አዲስ አበባን ጡት ከተጣባሁአት ወይም ሸገር በጉዲፈቻ መልክ እንበለዉ ከጠቀለለችኝ ጀምሮ ማለት ይቻላል ብዙ ነገር እታዘባለሁ፣ እሰማለሁ፣ አያለሁ፣ … … እንደዉ ምን ልበላችሁ በቃ ቃላት አጣሁለት ብዬ ብዋሻችሁ ይሻላል (ከሰዉ ከመቀያየም)፤ ምናለፋችሁ በልማት ሰበብ ከሚገነቡት ቤቶች ይልቅ በሚፈርሱት፣ ከሚሰሩት ይልቅ እንደ ጭቃ ልጥፍ በሚቦኩት እና ያለ እቅድ ተሰርተዉ ያለ እቅድ በሚፈርሱት መንገዶች … … አሁንም በ ወዘተ ልሸዉዳችሁ መሰለኝ!
እናላችሁ በዲሞክራሲ ሰበብ ገብቶ በአንባገነንነት መስኮት በሚወጣዉ ፍትህ፣ ዱላ ቀረሽ ድንጋይ ዉርወራና ለክፉ በማይሰጥ አይን ሊያጠፋ በሚነሳ አስለቃሽ ጭስ ጫወታ፣ ወዘተ እስከ ህልፈተ ህይወት፣ አካል ጉዳተኛ፣ ካስተሳሰብ መኮላሸት ድረስ ከ ወዘተ መለስ…. ታዝቤ ቋቴ ሞልቶ ተርፎላችሁ ፈሰሰ፡፡
እናላችሁ በዲሞክራሲ ሰበብ ገብቶ በአንባገነንነት መስኮት በሚወጣዉ ፍትህ፣ ዱላ ቀረሽ ድንጋይ ዉርወራና ለክፉ በማይሰጥ አይን ሊያጠፋ በሚነሳ አስለቃሽ ጭስ ጫወታ፣ ወዘተ እስከ ህልፈተ ህይወት፣ አካል ጉዳተኛ፣ ካስተሳሰብ መኮላሸት ድረስ ከ ወዘተ መለስ…. ታዝቤ ቋቴ ሞልቶ ተርፎላችሁ ፈሰሰ፡፡
ወደ ትዝብቴ ያመጣኝ ነገር ልንገራችሁ ሰሞኑን ከወደ ቡራዩ 20ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ግምት ያለዉ እሳት ማን አለብኝ ብሎ በላዉ የተባለዉ ወሬ ትእግስት አሳጥኝ፤ ወደፊት አንድ አልሚ(ኢንቨስተር) ወደ መዲናችን ሲመጣ ያገሪቱን የፀጥታ ሁኔታ ሳይሆን የእሳትና አደጋን መኖርና አለመኖር ግምት ዉስጥ አስገብቶ እንደሚመጣ አልጠራጠርም፡፡ ምክንያቱም 20ሚሊዮን የሚጠጋን ንብረት በአንድ ምሽት ቅርጥፍ ሲያደርግ ሃይ ባይ ከሌለ ለምን ተብሎ ኢትዮጵያ ገነት ነች እንዴ በሲኦል የምንቀይራት ሳይሉ እንደማይቀሩ ጠረጠርኩ፡፡
አያይዞም ቢሮዬ እንደጎዳና ተዳዳሪ መንገድ ዳር ከመሆኑ የተነሳ ወጪ ወራጁን ለማየት ታድያለሁ ወይ ተገድጃለሁና ሁሉን አያለሁ ሰማለሁ፤ ጡሩምባ፣የትራፊክ ፊሽካ፣የሰዉ ቱሬናፋ፣የአሙቡላንስ ጩኸት … … ከሁሉ ከሁሉ ግን የአሙቡላንሱ ጩኸት ዉስጤን ልዉስ ያደርገኝና ከተቀመጥኩበት እንደ ህሊና ፀሎት ከወንበሬ እመለሳለሁ አንድም ከሃዘኔ አንድም ተገቢዉን እርዳታ አግኝቶ በጤናዉ ሊመለስ ይችል ይሆን ከሚል ስጋት፤ የሆነዉ ሆኑ አሁን ይህን ሁሉ ዙሪያ ጥምጥም የሚያስኬደኝ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወይም በእኔ ጭንቅላት ዉስጥ ያለዉ ለእሳት እና አደጋ መኪና እና ለአምቡላንስ የትራፊክ መንገድ ቅድሚያ ይሰጥ የሚል ህግ (ህጉ ከሌለ ይቅርታ ይደረግልኝ እግረኛ እንጂ ሹፌር አይደለሁምና) ሲከበር አላይም ከአደጋ መብዛት የተነሳ ትራፊኩም ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎአል ህዝቡም ከቁብ አልቆጥረዉ ብለዉ እንዲያዉም ሲሽቀዳደሙት ሳይ አዝናለሁ፡፡ ከሹፌሩ ይልቅ ትራፊኩ ብሶ ተገኝቷል፡፡ ከዚህ የአምቡላንስ መካከል እኮ ይሄኔ መንግስታችን ከያዘዉ እቅድ አንዱ የእናቶችን ሞት እንቀንስ ይገኝበት ይሆናል ነዉም፡፡ ገጠር ያለችዋ እናት አምቡላንስ አጥታ ሞተች ብለን ስንጨነቅ የአዲስ አበባዋ እናት ደግሞ መንገድ ተነፍጋ ሞተች የራስ ምታት እየሆነ ነዉ የዚህን ትዉልድ ጭንቅላት የት እናስቀይረዉ ቻይና እንደሆነ ስራ በዝቶባታልና ???
ጎበዝ ፍረዱኝ!
Deresse Reta
No comments:
Post a Comment