Saturday, March 23, 2013

ኢህአዴግ ከ700 በላይ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ሰብስቦ ቅስቀሳ አደረገ


ትናንት ሀሙስ መጋቢት 12 ቀን 2005 ዓም የኢህአዴግ መንግስት 740 በላይ የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎችን ስድስት ኪሎ በሚገኘው ስብሰባ ማእከል ለአንድ ሙሉ ቀን በመሰብሰብ በመጪው የአዲስ አበባና አካባቢ ምርጫ ኢህአዴግን እንዲመርጡ ቀስቅሷል። ለእያንዳንዱ ተሳታፊ 100 ብር ከመስጠት በተጨማሪ  የምሳ፣ የቡና እና የሻ ግብዣም አድርጓል።የጎዳና ተዳዳሪዎች ትናንት 230 ላይ ነጭ ቲሸርት ለብሰው እና  የኢህአዴግ አርማ ያለበት የወረቅት ኮፍያ አድርገው ወደ ስብሰባው አዳራሽ የገቡ ሲሆን፣ በስብሰባው ላይ  ኢህአዴግ ለጎዳና ተዳዳሪዎች ካለፉት መንግስታት በተሻለ እንደሚያስብላቸው፣ የሙያ ስልጠና ሲሰጣቸው መቆየቱን እና በዚህም እንቅስቃሴ ለቁም ነገር የበቁ የጎዳና ተዳዳሪዎች መኖራቸውን ገልጿል።

የጎዳና ተዳዳሪዎችን ማሰልጠንና በአንድ አካባቢ አሰባስቦ የማኖር እቅድ እንዳለውም ኢህአዴግ ለጎዳና ተዳዳሪዎች ገልጿል። አንዳንድ የጎዳና ተዳዳሪዎችበምርጫ ተሳትፈን ስለማናውቅ እንዴት እንደምንመርጥ አናውቅም ቀኑንም አናውቅም፣ ማንን እንደምንመርጥም አናውቅምበማለት ጥያቄ ሲያቀርቡ፣መቼ እና ማንን እንደምትመርጡ እኛ እናሰለጥናችሁዋለን፣ እናሳውቃችሁዋለን፣ ኢህአዴግን ከመርጣችሁ ችግሮቻችሁ ይፈታሉበማለት መድረኩን ይመሩ የነበሩ ባለስልጣናት መልሰዋል።
አንድንድ የጎዳና ተዳዳሪዎች ምንም አይነት ቋሚ አድራሻ እና የቀበሌ መታወቂያ እንደሌላቸው የገለጹ ሲሆን ሰብሳቢው እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ተወክለው የመጡት የፖሊስ ባልደረባችግር የለም ስማችሁን በትክክል አስፍሩ እንጅ በአቅራቢያችሁ በሚገኙ ቀበሌዎች የመታወቂያ ወረቅትይዘጋጅላችሁዋል ፎቶም ትነሳላችሁየሚል መልስ ሰጠተዋቸዋል።
በእረፍት ሰአት ወጣቶች የተሰጣቸውን የታሸገ ውሀ በሲጋራ ሲለውጡ እና በርካሽ ዋጋ ሲሸጡ መታዘቡን ዘጋቢያችን ገልጿል።
በቅርቡ በሚካሄደው የአዲስ አበባና የአካባቢ ምርጫ 33 የፖለቲካ ድርጅቶች ለመሳተፍ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን  ይታወሳል።አስገራሚው ነገርይላል ዘጋቢያችን ሪፖርቱን ሲያጠቃልል፣  “የምርጫ ካርድ የመውሰጃ ጊዜ  እንዳለፈ ከተነገረ ከወራት በሁዋላ የጎዳና ተዳዳሪዎች የምርጫ ካርድ እንዲወስዱና እንደሚርጡ አሁንም እየተቀሰቀሱ ነው።
ኢህአዴግ 2002 ዓም ለተደረገው ብሄራዊ ምርጫ   52 ሚሊዮን ብር ማውጣቱን ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment