አበራ ሽፈራው (ከጀርመን)
በዓለማችን የችግርና የመከራ አገራት ተብለው በአሁኑ ሰዓት ከሚፈረጁ አገራት መካከል የአፍሪካ በተለይም የምስራቅ አፍሪካ አገሮች ዋናውን ድርሻ የያዙ መሆናቸውን ማናቸውንም መረጃ አስቀምጦ ማስረዳት ይቻላል። እነዚህ አገራት በተለይም በእርስ በእርስ ጦርነት፣በስደት፣በረሃብ፣ በግድያዎች፣ በመሬት ንጥቂያና ማፈናቀል፣ በሃብት ብዝበዛ፣ በሙስናና በሌሎች የፖለቲካ፣ የማህበራዊና የኢኮኖሚ ችግሮች ተተብትበው ይገኛሉ። በተለይም ባለፉት 40 ዓመታት የታዩት እውነታዎችን ስንመለከት ደግሞ ይኸው ሁኔታ በእነዚህ አገራት ጎልቶ መታየቱ እውነት ነው።
እነዚህ አገራት ባለፉት ዓመታት የታየባቸውን እውነታዎች ስንመለከት በተለይም ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳንና የዛሬዋን ኤርትራን፣ ዛሬ ዛሬ ደግሞ ኬንያም ስንመለከት እጅግ በለየላቸው አንባገነኖች፤ ለራሳቸውና ለቡድናቸው ጥቅም በሚሯሯጡ፣ ከህዝባቸው ይልቅ ለራሳቸውና ለቡድናዊ ሥምና ዝና ይጠቅመናል ያሉትንና የጌቶቻቸውን ጥያቄና ፍላጎት ለማሟላት በሚሯሯጡ ፤ ዘር ቆጥረው ወገንተኝነትን ፈጥረውና በአካባቢና በጎሳ ተደራጅተው የሌላውን ህዝብና ጎሳ ለማጥቃት ተደራጅተውና ታጥቀው በተነሱ ፤ ስውር ግቦቻቸውንና ተልዕኮቻቸውን ለማስፈጸም በወንድሞቻቸው ደምና ሥጋ ላይ በሚረማመዱ፤ ለዚች ምድር ክፋት መገልገያነት የሚያገለግሉ መሪዎች በነዚህ አገራት መኖራቸው ደግሞ ተጨማሪን ችግር እያባባሰ ከመሆኑም በላይ አገራቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለመከራ የተጋለጡና ህዝቦቻቸውም ለተለያዩ መከራና ችግር እንዲጋለጡ አድርጓቸዋል።
እነዚህ አንባገነኖች ህዝቦቻቸው ነጻነትን ሲጠይቋቸው መልሳቸው ማሳደድ፣ መግደል፣ማሰር፣ መንጠቅ፣ ማፈናቀልና የወደዱትን ሁሉ ይልቁንም በእነሱ ላይ ሊፈጸም የማይፈልጉትን ሁሉ በህዝቡ ላይ በተለይም በንጹሃን ላይ ሲፈጽሙ ይገኛሉ። የውጭ አጋሮቻቸው ተው ሲሉአቸው በኛ የውስጥ ጉዳይ አትግቡ ፣ልማታዊ መንግስት ነን፣ አዳዲስ ፕሮጆክቶች ፈጥረናል፣ ዲሞክራሲን እናሰፍናለን፣ስለህዝባችን አይመለከታችሁም ከእናንተ በላይ እኛ ህዝቡን እናውቃለን ለህዝባችን እኛ እናስብለታለን፤ ይልቁንም እንዚህን ጥያቄዎቻችሁን ተው እና እናንተ የፈለጋችሁን ጠይቁን እሱን እናስፈጽማለን። በሽብር ሰበብ ወታደር ላኩ ካላችሁን እንልካለን፤ አሸባሪ ያላችኃቸውን ተዋጉ ካላችሁን እኛ ወታደር እንልካለን እነሱ ይዋጋሉ። የዲሞክራሲ፣የሰብአዊ መብትን ጉዳይ፣የእኩልነትን ጉዳይ፣የፍትህና የነጻነትን ጉዳይ፣የነጻ ፕሬስን ጉዳይ ፣የመሬት ማፈናቀልን ጉዳይ አታንሱብን እንጂ ሌላውን እናንተ የጠየቃችሁንን እንፈጽማለን የሚሉ ለመሆን በቅተዋል።
ዛሬ ዛሬ ዓለም በትልቁ የተረዳው ይመስላል ሁለቱ የሱዳኑ አልበሽርና የኬንያው ኬንያታ በ ICC ከሚፈለጉ ወንጀለኞች መካከል ለመሆን በቅተዋል ። ይህንን ዓለም ያወቀውን የየአገራቱን መሪዎች ሃጥያት፤ በግልጽና በአደባባይ የታየውን እውነትና እውነተኛ ፍርድን ለማስቀረትና፤ የኬንያውያንንና የሱዳንያውያንን የንጹሃንን ደም ከንቱ ለማድረግ ፤ለእነዚህ ተፈላጊ ወንጀለኞች ጥብቅና በመቆም የእኛዎቹ የኢትዮጵያዎቹ የህወሃት ወንጀለኞች ትልቁን ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ። ነገ በእኛ ላይ ይመጣል ይህ ጉዳይ አስጊ ነው የሚሉ ይመስላል፤ ይሁንና ይህ ድርጊታቸው በሌሎቹ በራሳቸው ስራና ተግባር በሚተማመኑ የአፍሪካ አገራትና መሪዎች ፊት ከመቅለል ውጭ ምንም አላተረፈላቸውም።
ህወሓቶችና ባለሟሎቻቸው የሰውን ፍርድ በዚህና በመሳሰሉት መልኩ ለማምለጥና ለማጣመም ይሞክሩ ይሆናል፤ የአምላክን ፍርድ ግን እንዴት ያመልጡት ይሆን?
እነዚህ የምስራቅ አፍሪካ አንባገነን መሪዎች በየአገራቱ ያለውን የሰውን ሃይል፣የተፈጥሮ ሃብትና ንብረት፣መሬትን፣የአገራቱን ለመካከልኛው ምስራቅ፣ ለአውሮፓና ለሌሎች አገራት ያላቸውን ስትራቴጂካዊ ተጠቃሚነታቸውንና፤ ለልዩ ልዩ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ማዋል የሚችሉበትን ሁኔታዎችና ሌሎችንም መልካም ተፈጥሮአዊ አጋጣሚዎችን ለመጠቀምና ህዝቡንና የየአገራቱን ሃብቶች በተገቢው መልኩ ለመምራት ባለመቻላቸው፤ ዛሬ የነዚህ አገራት ህዝቦች ለለየለት ችግርና መከራ፣ለጦርነት፣ለስደትና በስደት ላይ ለሚታዩ ታላላቅ መከራዎች ምክንያቶች መሆናቸው የተሰወረ አይደለም።
እነዚህ የምስራቅ አፍሪካ አገራትና ህዝቦች ለሰው ልጆች ስብዕና ስሜት በማይሰጣቸው፣የህዝቦች መከራና ህመም በማያማቸው ሰዎች እጅ በመውደቃቸው፤ ለከፋ ችግር እንዲጋለጡ ከማድረጉም በላይ ዛሬ ዓለም በተለየ ሁኔታ የሚያያቸው አገራትና ህዝቦች ለመሆን በቅተዋል።
የእነዚህ አገራት መሪዎች 20 ዓመታትና ከዚያ በላይ በመምራት ይታወቃሉ። አንዳንዶቹ የይስሙላ ምርጫ አዘጋጅተው የምርጫ ኮሮጆዎችን መልሰው በጥይጥ ሲሰርቁ ይገኛሉ። ይህ ጉዳይ በኢትዮጵያና በኬንያ የታየ ሲሆን በተለይም በኢትዮጵያ ሁኔታው በተደጋጋሚ መታየቱ ከዓለም አይን የተሰወረ አይደለም።
ከነዚህም አምባገነኖች መካከል ደግሞ የኤርትራውን አምባገነን አመራር ብንመለከት ጭራሹን ምርጫና ዲሞክራሲ ቀርቶ ከመለስተኛ አንባገነንነት ወደ ፍጹም አምባገነንነት እየተለወጠ፤ አብረዉት የታገሉትን እየበላ፤በእስር ቤቶች እያሰቃየ፤ የአገሪቷን ወጣቶች ደም ማፍሰስና ማድማትን ተያይዘዉታል። የኤርትራውያን እናቶች በእነዚሁ የሰይጣን ፈረሶች ምክንያት የመጣባቸውንና የልጆቻቸውን የደምና የሞት እንባ ሳያብሱ፤ በልጅ ልጆቻቸው ላይ የሚደርሰውን ስቃይና መከራ እያዩ የኤርትራውያን እናቶች እንባ ለዓመታት እንዲቀጥል ምክንያት ሆነዋል። በሻዕቢያ ቁንጮዎች ምክንያት የኤርትራ ወጣቶች በየበረሃው የአካላቸው ስጋ እየተቆረሰ የሚሸጥበት ዘመን ላይ ደርሰናል፤ ይህም የሚፈጸመው ወገኔ በሚሏቸው እጅ መሆኑ ደግሞ ችግሩን መራራ እያደረገው ይገኛል።
ከስደት ጋር በተያያዝ በአፍሪካ በረሃዎችና በአውሮፓ ባህሮች ውስጥ ለሞት የሚዳረጉና፤ መከራቸውን የሚያዩ ኤርትራውያንና ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ እየጨመረ መምጣቱ እየታየ መሆኑና የዓለም ህዝብም እያየው ያለ ጉዳይ መሆኑም፤ በዚህም ምክንያት ህፃናት፣ወጣት ሴቶችና ወንዶች ፣ አዋቂዎች ለከፍተኛ ችግርና ሞት መዳረጋቸውና፤ የሱማሌያውያንም ችግር በዚሁ መልኩ የቀጠለና የተባባሰ መሆኑ ለዚህ ችግር መባባስም የሻዕቢያውና የህወሓት አስተዋጽኦ ቀላል እንዳልሆነ ይታወቃል።
ሱማሊያ ዛሬ ላለባት ችግር መባባስ የህወሃትና የሻዕቢያ የውድድር ሜዳ መሆኗም አስተዋጽኦ አድርጓል።የራሳቸውን ህዝቦች ችግር መፍታት ያልቻሉት እነዚህ የምስራቅ አፍሪካ ጠንቆች በሌላ አገር ጣልቃ ገብተው የሚፈጥሩት ውድድር የብዙ ኢትዮጵያውያንንና የኤርትራውያንን ደም ከማፈሰሱም በላይ በሱማሌያውያን መካከል ያለውን ውጥረት በማባባስ ደረጃ በእሳት ላይ ቤንዚል የመለኮስ ተግባር በመፈጸምና በብዙ ሱማሌያውያን ህይወት መጥፋት የሚያደርገው አስተዋጽኦ ቀላል አይደለም። ይህ የሁለቱ አገራት ቡድኖች በሱማሌያውያን ላይ የፈጠሩት የማይረሳ ጠባሳ በተለይም ለሁሌም ጎረቤት አገር ለሆነችው ሱማልያ ትልቅ የበቀል አይን ማረፊያ በመሆን ኢትዮጵያ እንድትታይ እንደሚያደርጋት ምንም ጥርጥር የለኝም።
ሻዕቢያና ህወሓት በየአገራቸው ያልነኩት ግለሰብ፣ቡድንና ህዝብ የለም በጎረበት አገራትም ቢሆን ያልደረሱበት የለም ጠንቁ ግን ሁሌም ለሃገራቱና ለህዝቦቻቸው ይሆናል፤ ሻዕቢያና የህወሃት የመቃብር ጊዜያቸው እየተፋጠነ እንዳለ ሰፊ ምልክቶች አሉ።
ለአገራቸውና ለህዝባቸው ምንም የማያስቡት የህወሃትና የሻዕቢያ መሪዎች ላለፉት 39 ዓመታትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ የሰው ልጅን ደም ከንቱነትን በተለማመዱበትና በተረዱበት ሰይጣናዊ እውቀታቸው የተነሳ እነዚህ ሰዎች ለሰው ልጅ የመኖር ተፈጥሮአዊ መብት ምንም ዴንታ ሳይሰጣቸው ዛሬም የእነዚህ አገራት ወላዶች አምጠው የሚወልዷቸውና የሚያሳድጓቸው ሁሉ ለህወሃትና ለሻዕቢያ የደም ግብር እየዋሉ መሆኑ ደግሞ እጅጉን ጉዳዩን መራራ ያደርገዋል። ይህ በየሜዳው የሚፈሰው ደም ግን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ደም የፈሰሰለትና ለመኖርም እንዲችል ከአምላክ የተፈቀደለት እንጂ የምስራቅ አፍሪካ የደም አፍሳሽ መንፈሶች ለሚፈልጉት መስዋእት የሚቀርብ አልነበረም።
ለአገራቸውና ለህዝቦቻቸው ምንም የማያስቡ መሪዎች ወገን እየያዙ ሲፈልጉ በሶማሊያ ሲፈልጉ ደግሞ በሱዳን ሰራዊት እያሰማሩ የኢትዮጵያውያንን ሆነ የኤርትራውያንን ደም ይነግዱበታል። ይህ ድርጊታቸውም በተለይም የብዙ የህወሃት ጄነራሎችን ኪስ ያደለበ የንግድ መንገድ ሆኗል።
ዛሬ ኤርትራ በሁሉም መስክ ካለባት ችግር የተነሳ በአለም አገራት የተገለለች አገር ለመሆን በቅታለች፤ ህዝቦቿም በልዩ ልዩ መከራ ውስጥ ለመሆናቸው ዓለም የሚያውቀው ሃቅ ሆኗል።
ኢትዮጵያም ከኤርትራ በከፋ መልኩ የጥቂት አምባገነኖችና ዘረኞች መፈንጫ አገር ከመሆኗም በላይ በህዝቦቿ ላይ በሁሉም መስክ ያለው እንግልትና ስቃይን በአገሪቷ ውስጥ ያሉ እስር ቤቶች ይመሰክሩታል፤ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች መዛግብት ይናገራሉ፣ የአረብ አገራት እስር ቤቶችና በየቤቱ የሚሰቃዩት እህቶቻችን እንባና ጩኸት ይናገራል፣ በየሜዳው በጥይት የሚደበደቡት የወንድሞቻችንና የእህቶቻችን ደም አሁንም ለምስክርነት ይጮሃል፣ ይህንን የህወሃትን የግፍ አገዛዝ በመሸሽ በዓለም አገራት በስደትና በስቃይ ላይ ያለው ኢትዮጵያዊ ይመሰክራል፣ የሚበላውን ያጣውና የበይ ተመልካች የሆነው፤ በየቤቱ ተኮማትሮ የተቀመጠው ኢትዮጵያዊው ይመሰክራል ።
የምስራቅ አፍሪካ አገራት ችግሮች የሚመሯቸው መንግስታትና ቡድኖች ችግር እንደሆነና ይህንን ችግር ለመፍታትም ሆነ ከዚህ ችግር ለመውጣትም የህዝቡ ቁርጠኝነት ማነስና ይህንን ትግልም ለመምራት የተቃዋሚው ጎራ ቁርጥኝነት ማጣት ሌላው ችግር እንደሆነ ይነገራል፤ ይሁንና የአፍሪካ ቀንድ ህዝቦች ከመቼውም ጊዜ በላይ በመቀራረብና በመተሳሰብ እንዲሁም በመተማመን እነዚህን በህልውናቸው ላይ ትልቅ ፈተና እየደቀኑ በብዙሃኑ ላይ ግፍ የሚፈጽሙትን ለመታገል የጋራ ሸንጎ የሚመሰርቱበትና በጋራ የሚነሱበት ጊዜ ቢኖር አሁን ነው። እነዚህን በዓለም የሚታወቁትን የምስራቅ አፍሪካ አንባገነኖች እድሜ ለማሳጠርና የህዝቦቹን መከራ ለመቀነስ በጋራ መረባረብ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም።
የአውሮፓና የአሜሪካ አገራትም የምስራቅ አፍሪካ አገራት ህዝቦች በተረጋጋና ሰላማዊ ህይወት እንዲገፉ ለማድረግ ያስችል ዘንድ ህወሓትንና ሻዕቢያን በመርዳት በህዝቦች ላይ መከራንና ጠንቅን እንዳመጡብን ሁሉ እነዚህን ሃይሎች በመጣል ታሪካዊ ስህተቶችን እንዲያስተካክሉ ማድረግ የሚገባቸው ሰአት መሆኑን ማስረዳት ያለብን ጊዜ አሁን ነው።
የአንዱ የአፍሪካ ቀንድ አገር ሰላም መሆን የሌላውን አገር ሰላም ማረጋገጥ እስካልቻለ ድረስ ሁሉም የምስራቅ አፍሪካ አገራት ነፃ ይሆናሉ ብሎ መጠበቅ ስህተት ነው። አምላክም እነዚህን አገራት እንዲያስብ አገራቱን በጸሎትም ማሰብ ይጠበቅባቸዋል። ቸር ይግጠመን።
እግዚአብሔር ምስራቅ አፍሪካን ይባርክ!
aberashiferaw.wordpress.com

No comments:
Post a Comment