Tuesday, February 5, 2013

ኢቲቪ በኦርቶዶክስ የሃይማኖት አባቶች ላይ እንደ ሙስሊሙ ተመሳሳይ ፊልም ለማሰራጨት ዝግጅት ማጠናቀቁን ታወቀ


ጥር ፳፰ (28) ቀን ፳፻፭( 2005) ዓ/ም
በእስር ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን በተመለከተ በዛሬው እለት ዶክመንተሪ ፊልም ለማሰራጨት ያስተዋወቀው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የሃይማኖት አባቶች ላይ ተመሳሳይ ፊልም ለማሰራጨት ዝግጅት ማጠናቀቁን ውስጥ አዋቂ ምንጮችን የጠቀሱ ዘገባዎች አመልክተዋል፤ቤተ ክህነት ለፊልሙ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጓ የተገለፀ ሲሆን ፤የሃይማኖት አባቶችም በሂደቱ ተዋናይ መሆናቸው ተመልክቶአል።

ሐራ ተዋህዶ የተባለው የኦርቶዶክሳዊያን ድህረ ገፅ እንደዘገበው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተቀነባበረው ፊልም ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዎስን ጨምሮ በሶስትአባቶች ላይ አተኩሯል።ፓትሪያልክ አቡነ መርቆሪዮስን ከቀድሞው ስርአት ጋር ግንኙነት አላቸው የሚል ውንጀላ የጨመረው ፊልም ብፁእ አቡነ መልክአ ጻዲቅን ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ድጋፍ መስጠታቸውን በአሸባሪነት መፈረጁም ተመልክቶል።
በብጹ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያና በቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሀፊ በብጹ አቡነ መልክአ ጻዲቅ እንዲሁም በብፁዕ አቡነ መቃሪዎስ ላይ የተነጣጠረው ይህ ዶክመንተሪ ፊልም በቅርቡም ይቀርባል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
ብጹ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ነፍጥ ካነሱ ሀይሎች በተልይም ከግንቦት ሰባትና አርበኞች ግንባር ጋር ይሰራሉ ተብለው  የተወነጀሉ ሲሆን በአሸባሪነትም ተፈርጀዋል ተብሎል።
በዚህ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ይቀርባል በተባለው ፊልም ላይ ንቡረዕድ ኤሊያስ አብርሀና 3 ሊቃነ ጳጳሳት በአስረጂነት መካተታቸውም ተመልክቶል። ሌሎች አባቶችም ፍቃደኛ አለመሆናቸውም ከዘገባው ለመረዳት ተችሎል። የፊልሙ ርዝማኔ 1 ፡ 30 ሲሆን በሁለት ክፍል ይቀርባል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
              ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
                                 ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment