Tuesday, February 26, 2013

‹‹ሐይማኖቴን፣ሐሳቤን፣መብቴን፣ የመግለጽ ነጻነት አለኝ ››


 ነፃነት ዘመቻ የምደግፈው የዚህኛው ወይም የዚያኛው ርዕዮተዓለም ደጋፊ ስለሆንኩ አይደለም፡፡ በዚህ ዘመቻ ላይ የሐሳብ ነጻነት ፈላጊ ነኝ።
(Freedom of Religion,Expression, Right) ደጋፊ ነኝ፡፡ 
ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ተፈጥሮ የለገሰን ነጻነት ነው፡፡ ሰው ሁሉ ሐሳብ አለው፤ ሐሳብ ያለው ሁሉ የመናገር ተፈጥሯዊ ተሰጥኦ አለው፤ በሕገ-መንግሥቱ እስከተፈቀደልኝ ድረስ ይህንን ተፈጥሯዊ ስጦታዬን መጠቀሜ እና የሌሎችን ማክበሬ ለማንም ወገንተኛ ብሆንም ባልሆንም የማምንለት እና የከራከርለት ነው፡፡
ይህንን ነጻነቴን ስጠቀም እና ሳደርግ በእራሴ ማሰብ እና ማድረግ የማልችል ይመስል ‹‹ከጀርባው ማን አለ?›› መባል ሰልችቶኛል፡፡ አገሬን እወዳለሁ፤ የገዛ አገሬን እና ሕዝቤን የሚጎዳ ሐሳብ እና ድርጊት ማፍለቅ አልፈልግም፤ ታዲያ ለምን ሐሳቤ እና ሐሳቤን የመግለጽ ነጻነቴ ይገደባል? የኔ ሐሳብ ከንቱ መሆን አለመሆኑን ገምግሞ የማጽደቅ ችሎታ ያለውስ ማነው? የኢትዮጵያ ሕዝብስ ሰምቶ ሲያበቃ ክፉ እና ደጉን መለየት አይችልምን? 
ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ ሃይማኖታዊ፣ ፖለቲካዊና ሌሎችም አመለካከቶች አሉ፡፡ ከእኔ ተቃራኒ ቢቆሙም እንኳን እንደኔ የራሳቸው ሐሳብ እና አመለካከት ያላቸውን ሰዎች ሁሉ ሐሳባቸውን የመግለጽ ነጻነታቸውን አከብራለሁ፡፡ መንግሥትም ይህን ተፈጥሯዊ መብቴን እንዲያከብርልኝ እፈልጋለሁ፡፡ የመንግሥትን አመለካከት ለማንፀባረቅ ፓርላማ፣ የመንግሥት ብዙኃን መገናኛ እና ብዙ መንገዶች አሉ፤ የእኔን ሐሳብ ግን የማቀርብበት መንገድ የለኝም፡፡ የፕሬስ ነጻነት ይከበር፣ የኢንተርኔት ገደብ ይቁም፣ ዙሪያ ገባውን በፍርሐትና በጥርጣሬ ሳልመለከት ሐሳቤን የመግለጽ ነጻነቴ ይከበርልኝ፡፡ ይህ የሚሆነው የታገዱ የሕትመት ውጤቶች እና የኢንተርኔት ብዙኃን መገናኛዎች ሲለቀቁ፣ ሐሳባቸውን በመግለጻቸው የተፈረደባቸው የኅሊና እስረኞች ሲፈቱ፣ የተሰደዱ ጋዜጠኞች ወደአገር ቤት ሲመለሱ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የሁላችንም ነች፤ እኔም ለአገሬ የማዋጣው ሐሳብ አለኝ፤ እንድናገረው ይፈቀድልኝ፡፡
"ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ ነጻነት ሕገ-መንግሥታዊ መብት እንጂ በመንግሥት በጎ ፈቃድ የሚቸር ወይም የሚነፈግ ስጦታ አይደለም።"
ወያኔ የራሱን ህገ መንግስ ያክብር፡:
ዘካሪያስ አሳዬ
           ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
                   ከሰብኣዊ


No comments:

Post a Comment