Tuesday, February 5, 2013

ኢፍዴኃግ ከምርጫው እወጣለሁ ሲል ገዢውን ፓርቲ አስጠነቀቀ



የአራት ፓርቲዎች ግንባር የሆነውና ከገዢው ፓርቲ ጋር በፓርቲዎች የጋራ /ቤት የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ፍትህ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ግንባር (ኢፍዴኀግ) በምርጫው ያቀረብኩት ዕጩ ታስሮብኛል ሲል ቅሬታውን በመግለፅ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በምርጫው ለመቀጠል አስገዳጅ ሁኔታ ተፈጥሯል ሲል ገዢውን ፓርቲ አስጠነቀቀ። 

የግንባሩ ዋና ፀሐፊ አቶ ገረሱ ገሳ ትናንት ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት፤ የግንባሩ አባል የሆነው የደቡብ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች አንድነት ፓርቲ የደቡብ ኢትዮጵያ አደራጅ የሆኑት አቶ ዱባለ ገበየሁ የተባሉና ሌሎች ሦስት ሰዎች ለዳውሮ ዞን /ቤት በዕጩነት ተመዝግበው እየተመለሱ እያለ መታሰራቸውን አስታውቀዋል። 
ግለሰቡ የታሰሩት ባለፈው አርብ ዕለት መሆኑን የጠቀሱት አቶ ገረሱ በዳውሮ ዞን የሚገኘው የግንባሩ /ቤትም እንዲዘጋ መደረጉን ገልፀዋል። ግለሰቡ የታሰሩበት በምክንያት ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመገርሰስ ሕዝብ ቀስቅሰዋል፣ የቀበሌ ታጣቂዎችን መሳሪያ በኃይል አደራጅተው አዘርፈዋል በሚል በዳውሮ ዞን ከፍተኛ /ቤት ከትናንት በስቲያ ቀርበው 14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል ሲሉ አቶ ገረሱ ጨምረው ገልፀዋል።
በተጨማሪም ግለሰቡ የታሰሩት ከክልል ባለስልጣናት በወረዳ ትዕዛዝ መሆኑን አረጋግጠናል ያሉት አቶ ገረሱ፤ ጉዳዩን በተመለከተ ለኢህአዴግ /ቤትና ለምርጫ ቦርድ አመልክተናል ብለዋል። 
በዳውሮ ዞን በምርጫው እንዳንወዳደር ስለተፈለገ አባላችን ታስሯልያሉት አቶ ገረሱ፤ የአባሎቻችንን ነፃነት ካልጠበቀ በጋራ በም/ቤት አባል ብንሆንም ችግራችንን ለሕዝብ ከመግለፅ አንቆጠብም ብለዋል። የጋራ /ቤት በተስማማንባቸው አዋጆችና በሀገሪቱ ሕግ መሠረት ገዢው ፓርቲ መንቀሳቀስ አለበት ሲሉም አሳስበዋል።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የደቡብ ክልል አስተባባሪ አቶ አብርሃም ጌዴቦ ጉዳዩን በወሬ ደረጃ ቀርቦ ለማየት መሞከሩን ገልፀው፤ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያለው በቂ ማስረጃ ባለመቅረቡ ለማጣራት እንዳልተቻለ ገልፀዋል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ የፓርቲው አባል መታሰራቸው እውነት መሆኑን ቢገልፁም፤ ግለሰቡ የታሰሩበት ምክንያት ከምርጫ ጋር መያያዝ፣ አለመያያዙን ለማጣራት አልቻልንም ብለዋል።

                            ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment