የካቲት ፩ (አንድ)1 ቀን8 ፳፻፭(2005) ዓ/ም
በሳውዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ለ አባይ ግድብ ማሰሪያ የሚውል የቦንድ ግዥ የሚካሄድበትን ፕሮግራም የያዘው ከሳምንታት በፊት ነው።በፕሮግራሙ መሰረት ትናንት ሐሙስ ከወትሮው በተለዬ መልኩ በሪያድና አካባቢው የሞኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን በስፍራው በመገኘት የኮሙኒቲውን አዳራሽ ከ አፍ እስከ ገደፉ ይሞሉታል።
የቦንድ ግዥውን ፕሮግራም ለመምራት ወደዚያው ያቀኑት የኢህአዴግ ባለስልጣናትም በስብሰባው ከተገኘው በርካታ ሰውደጎስ ያለ ገንዘብ እንደሚያሰባስቡ ተስፋ ያደረጉ።ሆኖም ሰሞኑን<<ጂሀዳዊ ሀረካት”በሚል ርዕስ መንግስት በ እስር ላይ ያሉትን የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች አስመልክቶ በቴሌቪዥኑ በለቀቀው ፊልም ቁጣቸው እየተቀጣጠለ በ አዳራሹ የተገኙት ሙስሊሞች የቦንድ ግዥውን ስብሰባ ወደ ከፍተኛ የተቃውሞ ትዕይንት ቀይረውታል።“ግድቡ ከመሪዎቻችን መፈታትና ከሰላማችን በሁዋላ ይደርሳል”በማለት ቅሬታቸውን መግለጽ የጀመሩት በሪያድ የሚኖሩ ሙስሊሞች፤ <<ኢቲቪ ሌባ!ኢቲቪ አሸባሪ!መጂሊስ ይውረድ! መሪዎቻችን ይፈቱ!ድምፃችን ይሰማ!>>በማለት አዳራሹንና አካባቢውን በከፍተኛ ጩኸት አናውጠውታል።ገንዘብ ለማሰባሰብ ወደ ፕሮግራሙ የመጡት የ ኢህአዴግ ባለስጣናትም ሁኔታቸው ከቁጥጥር ውጪ በመሆኑ በከፍተኛ ድንጋጤ በመጡበት አኳሁዋን መመለሳቸው ታውቋል።በ ሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በቅርቡ መንግስት በህዝበ ሙስሊሙ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍ እና በደል በመቃወም ለመንግስት ተደጋጋሚ የተቃውሞ ደብዳቤ ማስገባታቸው ይታወሳል
ከሰብኣዊ
No comments:
Post a Comment