Wednesday, February 20, 2013

ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቹዋ መስዋዕትነት ለዘላለም ተከብራ፣ ታፍራ ትኖራለች !


የካቲት 12 ቀን 2005 ዓ. ም. የሰማዕታት ቀን ሲከበር፣ በጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ተወካይ የተደረገ ንግግር

ክቡራትና ክቡራን

እናት አገራችን ኢትዮጵያ ከብዙ ሺህ ዓመታት ጀምሮ ከቅርብ ጎረቤቶችና ከሩቅ ጎረቤቶች ትንኮሳ ሲካሄድባት በቆራጥ ልጆቹዋ መስዋዕትነት ጠላቶቹዋን ድል እያደረገች እነሆ እስከዛሬ ነጻነቱዋን አስከብራ ኖራለች፡፡
የዛሬ 77 ዓመት በ1928ዓ.ም. ፋሽስት ኢጣልያ ከአርባ ዓማት በፊት በዳግማዊ አፄ ምኒሊክ አመራር የደረሰባትን ሽንፈት
ላለመበቀል ዘመናዊ የጦር መሣሪዎችን ታጥቃ በአውሮፕላን፤በታንክ ፣በመርዝ ጢስ በመጠቀም ተንደርድራ አዲስ አበባን ተቆጣጠረች፡፡ ይህ ሲሆን የኢትዮጵያ ልጆች በየአካባቢያቸው የጎበዝ አለቃ መርጠው ጠላት ሠላም ተነስቶ እንዲቅበዘበዘ ለአምስት አመት ብቻ በየከተሞች በየካምፑ ተወስኖ እንዲቆይ አድርገውታል፡፡
በአዲስ አበባ የፋሽስት ሀይል በሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን በደል አይተው ህሊናቸው እጀግ የቆረቆራቸው ሞገስ አስገዶምና አብርሃም ደቦጭ የተባሉ ወጣት ኢትዮጵያዊያን የሙሶሉኒ ቀኝ እጅ የነበረውና ኢትዮጵያን እንዲያስተዳድር የተላከውን ሩዶልፎ ግራዚያኒን ለመግደል የወረወሩበት ቦምብ ሳይገድለው ቀረ፡፡ ግን ክፉኛ ቆሰለ፡፡ ሆኖም በድርጊቱ እጅግ የተበሳጨው ግራዚያኒ ጥቁር ሸሚዝ ለባሽ የተባሉትን የፋሽስት ጦር ጨካኝ ቡድን በአዲስ አበባ ሕዝብ ሊይ አዘመተ፡፡ በዚች ከዛሬዋ ዕለት በ1929 ዓ.ም. እስከ የካቲት 14 ቀን በሦስተ ቀናት ብቻ 30000 ( ሠሊሳ ሺህ)የሚሆን ህዝብ ተጨፈጨፈ፡፡ ጭፍጨፋውም በርሸና በስቅላትና በእሳት በመለብለብ እንደነበር ሕያው ምስከሮች በመሃላችን አሉ፡፡

አቡነ ጴጥሮስ እና አቡነ ሚካኤሌ ሕዝብ ለፋሽስት ሀይል እንዲይገዛ ያወገዙት አባቶች ያለርህራሄ ተረሽነዋል፡፡ በደብረ ሊባኖስ ገዳም ይገኙ የነበሩ 300( ሦስት መቶ) መነኮሳት በግፍ ተጨፍጭፈዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሺህ የሚቆጠሩ ህዝቦች በአዲስ አበባና ከዚያም ውጭ በሚገኙ እሥር ቤቶች ተወርውረው እንዲማቅቁ ተደርገዋል፡፡ ይህን ሁሉ በደል የፈጸመው ግራዚያኒ እ.አ.አ. በ1948 ዓ.ም. በዓለም ጦር ፍርድ ቤት ቀርቦ በኢትዮጵያዊያንና በሊቢያዊያን የፈጸመው ግፍ በማስረጃ በመረጋገጡ ለ19 ዓመታት በጽኑ እሥራት እንዲቀጣ ተፈርዶበት ወደ ወሂኒ ቤት ተወርውሮ ከሁለት ዓመት እስራት በሁዋላ ተፈቶ ደብዛውን አጥፍቶ ኖሩዋሌል፡፡ ግራዚያኒ ያን ሁሉ ጭፍጨፋ በአካሄደ በ76 ዓመት እ.አ.አ. ነሐሴ 11 ቀን 2012 በሮም አጠገብ በምትገኝ መንደር የኢጣልያ መንግስት ተወካይና የቫቲካን ተጠሪ ባለበት በትልቅ ስነ ሥርዓት የተሠራለት ሃውልት ተመርቁዋል፡፡ የንጹሀንን ደም በከንቱ ያፈሰሰ አውሬ ጀግና ተብሎ መከበሩ ለሰው ልጅ ደህንነት የሚቆረቆርን ሁሉ አስገርሙዋል፡፡ ይህ ድርጊት እንዲቀለበስ በዓለም ዙሪያ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፡፡
የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ድርጊቱ አስቆጥቶት ሀውልቱ እንዲፈርስ በመጠየቅ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶበታል፡፡
ዛሬም ይህ ሐዋልት እኒዲፈርስ አበክረን እንጠይቃለን፡፡
የፋሽስቱ መሪ ቤኒቶ ሙሶሎኒ በኢትዮጵያና በጣልያን ሕዝቦች ሊይ ያደረሰው ግፍ ወደር የሌለው እንደነበር በሕይወት ያለና የታሪክ ተመራማሪዎች በታሪክ መዛግብት የሰጡት የምስክርነት ቃል አረጋግጡዋል፡፡
በጣልያን አገር በመጨረሻዋ ሰዓት ሙሶሎኒ በጣልያን አርበኞች እጅ እንዳይወድቅ ሲቅበዘበዝ ተይዞ በጥይት ከተደበደበ በሁዋላ ሬሳው ወደ ሚላን ተወስዶ ተዘቅዝቆ መሰቀለ ምን ያህል ህዝብ እንደጠላው ያሳያል፡፡ ይህን ግፈኛ ዛሬ ሙሶሎኒ በሰው ላይ ጥይት ተኩሶ አያውቅም፤ መልካም አስተዳዳሪ እንደነበር የሚመሰክሩ የጣልያን ፖለቲከኞች ቀና ቀና ማለት ጀምረዋል፡፡
ይህ አባባል በንጹሃን ደም ማላገጥ ይሆናል፡፡ ይህን አስተሳሰብ የሚያራምዱት ከድርጊታቸው አእንዱቆጠቡ እንጠይቃለን፡፡
የኢትዮጵያና የጣልያን ሕዝቦች ወዳጅነት በፋሽስቶች አይበረዝም !
የአረመኔው የግራዚያኒ ሓውልት አንዲፈርስ እንጠይቃለን !
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
            ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment