ ዋጋ እንደሚያስከፍለውስ ሳያቀው ቀርቶ ነው።መቼም የአማራ ክልል ብአዴን ለምን ዝም አለ አንልም ምክንያቱም የወያኔ ጀሌ፣ሎሌ ሆኖ እያገለገለ ያለ እንጂ ለህዝቡ እያገለገለ እንዳልሆነ ይታወቃል።
ዝም ባለ አፍ ዝንብ አይገባም ከሆነ ታዲያ ዝም ብንልም ወንጀለኞች ሆነናን። ዝምታው ይሰበር በአንድነት የጉዳዩ ተጠቂ ነን እንበል! ኢትዮጵያ የሁላችንም ነች! ኢትዮጵያ የዚህ የዚያ ብሄር አይደለችም የሁላችንም ነች። ከጠባብ የብሄር ጎጠኞች ኢትዮጵያን እንታደጋት!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
              ከዘካሪያስ
(edenasaye@yahoo.com)

No comments:

Post a Comment