ወያኔ የህትመት ነፃነትን አሳጥቶን፣የመናገር መብታችን ተነፍጎ፣ስለ ነፃነትና ስለ መብት ስንጠይቅ አሸባሪ በማለት በማፈን፣ በማሰርና በመግደል የት እንዳለን እንኳን በማይታወቅ ቦታ አፍኖን እየጠጣልን ስንቶቻችን ነን? ቤቱ ይቁጠረው
ብለን ዝም ማለት ያለብን? ዝም ማለት የለብንም!ትግል የሚጀምረው ከራስ ነው።
ዛሬ ላይ ሆነን ማን ይምራን ማለት የለብንም መሪዎቹ እራሳችን ነን መሆን ያለብን። ለምን ከፖለቲከኞቹ
ብቻ መሪ እንፈልጋለን? ለምን ዛሬ ሕዝቡ መሪ አይሆንም!
የአስተዳደር ብልሹነት፣የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ስራህን በአግባቡ እንዳትሰራ መደረግ፣ነፃነት
የፍትህ እጦት፣የነፃ ፕሬስ እትመት መታፈን ፣የፖለቲካ
ፓርቲዎች አባል ደጋፊ በማሰርና በማንገላታት ፣ጋዜጠኞችን እውነትን እንዳይናገሩና እንዳይፅፉ ማሰርና ከአገር እንዲሰደዱ ማድረግ፣የውሸት
ምርጫዎች መብዛት፣የፈለከውን የፖለቲካ ፓርቲ መምረጥ
አለመቻል፣ የሰብዓዊ
መብቶች ረገጣ፣የጎሳ ግጭት በመፍጠር ዘር ከዘር
እንዲጫረስ ማድረግ፣ የሥራ
አጥነት መበራከት፣ወጣቱንና ሙህራኑን ከአገር እንዲሰደዱ
ማድረግ፣ የአግአዚ
ጦር ሠራዊትና እና “የጆሮ ጠቢዎች”
በወገናችን የሚያደርሱት እልቂትና ስቃይ ሰለባ የሆናችሁና ነጻነትና የአገራችሁ አንድነት የሚያንገበግባችሁ ዜጎች ሁሉ አሁን ወቅቱ የሚሻው የትግል ጊዜ ላይ በመሆናችን በአንድነት
የወያኔን አገዛዝ ከጫንቃችን የምናሶግድበት ወቅት ላይ ነን።በኢትዮጵያዊነት ስሜት ከተረባረብን ትግሉን አፋጥነን የነፃነትን ድል
መውረስ እንችላለን።
የድል አጥቢያ
አብሳሪ የሆኑ ኢትዮጵያችን የሚያስፈልጋት የሰው ለውጥ ሳይሆን ስር ነቀል የሆነ የስርአት ለውጥ ነው፤ ይህ ማለት ደግሞ ከአገራችን ዉስጥ ተነቅሎ መወገድ ያለበት ወያኔ/ኢህአዴግ እራሱ ነው። ሌላው ለውጥ ኢትዮጵያዊው ወጣት ከአበው የተማረውን፣ የወረሰውን አመኔታን በመገንባት የውርደት ዝምታን በእምቢተኝነት በመለወጥ የማያዳግም የስርአት ለውጥ እንዲመጣ አበክሮ በመታገል፤ ኢትዮጵያን ወደ ዘላቂ ሰላምና አንድነት ማምጣት ነው።
ከእንግዲህ ኢትዮጵያን ‹‹በነፃነቷ ታፍራና ተከብራ የኖረች አገር›› ብሎ የሚጠራ ካለ እርሱ ጅል ነው፡፡ አገር ማለት ሕዝብ ነው፡፡ ያለ ሕዝብ አገር ትርጉም የለውም፡፡ ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ ታፍሮና ተከብሮ እየኖረ አይደለም፡፡ የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ ከቅኝ ገዢም በከፋ ሁኔታ ህዝብን ለውርደት እና ለስደት እየዳረገ ነው፡፡ ከአምባገነኑ ጋር በመሞዳሞድ ከርሳቸውን የሚሞሉ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሆዳሞች በህዝብ ውስጥ መኖራቸው እና ለእነርሱ ይህ እውነት እንደማይታያቸው እርግጥ ነው፡፡ እነዚህ ከርሳሞች አምባገነኑ ገዢ ሲወድቅ አንገታቸውን ይደፋሉ፡፡ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ የገዛ ህዝቧ ተሸማቆ፣ ተንቆ እና ተዋርዶ የሚኖርባት አገር ናት፡፡ ይህ ሕዝብ ለነፃነቱ ካልታገለ መከራው እንደሚበዛ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ከሆድህ እና ከነፃነትህ የቱን ትመርጣለህ ሲሉት ሆዴን ካለ ራሱን ለባርነት ዝግጁ እንዳደረገ ይወቀው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሕግ የለም፡፡ ፍትኅ ገደል ውስጥ ተፈጥፍጣለች፡፡ በመቀጠልም
ኢትዮጵያዊ የሆንክ ወገኔ ሁሉ ክርስትያን፣ እስላም ወይም እምነት የለሽ ሳትል በዘር ሳትከፋፈል በአንድ ላይ በጋራ ተነስተህ ይህችን ታሪካዊት እና ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያን ለመታደግ እጅ ለጅ መያያዝ ይኖርበሃል። ባለፉት ዘመናት ደጋጎቹ አባቶቻችን ዘር ሳይለዩ በሃይማኖት ሳይከፋፈሉ አንድነታችንን ለመፈታተን በመጡ ጠላቶቻችን ላይ በጋራ በማበር ቀፎው እንደተነካበት ንብ ከአራቱም ማእዘናት ከሰሜን፣ ከደቡብ፣ ከምስራቅና ከምእራብ በመትመም ደማቸውን አፍስሰው፣ አጥንታቸውን፣ ከስክሰው በመርዝ ጪስ እየተቃጠሉ ጠላትን አደባይተውና አሳፍረው ወደመጣበት በመመለስ በደም የተጻፈ ታሪክ ትተውልን አልፈዋል። ዛሬም ይህ ኢትዮጵያዊ ትውልድ የአባቶቹ ልጅ በመሆኑ ሴት፣ ወንድ፣ እስላም፣ ክርስትያን ሳይል እግዚአብሄር ሲፈጥረን ያጎናጸፈንን ነጻነት የሚባል ጸጋ ለመቀዳጀትና ኢትዮጵያዊ አንድነቱን፣ በነጻ የማምለክ መብቱን ለማስከበር እጅ ለእጅ ተያይዞ መነሳት አለበት። ዛሬ ታሪክ የሚሰራበት ወቅት ላይ በመሆናችን ሁላችንም በየተሰለፍንበት ሙያ በአንድ ላይ ሆነን ወደ አምላካችን በመጸለይ እና ጠንክሮ በመታገል ዘረኝነትን ለማጥፋት፣ የሃገራችንን አንድነት ለማስከበር ባጠቃላይ ኢትዮጵያ በምድሯ ላይ የሚኖሩ ዜጎቿ ሁሉ በሰላም፣ በአንድነት እና በፍቅር የሚኖሩባት ሃገር ትሆን ዘንድ ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ።ነፃነት በእጃችን ለማስገባት እንታገል!
እውነት ሁሌም አሸናፊ ነች።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ከዘካሪያስ
አሳዬ
No comments:
Post a Comment