ዛሬም (እንደወትሮው) አንድ ቀሽም አስተያየት ልስጥ!
በህወሓት ዉስጥ ያለው የሃይል አሰላለፍ እያየን ነው። ስብሃት ነጋ የሚዘውረው ቡድን አንሰራርቶ የፖለቲካ የበላይነቱ የሚቆጣጠርበት ዕድል ሊኖር ይችላል (መላምት ነው፣ ከውዲሁ በዚህ ጉዳይ እርግጠኛ መሆን አይቻልም)። የስብሃት ነጋ ኔትዎርክ ህወሓት ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ የትግራይ ህዝብ ጠፍሮ ሲገዛና ሲያሰቃይ የነበረ ነው።
ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን በሆነ ዉስጣዊ አለመግባብት ምክንያት የስብሃት ኔትዎርክ እየተመናመነ መጣ። አቶ አባይ ወልዱ የትግራይ ክልል ፕረዚደንት ከሆነ በኋላ ኔትዎርኩ በሌሎች ተተካ። ይባስ ብሎ ደግሞ ከመለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ አቶ አባይ ወልዱ የህወሓት ሊቀመንበር ሆነ። ከዚህ ግዜ ወዲህ ስለ አባይ ወልዱ ባህሪ መጥፎነትና የፖለቲካ ብቃት ማነስ በሰፊው ይወራ ጀመር።
እኔ የሌሎች የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት ያህል የአባይ ወልዱ የተሟላ መረጃ የለኝም። እንደሌሎቹም በሓሳብ ክርክር ፊት ለፊት ተገናኝተን አናውቅም። (መለስ፣ ስብሃት፣ ስዩም፣ አባይ ጸሃየ፣ አርከበ፣ ቴድሮስ ሓጎስ፣ ፀጋይ በርሀ … ብዙዎቹ በደንብ አቃቸዋለሁ)። አባይ ወልዱ ግን በደንብ አላውቀውም። አንድ ግዜ ብቻ በሆነ አጋጣሚ ተገናኝተን ብዙ አውርተን ነበር (አብርሃ ደስታ መሆኔን ሳያውቅ ማለት ነው)። ያኔ እንዳየሁት ትህተኛ (humble) ይመስላል (በአንድ ግዜ የሰው ባህሪ ለመገምገም ቢከብድም)።
ስለዚህ ስለ የአባይ ወልዱ ፖለቲካዊ ብቃትና የግል ባህሪ ጥሩነት ወይ መጥፎነት መመስከር አልችልም። ቁልፍ የሚባል የህወሓት ስልጣን ለባለቤቱ መስጠቱ ግን እንደማንኛውም ሰው ገርሞኛል። ይህ እንዳለ ሁኖ ስለ አባይ ወልዱ አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ። አባይ በህወሓት ካድሬዎች አይወደድም። አባይ የአምባገነንነት ባህሪ እንዳለውና የፖለቲካ ብቃት እንደሚያንሰው ለህዝቡ እንዲደርስ ተደርጓል። ማነው ስለ አባይ መጥፎነት የሚያወራ ቢባል መልሱ የህወሓት ካድሬዎች መሆናቸው ግልፅ ነው።
ለምን? አባይ የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር ከመሆኑ በፊት ቁልፍ የህወሓት ኔትዎርክ ተቆጣጥረው የነበሩ ካድሬዎች የስብሃት ነጋ ታማኞችና ዘመዶች ነበሩ። ትግራይ ሙሉ ተቆጣጥረውት ነበር። አባይ ወልዱ የነሱ ዘመድ አይደለም። አባይ ስልጣኑ ከጨበጠ በኋላ የስብሃት ታማኝ ኔትዎርከኞች ስጋት አደረባቸው። ስጋታቸውም የህወሓት ኔትዎርከኞች ቀስ በቀስ ይቀየራሉ፤ ቁልፍ የሆኑ የስልጣን እርከኞችም ከስብሃት ታማኞች ወደ አክሱም ተወላጆች ይሸጋገራሉ የሚል ነበር።
የስብሃት ህወሓቶች አንድ ሰው ከስልጣን ለማውረድ ወይም ስልጣን ለመስጠት ሲፈልጉ ስለሰውየው የፈጠራ ወሬ (የሚያዋርድ ወይ የሚያስወድስ) ለህዝብ ይነዛሉ። በቂ ኔትዎርክ ስላላቸው እነሱ የፈለጉትን ወሬ ከህዝብ ለማድረስ አይቸገሩም። እነሱ የፈልጉትን ሰው ወደ ስልጣን ለማውጣት …read more
Via: Zehabesha
No comments:
Post a Comment