Tuesday, October 1, 2013

9.5 ሚልዮን የባለ አንድ እና የባለ አምስት ብሮች የአገልግሎት ጊዜያቸው ከመጠናቀቁ በፊት ከገበያ ውጭ ሆኑ

መስከረም (ሃያ)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :- በኢትዩጵያ አቆጣጠር 2000 . በአውሮፓውያኑ 2008  ወደ ገበያ የገቡት የባለ አምስት እና ባለ አንድ ብር የመገበያያ ኖቶች ከተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ በታች በሆነ ጊዜ ውስጥ ከገበያ መውጣታቸውን የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደሚለው ገንዘቦቹ የወደሙት የአገልግሎት ጊዚያቸው አብቅቶ በመቀደዳቸው በመቆረጣቸው፣  በመንተባቸው ወይም  በመታሸታቸው ነው።
ብሮችን የሚቀብሩ እና አሽገው የሚያስቀምጡ እንዳሉ የገለጹት አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የባንኩ የህዝብ ግንኝነት ሰራተኛ፣  በየጊዜው የብር ዋጋ የመግዛት አቅም እየተዳከመ በመሄዱ ህብረተሰቡ ተጎጅ እየሆነ መምጣቱን ይገልፃሉ፡፡

መንግስት በብር አያያዝ በኩል ምንም አይነት የግንዛቤ ስራ ባለመስራቱ በመንግስት ላይ 2005 /. ብቻ 3.3 ሚልየን ብር የህትመት ወጭ ኪሰራ እንደገጠመው ሃላፊው ተናግረዋል፡፡ በተጠቀሰው አመትም 9.5 ሚልየን ብር የሚወክሉ የገንዘብ ኖቶች ከአገልግሎት ውጭ ሆነው ተቃጥለዋል።


No comments:

Post a Comment