ሰሞነኛው የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ዘጠነኛ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባኤ የሀገሪቱ አበይት የፖለቲካ ሁነትነበር፡፡ ከውጪ ሀገራት የመጡ የ13 ፓርቲ ልዑካናት፣ ከልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍል የተወከሉና የፓርቲውአባላት በጥቅሉ 2000 ዕድምተኞች በተገኙበት የተካሄደው የአራት ቀኑ ጉባኤ ሀገሪቱን የሚመለከቱ በርካታውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡ አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ሊቀመንበር፣ አቶ ደመቀ መኮንን ደግሞ ምክትል ሆነውእንዲሰሩ ያስወሰነው ጉባኤ ባለ አስራ አንድ አንቀፅ የአቋም መግለጫ በማፅደቅ ብቻ የተደመደመ አልነበረም፡፡ጉባኤው ድርጅቱ የቀድሞ መሪውን እጅግ የዘከረበትና የእሳቸውን ስራ የተመለከተ የጉባኤ ሰነድ ያቀረበበትምጭምር ነበር፡፡ከዚህ የኢህአዴግ ጉባኤ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ የግንባሩ አባል ድርጅቶች ህወሀት፣ ብአዴን፣ ደኢህዴግእና ኦህዴድ የየራሳቸውን ድርጅታዊ ጉባኤ በየክልሎቻቸው ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ ድርጅቶቹ በዚህጉባኤዎቻቸው ላይም በርካታ የአመራር ሹም ሽሮች ማድረጋቸውና መነጋገሪያ ሆኖ መሰንበቱም አይዘነጋም፡፡እኒህን የጉባኤ ሳምንታት አስታከንም በጉባኤያቱ ላይ የተከሰቱ ነገሮችን በተመለከተ በተቃውሞ ጎራ ያሉየፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን አስተያየት ለማሰባሰብ ሞክረናል፡፡
Sunday, March 31, 2013
Saturday, March 30, 2013
የ”ጎሳ ፖለቲካ”
እንደሚታወቀው አገራችንን ሊጠብሳት እያዘጋጃት ያለው የ”ጎሳ ፖለቲካ” ደራሲውና ቀማሚ በሞት ቢለዩም የሚያበርደው አስተዋይ መሪ አልተገኘም፡፡ በማስተዋል ማርከሻውን ለሚቀምሙም በቂ ጆሮ አልተሰጣቸውም – ጩኸቱ እጅግ ያደነቁራልና። ከውጪም ከውስጥም የሚረጨው የጎሳና የ”ደም” መርዝ ሳያንስ አሁን ደግሞ በሃይማኖት ተንተርሶ የተጀመረው አለመግባባት አስደንጋጭ ይዘት እንዳለው አያጠያይቅም። ተወደደም ተጠላም ያስፈራል። ኢህአዴግ ባቀናበረው “የድርሰት” ፊልም መነሻ ሳይሆን በበርካታ መረጃዎች የተደገፈ ማሳያ ማቅረብ ይቻላል።
ሞት ለአምባገነን!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ከሰብኣዊ
Friday, March 29, 2013
ጉረኛው ጓደኛችን
ጓደኛችን
ልጆች በነበርንበት
ወቅት (12-17 ዓመት ዕድሜ)
ክልል ውስጥ የቀበና ልጆች
እንደመሆናችን የተለያዩ የስፖርት
አይነቶችን ለመጫወት አራት
ኪሎ በሚገኘው ወወክማ (ወጣቶች
ወንዶች ክርስቲያናዊ ማህበር) ዛሬ
መጠሪያው ተለውጦ የህፃናትና
ወጣቶች ማዕከል ሆኗል፡፡ በድሮ
ስሙ ልቀጥል ቢል ሙስሊሞችንና
ሌሎችንም የሃይማኖት ተከታዮችን
ቅር ማሰኘቱ አይቀርምና
መጠሪያውን መቀየሩ በበጎ ጎን
ማየት ይቻላል፡፡
ልጆች በነበርንበት
ወቅት (12-17 ዓመት ዕድሜ)
ክልል ውስጥ የቀበና ልጆች
እንደመሆናችን የተለያዩ የስፖርት
አይነቶችን ለመጫወት አራት
ኪሎ በሚገኘው ወወክማ (ወጣቶች
ወንዶች ክርስቲያናዊ ማህበር) ዛሬ
መጠሪያው ተለውጦ የህፃናትና
ወጣቶች ማዕከል ሆኗል፡፡ በድሮ
ስሙ ልቀጥል ቢል ሙስሊሞችንና
ሌሎችንም የሃይማኖት ተከታዮችን
ቅር ማሰኘቱ አይቀርምና
መጠሪያውን መቀየሩ በበጎ ጎን
ማየት ይቻላል፡፡
ለሥራ ታላቅ አክብሮት የነበራቸው ንጉሥ !!
ነበራቸው፡፡ ንጉሳዊ ዘውድ ከማንም በላይ ነው የሚለውን አባባል አይቀበሉም፡፡ እንዲያውም ከማንኛውም ዘውድ በላይ የሆነው ገበሬ ነው የሚል ፅኑ ዕምነት እንደነበራቸው ታሪክ ይመሰክራል፡፡ አልፎ ተርፎም ሰውን በሚሠራው ሥራ የሚሳደብ ሰው እኔን እንደሰደበ ይቆጠራል ብለው አስጠንቅቀው ነበር፡፡ የሚሠራ ሰው የሚወዱና የሚያከብሩ ብቻ ሳይሆኑ ራሳቸውም ሥራ ወዳድ ነበሩ፡፡
ከዛሬ 104 ዓመታት በፊት የሚከተለው ማሳሰቢያ በጽሐፍ አስተላልፈው ነበር፡፡
‹‹... ከዚህ ቀደም ብረት ቢሠራ ጠይብ፣ ሸማ ቢሠራ ሸማኔ፣ ቢጽፍ ጠንቋይ፣ ቤተክርስቲያን ቢያገለግል ደብተራ እያላችሁ፤ አርሶ ነጩን ከጥቁር አምርቶ የሚያገባውን አራሽ ከዘውድ ይበልጣል የሚባለውን ገበሬ እያላችሁ፣ ነጋዴን ነግዶ ወርቁን ግምጃውን ይዞ ቢገባ አንተ ነጋዴ ገጣባ አጣቢ እያላችሁ በየሥራው ሁሉ ትሰድባላችሁ... ከእንግዲህ ግን እንዲህ ብሎ የተሳደበ እኔን የሰደበ ነው እንጂ ሌላውን መስደብ አይደለም፡፡ ዳግመኛ ግን ሲሳደብ የተገኘ ሰው መቀጫውን አንዳንድ ዓመት ይታሠራል፡፡ ሹማምንትም አስረህ ዓመት ለማስቀመጥ የሚቸግርህ የሆነ እንደሆነ አስረህ ወዲህ ስደድልኝ››
ከዛሬ 104 ዓመታት በፊት የሚከተለው ማሳሰቢያ በጽሐፍ አስተላልፈው ነበር፡፡
‹‹... ከዚህ ቀደም ብረት ቢሠራ ጠይብ፣ ሸማ ቢሠራ ሸማኔ፣ ቢጽፍ ጠንቋይ፣ ቤተክርስቲያን ቢያገለግል ደብተራ እያላችሁ፤ አርሶ ነጩን ከጥቁር አምርቶ የሚያገባውን አራሽ ከዘውድ ይበልጣል የሚባለውን ገበሬ እያላችሁ፣ ነጋዴን ነግዶ ወርቁን ግምጃውን ይዞ ቢገባ አንተ ነጋዴ ገጣባ አጣቢ እያላችሁ በየሥራው ሁሉ ትሰድባላችሁ... ከእንግዲህ ግን እንዲህ ብሎ የተሳደበ እኔን የሰደበ ነው እንጂ ሌላውን መስደብ አይደለም፡፡ ዳግመኛ ግን ሲሳደብ የተገኘ ሰው መቀጫውን አንዳንድ ዓመት ይታሠራል፡፡ ሹማምንትም አስረህ ዓመት ለማስቀመጥ የሚቸግርህ የሆነ እንደሆነ አስረህ ወዲህ ስደድልኝ››
የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር የተሰኘ የፖለቲካ ፓርቲ በሌንጮ ለታ መሪነት ተመሰረተ።
ካለፈው
ሳምንት ጀምሮ በኦሮሞ የውይይት መድረክ አዘጋጅነት በሚኒሶታ ሲካሄድ የነበረውን ተከታታይ ውይይት ተከትሎ በአቶ ሌንጮ ለታ መሪነት እና በ አቶ ዲማ ነገዎ ሰርቦ ተከታይ ምክትልነት የሚመራ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር የተሰኘ የብሄር ድርጅት መመስረቱ ይፋ ተደርጓል::
አብዛኛዎችን የቀድሞ የኦነግ አመራሮችን እና አባላትን ያቀፈው ይህ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ የድርጅቱን ደንብ በማጽደቅ በይፋ ስራ ጀምሯል:; የድርጅቱን ደንብ ይመልከቱት ::
DECLARATION OF THE OROMO DEMOCRATIC FRONT (ODF)
አብዛኛዎችን የቀድሞ የኦነግ አመራሮችን እና አባላትን ያቀፈው ይህ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ የድርጅቱን ደንብ በማጽደቅ በይፋ ስራ ጀምሯል:; የድርጅቱን ደንብ ይመልከቱት ::
DECLARATION OF THE OROMO DEMOCRATIC FRONT (ODF)
We, members of the Founding Congress of the Oromo Democratic
Front (ODF), announce the launching of a new Oromo political movement that
advocates justice for the Oromo and all other nations in Ethiopia. The founding
of ODF ushers in a new phase in the Oromo nationalist struggle with the
objective of working for the transformation of the Ethiopian state into a truly
democratic multinational federation equitably owned by all the nations.
We are launching this new movement cognizant of the fact that Ethiopia has been, and remains, the prison of nations and nationalities, with the Oromo being one of the prisoners. Today in Ethiopia, domination, repression, discrimination, eviction, denial of religious freedom, humiliation and exploitation of the Oromo and other nations and nationalities have attained new heights. And this needs to come to an end. It is to contribute to this end that we are launching a movement that advocates freedom and justice for all individuals and nations.
We are launching this new movement cognizant of the fact that Ethiopia has been, and remains, the prison of nations and nationalities, with the Oromo being one of the prisoners. Today in Ethiopia, domination, repression, discrimination, eviction, denial of religious freedom, humiliation and exploitation of the Oromo and other nations and nationalities have attained new heights. And this needs to come to an end. It is to contribute to this end that we are launching a movement that advocates freedom and justice for all individuals and nations.
Tuesday, March 26, 2013
ዕውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው?
የኢትዮጵያ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽ ኮሚቴና ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር በመሆን ያዘጋጁት ሰላማዊ ሰልፍ አላማ ለፋሺስቱና ለጦር ወንጀለኛው ግራዚያኒ በጣሊያን ሀገር የተገነባውን መናፈሻ ስፍራና ሀውልት ለመቃወም ነው፡፡ ይህ ግለሰብ ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ታሪክ አይዘነጋውም፡፡
ግራዚያኒ በመርዝ ጋዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ጨፍጭፏል፤ከየካቲት 12 ጀምሮ ለቀናት በዘለቀው የበቀል ጭፍጨፋም በአካፋ ሳይቀር በአዲስ አበባና በአካባቢዋ ያሉ ኢትዮጵያውያንን በግፍ ጨፍጭፏል፡፡ ግራዚያኒ በወቅቱ በሰጠው ትዕዛዝ የፋሺስት ወታደሮች ህይወት ያለውን ተንቀሳቃሽ ፍጥረትን ሁሉ ገድለዋል፡፡ ይህ እሩቅ በማይባል ጊዜ የተፈፀመ ድርጊት ነው፡፡የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለእንዲህ አይነቱ ጨፍጫፊ የተገነባን ሀውልት ለመቃወም በወጡ ዜጎች ላይ የወሰዱት የእስር ተግባር እውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው? አስብሎናል፡፡ኢህአዴግ በስልጣን ዘመኑ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ በተደጋጋሚ ጥፋት ፈፅሟል፡፡
Monday, March 25, 2013
ሰብኣዊነት ይቅደም!!!
ትግርኛ ተናጋሪ በመሆናችን ብቻ የህወሃትን አቀንቃኝ መሆን የለብንም፣ እንደ ጥሩንባ
ነፊ ፕሮፓጋንዳ ነፊ መሆን የለብንም! ትግርኛ ተናጋሪ መሪዎች ስላሉበት የህውሃት ደጋፊ መሆን የለብንም! ከነችግራቸው፣ከነበደላቸው፣ከነሐጢያታቸው መደገፍ ያለብን አይመስለኝም።ቆም ብለን እናስብ እንጂ እንደ ሰው! ያለበለዚያ ነገ ደግሞ ዋጋ
እንደሚያስከፍል ማወቅ ተገቢ ነው። አንድ ሰው ዘመድህ ወይም ያ ሰው ድርጅቱ መሪ፣ አባል፣ ደጋፊ ያንተ ሰው ከሆነ በሰው ልጅ ላይ መጥፎ ነገር እንዳይፈፅም መምከር ሲገባ በስጋ ወይም በዘር ስለተቆራኘን ብሎ መደገፍ፣ ማበረታታት ነገ ከወንጀል
አድራጊው የተለየ ስራ አለመስራታችን ማወቅ ተገቢ ነው።በደል ፈፃሚው ድርጊቱን ካላስተካከለ ተግባሩን በመቃወም ማሳየት።
የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች በርሃብ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ ነው
ከመጋቢት 2 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርት ማቆም አድማ ላይ የነበሩት የኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ስላሴ መንፈሰሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት በርሃብ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ እንደሆነ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለፁ፡፡
የትምህርት ጥራት መጓደል፣ የአስተዳደራዊ ችግሮችና በምግብ ጥራት መጓደል ምክንያት ጥያቄያቸውን ለኮሌጁ አስተዳደር ቢያቀርቡም ምላሽ በማጣታቸው የትምህርት መቆም አድማ ለማድረግ የተገደዱት ቅድስት ስላሴ መንፈሰሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት በርሀብ ተጎድተው ራሳቸውን በመሳት በመጀመራቸው በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል መወሰድ መጀመራቸውን ስምቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ተማሪዎች ተናግረዋል፡፡
Sunday, March 24, 2013
‹‹...እናትና አባትን የሚለያይ ፖለቲካ...›› ግራ የገባ ነገር ነው!
እትብታችን በተቀበረችበት በአገራችን ሁለተኛ ዜጋ፣ ተሰደን ባለንበት አገር ሁለተኛ ዜጋ ! ተሰደን በምንኖርበት አገር እንኳን
የፖለቲካው ሁናቴ የወያኔን የቤት ስራ መቅረፍ ሲገባን እንደውም ያባስነው ይመስለኛል። የኢህአዴግ/ ወያኔ በብሄር፣ በጎሣ፣ በዘረኝነት
የከፋፈላትን አገር መታደግ ሲገባን ዛሬ ደግሞ ተሰደን እራስ በራሳችን ተከፋፍለን በብሄር የፖለቲካ ድርጅት አቋቁመን እራስ በራሳችን
መሻኮትና ለብሄራችን፣ለዘራችን ነፃነት እንታገላለን ስንል የወያኔ ስራ ከማስፈፀም ምን ይለያል? ሁሉም የፖለቲካ ድርጅት አምባገነኑን
ስርዓት ጥለን የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን ባለቤት እናደርጋለን ብለን ካልን ምንድነው ችግራችን? አንድ የማንሆንበት! በእንደዚህ
አይነት አካሄዳችን የመቶ አመት ትግል እንዳያስፈልገን! በብሄር የታመነ ፖለቲካ የትም አያደርስም መጨረሻው ዋጋ ያስከፍላል ኢትዮጵያዊነትን
ያልጠበቀ ትግል ነው ምፃሜውም ያላማረ ነው።በብሄር ብቻ የተደራጀ ፖለቲካ እናትና አባትን የሚለያይ ፖለቲካ ውጤት ነው። ማንም ሲወለድ
ከዚኛው ብሄር ልወለድ ብሎ አልተወለደምና ብሄራችን ውበታችን ነው የመበላለጫ መለኪያ አይደለም! ደማችን ኢትዮጵያዊነት ነው። ለእኔ ከዘር ቆጠራ እና ከብሔር ነፃ የሆነው የማንነት መገለጫ ኢትዩጵያዊነት ብቻ ነው፡፡
ስዩም መስፍን፣ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ እና አርከበ ዕቁባይ ከሕወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴአባልነት ተሰናበቱ፡፡
የኢህአዴግ አራቱ አባልድርጅቶች በሳምንቱ ውስጥ ባካሄዷቸው ጉባኤዎች የየድርጅቶቹን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትና የኢህአዴግ የስራ አስፈፃሚዎችን መርጠዋል፡፡ እንዲሁም ዛሬ መጋቢት 14ቀን 2005 ዓ.ም በባህርዳር በሚከናወነውየኢህአዴግ ም/ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይየሚሳተፉ አባላቶቻቸውን እንደመረጡ ለመረዳት ተችሏል፡፡በዚህ መሰረት ሕወሐት በፊት የድርጅቱ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አባይወልዱ በሊቀመንበርነት እንዲቀጥሉሲወስን፣ በምክትል ሊቀመንበርነት ደግሞዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን መርጧል፡፡ በጉባኤው ለዓመታት ያህል በፓርቲውበማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ሲያገለግሉከቆዩ ነባር አባላት ውስጥ አምባሳደስዩም መስፍንን፣ አምባሳደር ብርሃነ ገ/ክርስቶስን፣ አቶ አርከብ እቁባይን እናአቶ ዘርአይ አስገዶምን ጨምሮ ዘጠኙባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ከማዕከላዊኮሚቴ አባልነታቸው ተሰናብተዋል።
Saturday, March 23, 2013
ኢህአዴግ ከ700 በላይ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ሰብስቦ ቅስቀሳ አደረገ
ትናንት ሀሙስ መጋቢት 12 ቀን 2005 ዓም የኢህአዴግ መንግስት ከ740 በላይ የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎችን ስድስት ኪሎ በሚገኘው ስብሰባ ማእከል ለአንድ ሙሉ ቀን በመሰብሰብ በመጪው የአዲስ አበባና አካባቢ ምርጫ ኢህአዴግን እንዲመርጡ ቀስቅሷል። ለእያንዳንዱ ተሳታፊ 100 ብር ከመስጠት በተጨማሪ የምሳ፣ የቡና እና የሻይ ግብዣም አድርጓል።የጎዳና ተዳዳሪዎች ትናንት 2፡30 ላይ ነጭ ቲሸርት ለብሰው እና የኢህአዴግ አርማ ያለበት የወረቅት ኮፍያ አድርገው ወደ ስብሰባው አዳራሽ የገቡ ሲሆን፣ በስብሰባው ላይ ኢህአዴግ ለጎዳና ተዳዳሪዎች ካለፉት መንግስታት በተሻለ እንደሚያስብላቸው፣ የሙያ ስልጠና ሲሰጣቸው መቆየቱን እና በዚህም እንቅስቃሴ ለቁም ነገር የበቁ የጎዳና ተዳዳሪዎች መኖራቸውን ገልጿል።
ኢህአዴግ 9ኛ ጉባኤውን በባህርዳር ጀመረ
መጋቢት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ (2005) ዓ/ም
”በመለስ አስተምህሮዎች ጠንካራ ድርጅትና የልማት ሀይሎች ንቅናቄ ለህዳሴያችን በሚል” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ጉባኤ ዋና አላማ ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በሁዋላ እየተዳከመና በውስጥ ሽኩቻ እየታመሰ የመጣውን ኢህአዴግን መልሶ ማጠንከር ነው።ግንባሩ በስልጣን ሽኩቻ የሚታመሱት አባላቱ ድርጅቱ የመጣበትን ጉዞ መለስ ብለው እንዲያስታወሱ የሚያደርግ ተውኔት አዘጋጅቶ አሳይቷል። ኢህአዴግ ደርግን ለመጣል ያሰላፈውን ታሪክ፣ የብሄር ብሄረሰቦችን እኩልነት ለማስከበር የከፈለውን መስዋትነትና አባይ ለመገደብ የጀመረው ጥረት የሚያሳየው ተውኔት በቀጥታ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንዲሰራጭ ተደርጓል።
ኧረ የፍትህ ያለህ !! ያለ ነፃነት መኖር በቃን! በቃን መኖር ሰለቸን ! ለውጥ ያስፈልጋል!
በዛሬይቱ ኢትዮጵያ የህግ የበላይነት እንዲከበር፣ግልፅነትና
ተጠያቂነት እንዲኖር እና በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ውስጥ ዜጎች በእኩልነት ሰብዓዊ መብታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ የሚያስቡ፣
የሚናገሩ፣የሚፅፉና የሚቆረቆሩ በጠቅላላው ለእነዚህ ፅንስ ሐሳቦች ዘብ የሚቆሙ በሙሉ የስርዓቱ ጠላቶች ተደርገው በመቆጠር ላይ
ናቸው::
ለአገሪቱ አንድነትና ሉአላዊነት ብልፅግና በጣም ከሚቆጠሩ መሪዎቿና የፓርቲአቸው ጠባብ ጎሰኛ ፖሊሲ የተለየ የሚያስቡ
ዜጎችና ቡድኖች ሁሉ ጠላትና ሽብርተኞች ወይንም አሽባሪዎች ወይም በዘመኑ አባባል ጽንፈኛ ተደርገው ይቆጠራሉ።
“የህዳሴው ግድብ” ከግማሽ በላይ የኢትዮጵያ አይደለም ትልቁን ድርሻ ኤፈርት ይዟል
“በራሳችን መሐንዲስ፣ በራሳችን ገንዘብ፣ በራሳችን የተባበረ ክንድ እንገነባዋለን” በማለት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመስቀል አደባባይ ታላቅ ህዝባዊ ድጋፍና “መዓበላዊ መነቃቃት” ፈጠሩበት የተባለለት የ”ህዳሴው” ግድብ 51 በመቶ ድርሻ የኢትዮጵያ እንዳልሆነ ነዋሪነታቸው በአውሮፓ የሆነ ዲፕሎማት በተለይ ለጎልጉል ገለጹ።ስማቸው ምስጢር እንዲሆን የጠየቁት ዲፕሎማት እንዳሉት 51 በመቶ ባለድርሻ የሆነችው አገር አውሮፓ የምትገኝ የኢትዮጵያ አጋር አገር ናት። ለጊዜው የባለድርሻዋን አገር ስም መግለጽና የውሉን ዝርዝር ይፋ ማድረግ ያልፈለጉት ዲፕሎማት ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ የፈለገችውን ውሳኔ በራስዋ ለማስተላለፍ እንደማትችል፤ ያላት ድርሻ 49 በመቶ ብቻ በመሆኑ ድምጽን በድምጽ በሚሽረው በአብላጫ ድምጽ ህግ መሰረት በግድቡ ላይ የሚወሰነው ውሳኔ 51 በመቶ ባለድርሻ በሆነችው አውሮፓዊቷ አገር መሆኑን አብራርተዋል።49 በመቶ ተብሎ የተገለጸው የድርሻ መጠን ጅቡቲን ጨምሮ የተለያዩ አገሮች የተቀራመቱት መሆኑን ያመለከቱት የመረጃው ባለቤት፣ አገር ውስጥ ካሉት የንግድ ተቋማት መካከል ኤፈርት ትልቁን ድርሻ መውሰዱን እንደሚያውቁ ተናግረዋል።የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የግል ባለሃብቶች፣ ማህበራት፣ ባንኮችና የተለያዩ ግለሰቦች በትዕዛዝ አክሲዮን መግዛታቸውን ያስታወሱት እኚሁ ዲፕሎማት “በግድቡ ዙሪያ ከሚፈራው የጸጥታ ችግር በላይ አስጊው ጉዳይ የባለድርሻዎች ምስጢር መሆን ነው” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።መንግስት ለግንባታው የሚሆን ከፍተኛ ገንዘብ ከአውሮፓዊቷ አገር ማግኘቱን ያመለከቱት የጎልጉል ምንጭ፣ “ከአገር ውስጥ በአክሲዮን ስም የሚሰበሰበው ገንዘብ ለአገር ውስጥ በጀት ማሟያና ለመንግስት የስራ ማከናወኛ የሚውል ነው” ብለዋል።
Friday, March 22, 2013
ዶ/ር ያዕቆብን ጨምሮ 38 ሰዎች ታስረው ተፈቱ
ለፋሽስቱ ጄነራል ሩዶልፍ ግራዚያኒ መታሰቢያ እንዲሆን በጣሊያን ሀገር መናፈሻና ሙዚየም መሰራቱን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው የነበሩት ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያምን ጨምሮ ሌሎች 38 ሰዎች ያልተፈቀደ ሰልፍ አድርገዋል በማለት ለሁለት ቀናት ከታሰሩ በኋላ ባለፈው ሰኞ በዋስ ተፈቱ።
ባለፈው እሁድ መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓ.ም ስድስት ኪሎ የካቲት 12 መታሰቢያ ሐውልት ዙርያ በመነሳት ወደጣሊያን ኤምባሲ ሊደረግ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ በፖሊስ እና በደህንነት ኃይሎች እንዲበተን ከተደረገ በኋላ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነትና ሌሎች ሰልፉን ሲያስተባብሩ የነበሩ ወጣቶች በመኪና ተጭነው ወደ አራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ተወስደዋል። በፖሊስ ጣቢያው ቃላቸውን ከሰጡ በኋላ አንድ ቀን እንዲያድሩ ከተደረገ በኋላ በመታወቂያ ዋስ ተፈተዋል።
ከታሰሩት አንዱ የሆኑት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ስለሁኔታው ሲናገሩ ‘‘ጠዋት በግምት ሦስት ሰዓት አካባቢ ሰልፉ ከሚጀመርበት የካቲት 12 ደረስን። ወጣቶች ቲሸርት ለብሰው ተሰላፊዎችን ያስተናግዱ ነበር። በግምት አንድ መቶ የምንሆን ሰዎች በተገኝንበት ሁኔታ አንድ ሲቪል የለበሰ ሰው ‘‘እዚህ ጋ መሰብሰብ አትችሉም’’ ሲለን ሕገ-መንግስታዊ መብታችን ነው። ሰልፉን ለማካሄድ ለሚመለከተው አካል አሳውቀናል ብለን ተጨማሪ ሰልፈኞችን መጠባበቃችንን ቀጠልን። በኋላም መኪና ይዘው በመምጣት እኔን ጨምሮ ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያምና ሌሎች የሰልፉ አስተባባሪዎችን ወደ መኪና ካስገቡን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ሰልፉ ወደ እስር ተለወጠ’’ ሲሉ ተናግረዋል።
ከጠቅላይ ፍ/ቤት እስከ ሚንስትሮች ም/ቤት
መጋቢት 18/2005 ዓ.ም የእነ እስክንድር ነጋ ይግባኝ ለመጨረሻ ጊዜ ተብሎ ተቀጥሯል፡፡ በዚህ መዝገብ የተከሰሱት የህሊና እስረኞች ይግባኝ ከጠየቁ አምስት ወር አልፏቸዋል፡፡
ለምን? …በአዲስ መስመር እንነጋገርበት፡፡
የይግባኙን ውሳኔ ያዘገየው የፖለቲካ ተንታኝ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የተከሰሰው በሀሰት ስለሆነ ነው፡፡ በእርግጥ ይህንን ያልኩት እኔ አይደለሁም፤ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የመሀል ዳኛ የሆነው አቶ አማረ አሞኘ ነው፡፡ ባለፈው ወር ዳኛው አቃቢ ህጎቹን ሰበሰበና እንዲህ አላቸው፡-
‹‹ይህን ሰው አሻባሪ ነው ብላችሁ ስትከሱት ያቀረባችሁት ማሰረጃ በተለያየ ጊዜ የፃፈውን ፅሆፎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና በአንድ የፖለቲካ ፓርቲ መድርክ ላይ ተናገረው ያላችሁትን ብቻ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ፅሁፉና ንግግሩ ያስከተለው አደጋ አልተገለፀም፤ ወይም ምንም አይነት አደጋ አላስከተለም ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ተከሳሹ ላይ ቅጣት ለመጣል አያስችልም፡፡ ስለዚህም ሌላ ጥፋተኝነቱን የሚያረጋግጥ ማሰራጃ ካላችሁ አቅርቡ? አሊያም በሚቀጥለው ቀጠሮ ሲቀርብ በነፃ እለቀዋለሁ፡፡››
አቃቢ ህጎቹ ምንም ማስረጃ አልነበራቸውምና በደፈናው ‹‹ሰውየው አሸባሪ ስለሆነ ዝም ብለህ፤ ይግባኙን ውድቅ አድርግና የከፍተኛው ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አፅናበት›› የሚል ይዘት ያለው ተመሳሳይ አቋም አንፀባረቁ፡፡ ዳኛው ምን አይነት መንፈሳዊ ኃይል ተጭኖበት እንደ ሆነ እንጃ! ‹‹በፍፁም ከህግ ውጪ አልሰራም፤ ህሊና አለኝ›› ብሎ ፍንክች ያባ ቢለዋ ልጅ ይላል፡፡
ይህን ጊዜም ነገሩ ቦግ ያደረገው አንድ አቃቢ ህግ
‹‹አንተ እስክንድርን እለቃለሁ የምትለው ያገርህ ልጅ ጎንደሬ ስለሆነ ነው!››
ይለዋል ቁጣ በተቀላቀለበት ድምፅ፡፡ ዳኛ አማረም ይበልጥ ተናዶ
‹‹እኔ እሰከ ዛሬ ድረስ ያገለገልኩት ሀገሬን ኢትዮጵያ እንጂ የትውልድ መንደሬን አይደለለም፡፡ ደግሞም ዘረኝነት የለብኝም›› ሲል መለሰለት፡፡
ለምን? …በአዲስ መስመር እንነጋገርበት፡፡
የይግባኙን ውሳኔ ያዘገየው የፖለቲካ ተንታኝ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የተከሰሰው በሀሰት ስለሆነ ነው፡፡ በእርግጥ ይህንን ያልኩት እኔ አይደለሁም፤ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የመሀል ዳኛ የሆነው አቶ አማረ አሞኘ ነው፡፡ ባለፈው ወር ዳኛው አቃቢ ህጎቹን ሰበሰበና እንዲህ አላቸው፡-
‹‹ይህን ሰው አሻባሪ ነው ብላችሁ ስትከሱት ያቀረባችሁት ማሰረጃ በተለያየ ጊዜ የፃፈውን ፅሆፎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና በአንድ የፖለቲካ ፓርቲ መድርክ ላይ ተናገረው ያላችሁትን ብቻ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ፅሁፉና ንግግሩ ያስከተለው አደጋ አልተገለፀም፤ ወይም ምንም አይነት አደጋ አላስከተለም ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ተከሳሹ ላይ ቅጣት ለመጣል አያስችልም፡፡ ስለዚህም ሌላ ጥፋተኝነቱን የሚያረጋግጥ ማሰራጃ ካላችሁ አቅርቡ? አሊያም በሚቀጥለው ቀጠሮ ሲቀርብ በነፃ እለቀዋለሁ፡፡››
አቃቢ ህጎቹ ምንም ማስረጃ አልነበራቸውምና በደፈናው ‹‹ሰውየው አሸባሪ ስለሆነ ዝም ብለህ፤ ይግባኙን ውድቅ አድርግና የከፍተኛው ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አፅናበት›› የሚል ይዘት ያለው ተመሳሳይ አቋም አንፀባረቁ፡፡ ዳኛው ምን አይነት መንፈሳዊ ኃይል ተጭኖበት እንደ ሆነ እንጃ! ‹‹በፍፁም ከህግ ውጪ አልሰራም፤ ህሊና አለኝ›› ብሎ ፍንክች ያባ ቢለዋ ልጅ ይላል፡፡
ይህን ጊዜም ነገሩ ቦግ ያደረገው አንድ አቃቢ ህግ
‹‹አንተ እስክንድርን እለቃለሁ የምትለው ያገርህ ልጅ ጎንደሬ ስለሆነ ነው!››
ይለዋል ቁጣ በተቀላቀለበት ድምፅ፡፡ ዳኛ አማረም ይበልጥ ተናዶ
‹‹እኔ እሰከ ዛሬ ድረስ ያገለገልኩት ሀገሬን ኢትዮጵያ እንጂ የትውልድ መንደሬን አይደለለም፡፡ ደግሞም ዘረኝነት የለብኝም›› ሲል መለሰለት፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)