Sunday, February 3, 2013

እስራኤል ለኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች አስገዳጅ የወሊድ መቆጣጠሪያ መስጠቷን አመነች


ከአምስት ዓመታት በፊት ጥርጣሬ ፈጥሮ የነበረውና የእስራኤል መንግስት በአስገዳጅ ሁኔታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒት እንዲወጉ አድርጓቸዋል የሚለው ወሬ እውነት መሆኑን የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሆኑት ፕሮፌሰር ሮን ጋምዙ፤ እስራኤል ውስጥ ለሚገኘው የሲቪል መብቶች ተሟጋች ማህበር በፃፉት ደብዳቤ አመኑ።
ኢትዮጵያውያኑ እናቶች “ዴፖ-ፕሮቬራ” የተሰኘውን የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒት መወጋታቸውን የሚያትት ወሬ ከዚህ ቀደም ወጥቶ የነበረ ቢሆንም፤ በእስራኤል ባለስልጣናት እውቅና ባለመስጠታቸው ምክንያት ባለፉት አምስት አመታት ተሸፋፍኖ ቆይቷል ይላል ዘገባው። የጤናጥበቃ ሚኒስትሩ አክለውም ባስተላለፉት ትዕዛዝ በኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ላይ የተፈፀመው አስገድዶ መድሃኒት የመስጠት ጉዳይ በአፋጣኝ እንዲቆም ብለዋል።

ይህ ጉዳይ ዳግም ይፋ ሆኖ መነጋገሪያ ሊሆን የበቃው በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ አካባቢ በተላለፈ የቴሌቪዥን የምርመራ ፕሮግራም ሲሆን፤ አንዲት ስሟ ያልተጠቀሰ የ35 ዓመት ሴት እንደተናገረችው፣ “በአስገዳጅ ሁኔታ የወሊድ መቆጣጠሪያውን እንደወጓቸውና ያንን ባያደርጉ ደግሞ ወደስደተኞች መቆያ ጣቢያ እንደሚመልሷቸው አስጠንቅቀዋቸው እንደነበር አስረድታለች። ዜናው አክሎም፤ ምናልባትም በዚህ ምክንያት ይሆናል ካለፉት 10 ዓመታት ወዲህ የኢትዮጵያኑ ስደተኞች የወሊድ መጠን በ50 በመቶ ቀንሶ ተገኝቷል ብሏል።
                    ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
                                   ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment