Thursday, October 3, 2013

ለዲ/ን ዳንኤል ክብረት “ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ሆኖ የገደለው ሰው የለም’ መጣጥፍ መልስ

ውድ አንባቢዎች ሆይ፤
ይህ የዲያቆን ዳንኤል ቃለ ምልልስ፣ ላይ ላዩን ሲያዩት እውነት በሚመስሉ የታሪክ ማስረጃዎች የተዋዛ፣ ነገር ግን ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ለመረመረው ግን ምንም የታሪካዊም ሆነ የርዕዮተ-ብይን ተጨባጭነት በሌላቸው ክስተቶች የታጨቀ፣ በአንድ ያልተማረ ነገር ግን ብልጣብልጥ አስመስሎ-አደር፣ በነገረኝነት የተባ ቆልማሚ ሰው የተሰጠ መግለጫ ነው፡፡
እንግዲህ ጉዳዩ ከወዲህ ነው፡፡ እንደ ዲ/ን ዳንኤል ያለ እውቀተ-ቁንፅል የሆነ ሰው ካልሆነ በስተቀር፣ የአሸባሪነትን ፅንሰ-ሀሳባዊ ርዕዮተ-ብይንን ታቅፎ ከክርስትናም ሆነ ከእስልምና ውጪ ልኬተ- ስምም ፍለጋ የሚዋትት ይኖራል ተብሎ አይታመንም፡፡ በእርግጥ መለስ ዜናዊ እና ግብራባሮቹ እንዲያ እድረገዋል፤ ነገር ግን እነርሱም ቢሆኑ በድድብናና በአስክሮተ-ስልጣን ታብየው ነው፡፡
አሁን ባለንበት ዘመን የአሸባሪነት ፅንሰ-ሀሳብ በአያሌው ከእስልምና ሐይማኖት ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ በእርግጥ ዲ/ን ዳንኤል ሳያቅ በድፍረት እንዳብራራው፣ አሸባሪነት እና አክራሪነት የሚመሳሰሉት እና የሚለያዩት ለተግባራዊነት ባላቸው ቀረቤታ ብቻ አይደልም፡፡ እንዲህ ብሎ መከራከሪያ ለማቅረብ፣ መጀመሪያ የአሸበሪነት ጠባያትን አንድ ሁለት ብሎ ጠቅሶ መትንተን እና የነኛን ጠባያት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን አስተምህሮት እነዲሁም ታሪክ ጋር ያላቸውን ፅንሰ-ሀሳባዊም ተራክቦ ነቅሶ መተንተን ያሻል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የአክራሪነትም ሆነ የአሸባሪነት ፅንሰ-ሀሳብ ከሐይማኖት ዘለል ባሉ ሌሎች መሀበራዊ መስተጋብራዊ-ኩነቶች ማለትም ነገደ-ዘውገኝነት እና የወንዜኛ-ጎጠኝነት ጋር ያላቸው ተወራራሽነት እና መለዮ ጠርቶ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡ ዲ/ን ዳንኤል ታዲያ እነኝህን ሁሉ አድበስብሶ ዲቃላ ሀሳቡን ያሳክራል፡፡ በእርግጥ በጅማ አከባቢ በክርስቲያኖች ላይ የተፈፀመውን አሳዛኝ ድረጊት ከእስልምና አሸባሪነት ጋር አያይዞ ከማቅረብ በፊት፣ ቀረብ ብሎ የነገደ-ዘውግ እና የወንዜኛ-ጎጠኝነት አክራሪነት በሂደቱ ውሰጥ የነበራቸውን ድረሻ መመርመር ያሻል፡፡ ሌሎች የእስልምና እምነት ተከታዮች በአብላጫነት ሰፍረው ከሚኖሩባቸው አከባቢዎች፤ ለምሳሌም ያክል በአፋር፣ በሱማሌ፣ በቤኒሻንጉል …ወ.ዘ.ተ፣ አከባቢዎች በተለይ በከፋ አከባቢ ብቻ ይህ ድረጊቱ ወይንም ይህ “እስልምና አሸባሪነት” ሊፈፀም ቻለ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ በእረግጥ ለዲ/ን ዳንኤል እና አጉራ ዘለል ጓደኞቹ ጭንቅላት ካልሆነ በስተቀር እንዲህ ቀላላል ሆኖ አይገኝም፡፡
ከዚያም በላይ ግን፣ በመሰረቱ በአሸባሪነት እና በአክራሪነት መሀከል ያለውን ልዩነት በተግባር ለመረዳት ያን ያህል ውስብስብ አይደልም፡፡ በእርግጥ ዲ/ን ዳንኤል ባላዋቂነት እንዳስቀመጠው በሚያስከትለው የሞት ውጤት የሚለካም አይደለም፡፡ ሞትን በማስከተሉ፣ አንድ ድርጊት አሸባሪነት ወይንም አንድ ሰው አሸባሪ ተብሎ በተግባር እንደ ማይፈረጅ የኖረዌያዊውን አንድሪው ብሬቪክን ድረጊት እና የስከተለውን ምላሽ በምሳሌነት መጥቀስ ይበቃል፡፡ በገዢው ፓርቲ የስደተኞች እና የንዑስ ማህበረሰባት አደላዳይ ድንጋጌያት አቂሞ የዛን ፓርቲ ተተኪ ምልምል ወጣቶች አመቺ ግዜና ቦታ ጠብቆ ከሶስት አመታት በፊት በጅምላ በገደለ ግዜ፤ አንድሪው ብሬቪክ የግራ-ዘመም ፖለቲካ አክራሪ ተባለ እንጂ ድረጊቱ አሸባሪነት ሰውዬውም አሸባሪ አልተባለም፡፡ በግልጥ ብናሰቀምጠው፤ ምዕራባዊ ሌላ ምዕራባዊን፣ እንድ ክርስቲያን ሌላ ክርስቲያንን ወይንም የእስልምና እምነት ተከታይን ሲገድል ተግባሩ አጥባቂነት/አክራሪነት ሰውዬው ደግሞ ስሙ አክራሪ ነው፡፡ አንድ የእስልምና ተከታይ ደግሞ ተመሳሳይ ድረጊት ፈፅሞ ሲገኝ ድረጊቱ አሸባሪነት አድራጊው ደግሞ ሽብርተኛ ይባላሉ፡፡ በመሆኑም አሸባሪነተ እና አክራሪነት በተግበሩ ፈፃሚው ማንነት በለያዩም በፅንሰ-ሀሳብ ደረጃ አንድ ናቸው ማለት ነው፡፡ በዚህ አኳሃን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቦታ እና ይዞታ መፈተሽ ይቻላል፡፡ ዲ/ን ዳንኤል ያመላከተው የታሪክ ማጣቀሻ የተዛባ ከመሆኑም በላይ እውነትነትም የጎደለው ነው፡፡ ለምሳሌ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ታሪክና አስተምህሮት አክራሪነት ቦታ እንዳልነበራቸውና አሁንም እንደሌላቸው ሲስረዳ ዲ/ን ዳንኤል እነዲህ ይላል፤
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ አክራሪነት ቦታ የለውም፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ይዘት፣ ከቀኖናው ስንነሣ ይህች ቤተ ክርስቲያን ለሌሎች ዕውቅና የመንፈግ ችግር አልነበረባትም፡፡ ዕውቅና ስትሰጥ ነው የኖረችው፡፡ … በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሁልጊዜ ግጭቶች ይፈጠሩ የነበሩት፣ ሌሎች ለእርሷ ዕውቅና መስጠት ሲያቅታቸው ነው፡፡ … በ17ኛው መ/ክ/ዘ በዐፄ ሱስንዮስ ጊዜ ካቶሊኮችና በኦርቶዶክሶች መሐል የተከሠተው ግጭት መንሥኤው አስቀድሜ የገለጸኹት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ ሮማ አልሄደችም፡፡ ሮም ናት እዚህ የመጣችው፡፡ እዚህ መምጣቷ ብቻ አልነበረም ችግሩ፣ ‹‹ከዛሬ ጀምሮ ከበሮው፣ ታቦቱም፣ የካህናቱ አልባሳትም ይውጣ! የዘመን አቆጣጠሩም እንደ ጎርጎሮሳውያን ይሁን! በዓላቱም ይቀየሩ! የዓመቱ መጀመሪያ መስከረም መኾኑ ቀርቶ ታኅሣስይሁን!›› በሚል በቀጥታ በቤተ ክርስቲያኒቱ ህልውና ውስጥ ገቡ፡፡ ይህን የመሰለው ግፊትና ዕውቅና የመንፈግ ኹኔታ ሲመጣ ወደ ጦርነት ደረጃ ታለፈ፡፡

በመሰረቱ ይህ ሸውራራ መልስ ነው፡፡ እርግጥ ነው፤ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ፖርችጋሎች ናቸው፡፡ የመጡት ግን በንግስት እሌኒ ጋባዥነት፣ በወቅቱ በግራኝ ጦር ለተፈታው የኦረቶዶክሱ መንግስት ድጋፍ ለመስጠት ነበር፡፡ ከጦረነቱ ፍፃሜ በኋላ ግን የተረፉት የፖርቹጋል ወታደሮች መሬትናሚስት አየተሰጣቸው በደንቢያ ሰፈሩ፡፡ ውለው አድረውም ሓየማኖታቸውን ማስተማርና ምዕመናቸው ማብዛ ያዙ፤ ካቶሊክ እና በኦርቶዶክስ መሀከል ያለው የቀኖና/ዶግማ ልዩነት ፈጦ ወጣ፡፡ ከአፄ ገላወዲዎስ ግዜ አንስቶ ልዩ ጉባኤዎች ተደርገው ልዩቱን ለመፍታት ተሞከረ፡፡ የኢትዮጵያ ኦረቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን የወቀቱ ምሁራን የቤተ-ክርስቲኗን ዘልማዳዊ ቀኖናዎች መለትም ግርዘትን፣ የአሳማ ስጋን መብል፣ ከአንድ በላይ ጋብቻን፣ ተስካርን፣ ፍትሀትን፣ ታቦትን… ወዘተ መፅሀፍ ጠቅሰው በጉባኤ ማስረዳት የማይሆንላቸው ሲሆን ሰውን ለጠብ ጋብዘው በአንድ ቀን ውጊያ አስከ ሰባተ ሺህ ገበሬ አስተራርደው አንድ ሳምነት ሙሉ ቸብቸቦ ቆጠሩ፡፡ ዲ/ን ዳንኤል እነዳለው አነኛ ገበሬዎች ሮመውያን አልነበሩም፡፡ ኢትዮጵያዊን ካቶሊኮች ነበሩ፡፡ ከሁሉ በላይ ግን፤ የኢትዮጵያ ኦረቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን፣ ከነገስታት ጋር እጅና ጓንት በመሆን፣ በፈላሻዎች እና በደቂቀ እሰጢፋኖሳዊን ላይ ለዘመናት እነደ ፈፀመችው፣ በዚህ ዘመን እነኳን ሲሰሙት ብርክ የሚሲዝ አሰጠያፊ አካላዊ ቅጣት እና የጅምላ ግድያ ድረጊት፣ የመሰለ ለቤተ-ክርስቲያኒቱ የአክራሪነት መነሻ እና መዳረሻነት ሌላ ምሳሌ መጥቀስ አያሻም፡፡ በእርግጥ ለቤተ-ክርስቲያናችን ቀናኢ መሆን የተገባን ነው፣ነገር ግን የፈጠጠን እውነትን መካድ ግን ስብዕናችንን ማዋረድ እና ልዕለ-ህሊናችንን ማራከስ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሚዞር ድምሩ ማህበረ-ልዕልና አልባነት ይሆናል፡፡ ዛሬ የነበሩንን ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ባህላዊ አሴቶች በፍጥነት እያጣን ያለነው ከዚህ የተነሳ ነው፡፡
Addugna Jaffero  …contact him by email  begashawdebela@hotmail.com

No comments:

Post a Comment