Wednesday, February 13, 2013

መረጃ ቁልፍ ነው። ቁልፉ ደግሞ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን( ኢሳት) ነው።

                           
                                     NORWAY OSLO ESAT FUNDRAISING FEB.10 2013
የመልካም አስተዳደር እጦት፣ነፃነትና የፍትህ እጦት፣የነፃ ፕሬስ እትመት መታፈን ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች አባልና ደጋፊ በማሰር ፣ጋዜጠኞችን ማሰርና ከአገር እንዲሰደዱ ማድረግ፣የውሸት ምርጫዎች መብዛት የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ የሥራ አጥነት መበራከት፣ የአግአዚ ጦር ሠራዊት እናየጆሮ ጠቢዎችበወገናችን የሚያደርሱት እልቂትና ስቃይ ሰለባ የሆናችሁና ነጻነትና ፍትህን ናፋቂ የሆንን ፣የአገራችሁ አንድነት የሚያንገበግባችሁ ዜጎች ሁሉ አሁን ወቅቱ የሚሻው የትግል ጊዜ ላይ በመሆናችን ለዚህ ሁሉ ደግሞ መረጃ ያስፈልጋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ያለውን የሕዝብ ብሶት የሚያሰማው የሕዝብ ሀብት የሆነውን ኢሳትን መርዳት ከዘመናዊ ባርነት፣ከውሸት ፕሮባጋንዳ ለመዳን፣የሕዝብ ብሶትንና በደልን ለማሳወቅ ትልቁ የመገናኛ መሣሪያ መሆኑን አያጠራጥርም! ኢሳት የማያጠያይቅ ቁልፍ መረጃ ነው።ለዚህ ደግሞ ኢሳትን መርዳትና መደገፍ የዜግነት ግዴታ ውዴታም ነው።የሕዝብን የስቃይ ግዜ ለማሳጠር ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ተደራጅተን መረጃዎችን ለኢሳት በመስጠት ሕዝባችን መታደግ አለብን።

በኖርዌ አገር በተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ በጣም የሚያዛዝን ድራማ ተዘጋጅቶም ነበር ። ያም ድራማ የሚያሳየው የውያኔ ሰራዊትና ፌደራል ፖሊስ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ በህዝቡ ላይ የሚያደርሱትን ስቃይና እንግልት የሚያሳይ  ተመልካችን በእንባ ያራጨና ወደ ኋላ በትዝታ ወስዶ የተፈፀሙትን ግፍና መከራ ያስቃኘ ነበር።   ሕዝቡም ከልብ ያለቀሰበት,፣ ያሳዘበት ግዜም ነበር ! ድራማው ሲተውኑ የነበሩትም ሰዎች በጥሩ ሁናቴ ተጫውተውትም ነበር በተለይ በፌደራል ልብስ ለብሶ ሲተውን የነበረው ዳንኤል በቀለ የተመልካቹን ድባብ በፌደራል ፖሊስ ንግግር ፈገግ አድርጎት አምሽቷል። ባጠቃላይ የገቢ ማሰባሰቢያው የተሳካ  ምሽት ነበር።

 ሀገሩንና ሕዝቡን የሚወድ ደግሞ ኢሳትን ይታደግ!

እውነት እንዲ ነው!! ”…እኔ አርቲስት ነኝ በአርቲስትነት መኖር እችል ነበር። መፅሐፉ የሚለው ከፊትህ  እሳት ቀርቦልሃል እጅህን ወደወደድከው ጨምር ነው። እኔ እጄን ወደ ውሃ ከትቼ በአርቲስትነቴ እየደነስኩ መኖር አያቅተኝም ነበር። ነገር ግን የእውነት ጉዳይስ? የኢትዮጵያ ጉዳይስ? ዝም ብሎ የሚኖር ህሊና አለን?… እድሜዬ እንደምታዩኝ ላይሆን ይችላል። ፖለቲካ ያቃጥላል፣ ያናድዳል። ሆኖም ግን እስከመጨረሻ ለመፅናት ነው ቃል የገባሁት።አርቲስትና አክትቪስት ታማኝ በየነ
                        ኢሳት የኢትዮጵያ ሕዝብ አይንና ጆሮ ነው !
    ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
               ከዘካሪያስ አሳዬ

No comments:

Post a Comment