በመነኮሳት ስም ያደራጃቸው አባላቱም በቤተ ክህነቱ የተለያዩ እርከኖች ላይ በመቀመጥ ቤተ ክርስቲያናችን የክርስቶስ ሳይሆን የአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ዓላማ ማስፈጸሚያ እንድትሆን አስገድደዋታል። ወታደራዊው መንግሥት እንኳን ያላደረገውን የቤተ ክህነቱን መዋቅር ከዋናው እስከ አጥቢያው ካባ በለበሱ ካድሬዎች በማደራጀት ቤተ ክርስቲያኒቱ የክርስቶስ መንግሥት ሳይሆን የህውሃተና ጀሌዎቹ! አገልጋይ እንድትሆን አድርገዋታል።
ይህም ሳያንስ በልማትና በዕድገት ስም የቤተ ክርስቲያኒቱ ይዞታ ከመደፈሩም ባሻገር የገዳማት ርዕስ የሆነውን የዋልድባን ድንበር በመጋፋት እና የቅድስና ኑሮውን በመግሰስ አበው ገዳማውያን የመከራ ኑሮ እንዲኖሩ በማስገደድ ላይ ይገኛል። ታዲያ እዚህ ላይ ተያይዞ አብሮ የሚነሣው ነገር “ሃይማኖቱን የሚወደው፣ ለእምነቱና ለማተቡ ሟች የሆነው ክርስቲያን ሕዝብ እንዴት ዝም አለ? መንግሥትስ እንዴት የሕዝቡን ስሜት ከቁብ ሳይቆጥረው ቀረ? ሕዝቡንስ እንዴት እንዲህ ሊንቀው ቻለ? ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ‘ድምጻችን ይሰማ’ ሲሉ የክርስቲያኑ ዝምታ ከምን የመነጨ ነው?” ወዘተ የሚለው ጥያቄ ነው።''
እውነት ግን ዝምታው ከየት የመጣ ነው? የፍርሃት ቆፈን ውስጥ የተደበቅነው ለምንድን ነው? እስከመቼስ ነው? አረ ዝምታው ይሰበር!
እውነት ግን ዝምታው ከየት የመጣ ነው? የፍርሃት ቆፈን ውስጥ የተደበቅነው ለምንድን ነው? እስከመቼስ ነው? አረ ዝምታው ይሰበር!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ከሰብኣዊ
No comments:
Post a Comment