''በግል ሥራ የሚተዳደሩ መሆናቸውን የገለጹና ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረቡት አቶ መስፍን አህመድ የተባሉ ተጠርጣሪ፣ ክሱ ተነቦላቸውና ዋስትና ተከልክለው በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ታዟል፡፡''
እኔ የምለው የፀረ ሙስናን ክስ ሊያስቆም የሚችል የበላይ ኃላፊ ማን ነው? ደግሞስ አቃቢ ሕግ ይህንን ሲናገር እንደ ሕግ አስከባሪ አካልነት ከተጠያቂነት ያድነዋል? ''የበላይ አዟል'' በሚል አነጋገር ሕግ ይሻራል? ነገሩ ስንት በተደረገባት ሀገር ይህ አይደንቅም። ''የበላይ አዟል'' ብሎ ከቤት ሄዶ ተጠቅልሎ መተኛት ግን ለአቃቢ ሕግ? ኢትዮጵያ!!!!!
''ሌላው ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረቡት ተጠርጣሪና በግል ሥራ የሚተዳደሩ መሆናቸውን የገለጹት፣ ነገር ግን ቀደም ብሎ በባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት የግብር አወሳሰንና ምርመራ ኦዲተር እንደነበሩ በክሱ የተጠቀሰው አቶ ዳንኤል ገብረ ኪዳን፣ የተጠረጠሩበትና የተከሰሱበት ጉቦ የመቀበል የሙስና ክስ ተነቦላቸው የተጠቀሰባቸው የወንጀል አንቀጽ ዋስትና የሚከለክል ባለመሆኑ በ15 ሺሕ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ተደርጓል፡፡''
''በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ክስ ከተመሠረተባቸውና የዋስትና መብት ተነፍገው በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከራከሩ ትዕዛዝ ከተሰጠ በኋላ በምን ምክንያት እንዲፈቱ እንደተወሰነ፣ መጀመሪያውኑ ስማቸውን በክስ ሰነድ ውስጥ ማካተት ሳያስፈልግ ወይም ከተካተተም በኋላም ቢሆን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ክሱን መሰረዝ ወይም ማቋረጥ ያልተቻለበትን ሁኔታ የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ማብራሪያ እንዲሰጠን ላቀረብነው ጥያቄ፣ ‹‹የበላይ ኃላፊዎች ውሳኔ ነው፡፡ ደግሞም ኮሚሽኑ የመክሰስና ክስ የማቋረጥ ሥልጣን ስለተሰጠው ማቋረጥ ይችላል፤›› ከማለት ውጪ ተጨማሪ ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም፡፡''
ዝርዝሩን ከሪፖርተር ጥቅምት 27/2006 ዓም
No comments:
Post a Comment