“ብሶት የወለደው ጀግናው የህወሓት ሰራዊት አዲስ አበባን ተቆጣጠረ…”
ይህን “ሰበር” ወይም “ሰባሪ” ዜና ግንቦት 20፣ 1983 ዓ.ም የሀገሪቱ ሬዲዮ ጣቢያ ያስተላለፈው ነበር። እስከ 1983 ዓ.ም ድረስ ስንት ጉንቦቶች አለፉ! ከአስራ ሰባት በላይ።
የህወሓት ፊታውራሪዎች ዓይነ ህሊናቸው ደደቢትን እንዲማትር ያደረጋቸው ፣ የብሄር ብሄረሰቦች ጭቁና፣ “የኤርትራ ቅኝ ተገዥነት”፣ የፍትህ እጦት፣ “የአንድ ብሄር የበላይነት”…ሌላም ሌላም ችግሮች አንደሆኑ እስከ ዶቃ ማሰሪያችን ደግመው ደጋግመው ግተውናል። ለማይገባን ደግሞ በፊልም መልክ ሰርተው ሰጥተውናል(አሳጥተውናል)።
እናም ትምህርታቸውን እየጣሉ (ከብዷቸውም እንደሆነም እንጃ!) የአስመራው “ከበሌ” ወደ ናቅፋ፣ የአድዋው “ቡችላ” ወደ ደደቢት ኮበለሉ- ብረታዊ ቃልሲ ለማካሄድ፡፡ (ንህዝቢ አምሓራ ንምድምሳስ) (አቶ ለገስ ይታገሉ አይታገሉ አላውቅም)
ህወሓት ችግረኛ የትግራይ ተማሪዎችን ለመርዳት በሚል አዲ አበባ ዩኒቨርሲቲ ላይ ማህበረ ገስገስቲ ትግራይ (ማገብት) በሚል በትግራይ ተወላጅ ልጆች እንደተጠነሰሰ ልብ ይሏል። ርዳታው ሽፋን ነበር። ለህወሓቶች አጀንዳ ቀርፆ የሰጣቸው ዛሬ ያልተዘመረለት የያኔው “መሓኒዲስ” አቶ ኢሳያስ ነበር።
“ነፃነቴን አጣሁ፣ ህዝቤ ፍትህ ተነፈገ፣ ሀገሬ እየደማች ነው” ብሎ ጫካ ለሚገባ በግሌ አሁንም እደግፋለሁ። ነገር ግን የጫላን እና የአበበን መብት ረግጦ የሓጎስን ወይም የገብረትንሳኤን መብት ለማስከበር ከሆነ ያ ሰው አስተሳሰቡ ቃሪያ ነበር ማለት ነው። ሰብኣዊ መብት የሰው ልጆች ነውና። “ጀግኖች ህወሓቶች” ግን ወደ ደደቢት በረሃ ሲያቀኑ ያቀነቅኑት የነበሩት ፀረ- አማራ ነበር። ከ66 እስከ አሁን የሚዘፈኑት የትግርኛ ዘፈኖች ትርጉማቸውን ላወቃቸው የአማራ ህዝብ ለትግራይ ብሄረሰብ ጠላት እንደሆነ የሚስብኩ ናቸው። “…አርኪብካ በሎ ነዚ ዓሻ አምሓራይ” የሚለውን ዘፈን በየስብሰባው እየከፈተ እንጡት እንጡጥ ለሚለው የብኣዴን ካድሬ እና የመንደር ተላላኪ ትርጉሙ ቢነገረው ምን ይል ይሆን! እዚጋ ወራጅ አለ! ለብኣዴን ሆድ እንጂ!…..ለነገሩ ብኣዴን የተመሰረተው በአማራ ህዝብ ልጆች ሳይሆን በትግራይ ብሄር ልጆች ስለሆነ ውስጣቸው ሲገለጥ ህወሓት……
ወደ ዋናው ቁም ነገር ስመለስ የህወሓት የመጀመሪያ ዓላማ የአማራን የበላይነት ገርስሶ ዳግም እንዳያንሰራራ በማድረግ ከወሎ እና ከጎንደር ተወሰዱብን ያሏቸውን መሬቶች አስመልሶ “ታላቋ ትግራይን” መመስረት ነበር። (ለዚህ ነበር አቶ መለስ አሰብን የእኛው ስለሆነች ከኢሳያሳ ጋ ትቆየን ብለው በኋላ ነገሩ ሲገለበጥ ቃላቸውን ማጠፍ ሀፍረት ሆኖባቸው፣ ወደብ የሚጠይቁት “ነፍጠኛ አማራ፣ ትምክህተኛ፣ ከአዝማሪ የማይሻል የአማራ ፕሮፌሰር ብቻ” ነው በማለት ሊስቁ ይሆን ሊሳለቁ የሞከሩት። ለእሳቸውማ ኢትዮጵያ ምናቸውም አይደለች። ለካ ሀገሬ ማለት ያሰድባል፡፡ ለካ አልገባን ብሎ ነው እንጂ ለኢትዮጵያ የማያስብ ሰው ነው የሚያስተዳድራት፡፡ እንዲህ ነው እንጂ መሓንዲስ ወይም መንዲስ! በነገራችን ላይ አይተ መለስ እንዴት እንደተወለዱ ያውቃሉ ዜናዊ አስረስ ጣሊያንን እየመሩ ጎንደርን እና ትግራይን ያስወርራሉ። ባንዳ ሆነው። ይህን ያየ አንድ የትግራይ ሰው “አቶ አስረስ ርጉም ውሻ ውለድ” ብለው ረግመው ትግራይ ውስጥ ሚስት እንዳያገቡ ሁሉ ያደርጋሉ። በዚህ ጊዜ አቶ አስረስ ሓማሴን አውራጃ ሄደው ወ/ሮ አለማሽን ያገባል። ከዚያ….ተወለዱ….ለእናት ሀገሬ ኤርትራ እንዳሉ ሞቱ…. )
“ጀግናው” የህወሓት ሰራዊት አዲስ አበባን ሲቆጣጠር “ታላቋ ትግራይን” ከመመስረት የበለጠ የታላቋ ኢትዮጵያ ገዥ የመሆን እድል መጣና አቶ ለገስ፣ ግልፍተኛው ኢሳያስ እንዳያለቃቅስ አሰብን መርቀው አባረሩትና አራት ኪሎ ጉብ አሉ። “ታላቋ ትግራይ” የሚለውን ቅዠታቸውን በይደር አቆዩት፡፡ የማይመች ነገር ከመጣ ሊመለሱበት፡፡ (ለነገሩ የታላቋ ትግራይ ምናምን በትግራይ ህዘብ ተቀባይነት አላገኘም ነበር፡፡ ወዲ አፈወርቂም ወዲ ዜናዊ ሲሸውዳት ተናዳ ወረረችን፡፡ ባድመን ፈልጋ እኮ አልነበረም…እኛ ጠፍቶን ነው… )በአማራ ህዝብ ላይ ያላቸው ጥላቻ ግን እየጋመ ሄደ እንጂ አልበረደም። እናም “መሓንዲሱ” መለስ ይህን የፈረደበት ህዝብ የማጥፋት የረጅም ጊዜ ስትራቴጂ በሰፊው ነደፉ። በወልቃይት እና ሁመራ የሚኖሩትን የአማራ ህዝቦች በማፈናቀል የትግራይ ብሄሮችን በማስፈር የዘር ማጥፋት ወንጀል በመፈጸም አሃዱ አሉ። በአላማጣ ክልኤቱ። ቀጥሎም በጎንደር፣ በጎጃም፣ በወሎ፣ በሸዋ ምንም አይነት ፋብሪካ እንዳይቋቋም፣ ደርግ ሁሉም ወደ ጦር ግንባር እንደሚለው ወያኔ ደግሞ ሁሉም ነገር ወደ ትግራይ ማለት ያዘ፡፡ ይህ ህዝብ ወደ ፊት ጥገኛ ሆኖ እንዲቆም ለማድረግ የዋልድባን ስካር ፋብሪካ በትግራይ 36ኛው ፋብሪካ አድርገው ማቋቋማቸው ለዚህ ማጠናከሪያ ነው። (ካልጠፋ ቦታ ገዳማ አርሼ ስኳር ፋብሪካ ካልገነባው ያለው ከክልሉ ሊወጣበት ስለሆነ ነው፡፡ በራሱ አጠራር “አማራ ክልል” ብሎ በሰየመው ቦታ ይህ ነው የሚባል ተቋም የለም፡፡ የክልል ዋና ከተማ ባህርዳር እንደሆነች ጣናን እና በትግሬው ብሄር የሚተዳደረውን ጊዮን ሆቴል ታቅፋ ተቀምጣለች። ሌላው በክልሉ የሚማሩ ተማሪዎች የላሸቁ እንዲሆኑ ምን ማድረግ አለብን በማለት ውዱብ ህወሓት በሰፊው መክራበታለች። አሁንም 1 ለ 5 በሚል የተያይዘህ ላሽቅ ድብቅ ፖሊሲ እያራመደች ነው፡፡ ይህች “ወርቅ” ከሆነው ሕዝብ የተፈጠረች ውዱብ ከዩኒቨርሲቲ አመራርነት ጀምሮ በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች አማራዎች እንዲገለሉ፣ በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ አማሮች እንዳይሳተፉበት አድርጋለች፡፡
ሌላው 30 ሚሊዮን ህዝብን ብቻውን መታገል እንደማይችል ሲያውቀው “መሓንዲሱ” ሌላ ስልት መነደሱ። ወደ ደቡብ ወረድ ብለው፣ “እንደዚህ በድህንት እንድትማቅቁ ያደረጓችሁ አማሮች መሆናቸውን ታውቃላችሁ” ወደ ኦሮሞው አለፍ ብለው “6 ሚሊዮን አሮሞዎችን የጨፈጨፉት አፄ ምኒሊክ መሆናቸውን እንዴት ትረሳላችሁ! የኦሮሞ እናቶችን ጡት የቆረጡት አማሮች መሆናቸውን ለልጅ ልጆቻችሁ አውርሱ!” (በትምህርት ካሪኩለም ተካቷል) ልዩነት የሚያስደስተው ወያኔ ከወለጋ እና ከጎጃም ቆራርጦ ጉምዝ ብሎ በሰየመው ቦታ “እንደዚህ ጥቁር የሆናችሁት በአማሮች ተንኮል መሆኑን ታውቃላችሁ” ሲል እሱ ብቻ አሳቢያቸው እንደሆነ ሸወዳቸው። አዋሳን ሐዋሳ (በሐ እና በአ መካከል ያለውን ልዩነት ንገሩኝ) ናዝሬትን አዳማ፣ ደብረ ዘይትን ቢሾፈቱ፣ አለማያን ሐሮማያ በማለት ለኦሮሞ ህዝበ የተለየ እንደሰራ እና አማራን ለማጥፋ ከጎኑ እንዲሰለፉ አታለላቸው። የኦሮሞ ህዝብ የሚፈልገው መብቱ እንዲከበርለት፣ ነፃነቱን እንዳይነፈግ፣ እውነተኛ ተወካዮቹ እንዲመሩት እንጂ ናዝሬት አዳማ እንዲባልለት አይደለም፡፡ “ቅኝ ተገዥ ነበርክ” አይነት ሰባካም ያካሂዳል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ አብዛኛው ማን ሆኖ ነው የኦሮሞ ህዝበ ቅኝ የሚገዛው፡፡ ኢጆሌ ኦሮሞ ልብ ብለህ ስማ፡፡ ካንተ የበለጠ ኢትዮጵያዊ ማን ነው! “ለዚህ ያበቃውህ እኔ ነኝ፡፡ ስለዚህ ዝም ብለህ ተገዛ” ቢልህ አትስማው፡፡ አናሳው ብሄር (ሶስት ሚሊዮን ብሄር) እንኳ ይህችን ሀገር እያስተዳደረ ነው፡፡(አይ ማስተዳደርi እየተዳደረባት) የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ዕላማ የሀገሪቱን ትልልቅ ህዝቦች (አማራ እና ኦሮሞ) አጣልቶ 4 ኪሎ ተኮፍሶ ትግራይን ማልማት ነው፡፡ (በነገራችን ላይ በትግራይ መልማት ቅሬታ የለኝም፡፡ የእናቴ የትውልድ ቦታ ነው፡፡ ነገር ግን ትግራይ ለመልማት ያባቴ ትውልድ ቦታ ወሎ መድማት የለበትም! እኔ እንደ አቶ ሰውዬው አጥንት እየቆጠርኩ እንትን አልልም፡፡ ኢትዮጵያ ነች ሀገሬ፡፡ ለነገሩ እኔም ባንድ በኩል ለካ “ወርቅ” ነኝ! አይ የኔ ነገር..ኢትዮጵያዊነቴን እንጂ ህን ረስቼው! ግን ችግር የለውም፡፡ እድሜ ለወያኔ ታስታውሰኛለች፡፡ እኛ ራያዎችም ወዳልፈለግነው ቦታ በመከለላችን ያልተመለሰ ጥያቄ አለን! ኋላ እስራኤል እና ፍልስጤም እንዳንሆን)
እናም ሰሞኑን እየሆነ ያለው አማራውን የማጥፋ ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠሉን ነው። አማራ በገዛ ሀገሩ ከሀገር ውጣ እየተባለ ያለው በህወሓት የዘመናት አጀንዳ ነው። የኦሮሚያ፣ የሀረሪ፣ የቤንሻንጉልም ሆነ የደቡብ ህዝብ የአማራን ህዝብ በጭራሽ ከሀገራችን ውጡ አይልም። ይህ የሆነው በህወሓቶች ቀጥተኛ ትዕዛዝ ስለመሆኑ የሚጠራጠር የአማራ ህዝብ ካለ ወንቅሸት ገብርኤል ሂዶ ይጠመቅ። ውድ የደቡብ፣ የኦሮሚያ፣ የቤንሻንጉል፣ የአፋር፣ የጋምቤላ ወንድሞቻችን! እነዚህ ምስኪን ኢትዮጵያዊያን ጎዳና ላይ ያለ አምስት ሳንቲም ሲወድቁ ምን ተሰማችሁ ይህ “ነገ በእኛ ቢደርስ” ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ ማለትም ሕወሓት ለስልጣኑ ጠቃሚ ሆኖ እካገኘው ድረስ ኦሮሞ ሀገራችን ለቃችሁ ውጡ ማለቱ አይቀርምና ነው፡፡
ውድ የሀገራችን ህዝቦች የወያኔን ሴራ ልናውቀው እና ልናከሽፈው ይገባል፡፡ የሌላውን ህዝብ በአማራ ህዝብ ላይ በጠላትነት የሚያሰልፈው ለማን ጥቅም ነው በየሜዳው የወደቁትን ህዝቦች እናስብ፡፡ ንፁሃን ዜጎች ናቸው፡፡ ሰፊው የአማራም ሆነ የኦሮሞ እውነተኛ ተወካይ የለውም፡፡ እኛው ካልደረስንለት ማንም አይደርስለትም!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
No comments:
Post a Comment