Thursday, October 3, 2013

ኣልሸባብ በ ኢትዮጵያ ላይ ዛተ

Photo: ኣልሸባብ በ ኢትዮጵያ ላይ ዛተበኬንያ የገበያ ኣዳራሽ ኣሰቃቂ ጥቃት ያደረሰው ሽብርተኛው ድርጅት ኣል ሻባብ በኢትዮጵያ ላይ ተከታታይ ጥቃት እንደሚያደርስ ዛተ፡፡ በመቅረጸ ድምጽ  ተቀድቶ በትዊተር የተሰራጨው ዛቻ የኬንያው ኣሰቃቂ ተግባር የመጀመርያ ብቻ እንደሆነ ገልጿል፡ ፡ በድምጽ የተላለፈው ዛቻ ኣሸባሪ ድርጅቱ በሚጠቀምበት ትዊተር ኣካውንት HMS_PR, ሓራካት ኣል ሻባብ (HSM) በሚል ምሕጻረ ቃል እንደሆነ የኖርወይ እለታዊ ጋዜጣ “ኣፍተን ፖስተን” ዘገበ፡፡ እለታዊ ጋዜጣው በድምጽ የተቀረጸውን ዛቻ ለኖርወጂያዊው የ ኣልሸብስብ ኤክስፐርት ዶክተር ስቲግ ያርለ ሃንሰን በመላክ ምንጩን ለማረጋገጥ ባደረገው ሙከራ ኤክስፐርቱ ድምጹ እዉቁ የኣልሸባብ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፈ የ ሼኽ ዓሊ ድረ እንደሆነ ኣረጋግጠዋል፡፡ኤክስፐርቱ ለኣፍተን ፖስተን በሰጡት መግለጫ  በተቀረጸው ድምጽ  ዓሊ ድረ ነው ብለዉ የገመቱት ሰው " ይህ የመጀመርያው  ነው ኬንያና ኢትዮጵያ ተከታታይ የጥቃት ማእበል መጠበቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ሲል ይደመጣል ብለዋል፡ ፡ ጉዳዩ እጅግ ኣሳሳቢ ነው ሲሉም ተደምጠዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ መሰንበቻውን በኢትዮጵያ በሽብርተኝነት የተፈረጀው ድርጅት “ግንቦት7” መሪዎች በኤርትራ በኩል ጥቃት ለመፈጸም ኣልሸባብን በመደገፍ ዓለማቀፉ ሕብረተሰብ ማእቀብ ከጣለበት መሪ ጋር ቃልኪዳን መፈጻማቸውን ሲዝቱ ሰንብተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የዲያስፖራው የተቃዋሚ ጎራ በሁለት ተከፍሎ በማሕበራዊ ሜድያ/ፓልቶክ ሲጨቃጨቅ ሰንብቷል፡፡

በኬንያ የገበያ ኣዳራሽ ኣሰቃቂ ጥቃት ያደረሰው ሽብርተኛው ድርጅት ኣል ሻባብ በኢትዮጵያ ላይ ተከታታይ ጥቃት እንደሚያደርስ ዛተ፡፡ በመቅረጸ ድምጽ ተቀድቶ በትዊተር የተሰራጨው ዛቻ የኬንያው ኣሰቃቂ ተግባር የመጀመርያ ብቻ እንደሆነ ገልጿል፡ ፡ በድምጽ የተላለፈው ዛቻ ኣሸባሪ ድርጅቱ በሚጠቀምበት ትዊተር ኣካውንት HMS_PR, ሓራካት ኣል ሻባብ (HSM) በሚል ምሕጻረ ቃል እንደሆነ የኖርወይ እለታዊ ጋዜጣ “ኣፍተን ፖስተን” ዘገበ፡፡
እለታዊ ጋዜጣው በድምጽ የተቀረጸውን ዛቻ ለኖርወጂያዊው የ ኣልሸብስብ ኤክስፐርት ዶክተር ስቲግ ያርለ ሃንሰን በመላክ ምንጩን ለማረጋገጥ ባደረገው ሙከራ ኤክስፐርቱ ድምጹ እዉቁ የኣልሸባብ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፈ የ ሼኽ ዓሊ ድረ እንደሆነ ኣረጋግጠዋል፡፡

ኤክስፐርቱ ለኣፍተን ፖስተን በሰጡት መግለጫ በተቀረጸው ድምጽ ዓሊ ድረ ነው ብለዉ የገመቱት ሰው ” ይህ የመጀመርያው ነው ኬንያና ኢትዮጵያ ተከታታይ የጥቃት ማእበል መጠበቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ሲል ይደመጣል ብለዋል፡ ፡
ጉዳዩ እጅግ ኣሳሳቢ ነው ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ መሰንበቻውን በኢትዮጵያ በሽብርተኝነት የተፈረጀው ድርጅት “ግንቦት7” መሪዎች በኤርትራ በኩል ጥቃት ለመፈጸም ኣልሸባብን በመደገፍ ዓለማቀፉ ሕብረተሰብ ማእቀብ ከጣለበት መሪ ጋር ቃልኪዳን መፈጻማቸውን ሲዝቱ ሰንብተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የዲያስፖራው የተቃዋሚ ጎራ በሁለት ተከፍሎ በማሕበራዊ ሜድያ/ፓልቶክ ሲጨቃጨቅ ሰንብቷል፡፡

No comments:

Post a Comment