Friday, March 15, 2013

በቃን በቃን!!


ህወሃት/ወያኔ ጠባብና ዘረኛ የፖለቲካ አላማውን ከግብ ለማድረስ ላለፉት 21አመታት በመንግስት ስልጣን ላይ ተቀምጦ በፈፀማቸውና ዛሬም በሚፈጽማቸው መንግስታዊ የሽብር ተግባሮች ምክንያት የሐገሪቱ አንድነትና ሉአላዊነት እንደተሸረሸረ ፣ ሐብትና ታሪካዊ ቅርሶቹ አለ አግባብ እንደተዘረፉ ዜጎቿ እስራት፣ እንግልት፣ ድብደባ ፣ሰቆቃና ግድያ እንደደረሰባቸው አለም አቀፍ የመረጃ ምንጮች በየጊዜው ይፋ ያደረጉት ሃቅ ነው።
ከጥቅማጥቅም ታግዶ የንብረት ባለቤትነቱን ተነጥቆ…. የገጠሩ አነስተኛ ገበሬ ለባእዳንና ለባለ ሐብቶች…..ጥቅም ከይዞታው ያለ ፈቃዱ ያለ መጠጊያና ያለ ዋስትና ተፈናቅሎ .ረሀብ ድህነት እና ግፍ ያስመረረው በሌላ በኩል ቤተሰቡን ወገኖቹን የሚወደውን አካባቢና ታሪካዊ ሐገሩን ጥሎ መሰደዱን የባዕድ መሬትና ድንበር ሲያቋርጥ በማያውቀው ምድር ለእስር መዳረጉን በባህርና በየበረሃው ወድቆ መቅረቱን በጠቅላላው በዜጎቿ ላይ ስለደረሰውና በመድረስ ላይ ስላለው ግፍና በደል ከኛ ይበልጥ በርካታ የውጭ ምሁራንና አለም አቀፍ ድርጅቶች ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ። ያለ ነፃነት መኖር በቃን! በቃን መኖር ሰለቸን ለውጥ ያስፈልጋል ???
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment