Friday, October 4, 2013

ወያኔ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ በማጓጓዝ ስራ መጠመዱ ተሰማ

33
ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የሚወስዱ አዉራ መንገዶች ታንኮችን፤ መድፎችንና ሌሎችም ከባድ የጦር መሳሪያዎችን በተሸከሙ ከባድ ወታደራዊ የጭነት ማመላለሻ ከሚዮኖች እየተጨናነቁ መሆኑን ኢሳት ቴሌቪዥንና ሬድዮ የአይን እማኞችን ጠቅሶ ዘገበ። ወያኔ ከኤርትራ ጋር ባለበት የድንበር አተካሮ ብዙም ዉጥረት በማይታይታይበት በአሁኑ ወቅት የጦር መሳሪያዎቹን በዚህ ደረጃ ለማንቀሳቀስ ለምን እንዳስፈለገ ብዙም የሚታወቅ ነገር ባይኖርም አንዳንዶች ወይኔ ሀይሉን ለማሳየት የሚያደርገዉ ከንቱ የእዩኝ እዩኝ ዘመቻ ነዉ ሲሉ ሌሎች ደግሞ በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢ ከቀን ወደ ቀን እያየለ የሚጣዉን የአማጽያን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ነዉ ይላሉ። ያም ሆነ ይህ ወታደራዊ እንቅስቃሴዉን አስመልክቶ ከአገዛዙ ባለስልጣናት የተሰጠ መግለጫ ካለመኖሩም በላይ ሦስተኛ አካላት ጉዳዩን ለማጣራት ከመንግስት ጋር ያደረጉት ግንኙነትም ፍሬ አልባ ሆኗል።

ሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ፤ ጎንደርና አፋር ዉስጥ የወያኔን ስርዐት በኃይል ለመናድ የሚንቀሳቀሱ አያሌ መሳሪያ ያነገቡ ድርጅቶች የሚገኙ ሲሆን እነዚህ ላለፉት ሃያ አመታት በተናጠል ወያኔን የተዋጉ ኃይሎች ከቅርብ ግዜ ወዲህ የጋራ ግንባር እየፈጠሩ መምጣታቸዉ ወያኔን እንዳሳሰበዉና ክፉኛ እንዳስደነገጠዉም ታዉቋል። እንደብዙ የፖለቲካ ተንታኞች ግምት ይህ ከሰሞኑ የታየዉ ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴም የዚሁ ድንጋጤ ዉጤት ነዉ የሚሉ ብዙዎች ናቸዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ አዲስ አበባን ጨምሮ በየክልሉ የነጻነት ኃይሎችን ለመቀላለቀል የሚደረገዉ እንቅስቃሴ እያደገ መምጣቱ ሌላዉ የወያኔ ስጋት ስለሆነ የሰሞኑ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የሚደረገዉ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከመሀል የአገሪቱ ክፍሎች ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የድንበር አካባቢዎች የሚወስዱ መንገዶችንና ኬላዎችን ለመዝጋት ነዉ የሚሉም አልታጡም። በዚህ ተኬደ በዚያ የሰሞኑ የወያኔ ወታደራዊ ሩጫ አላማዉ ባዕዳንን ለመከላከል ሳይሆን ለአገር አንድነትና ለህዝብ መብትና ነጻነት የሚታገሉ ኃይሎችን ለማፈን ነዉ።

No comments:

Post a Comment