Thursday, February 7, 2013

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፎቶግራፎችና ፖስተሮች ይነሱ!ሲል ሪፖርተር ጋዜጣ ጠየቀ።


ጋዜጣው በትናንት ርዕሰ-አንቀጹ አቶ መለስ ፎቶና ፖስተር ያልተሰቀለበትን አዲስ አበባ ጎዳና ፈልጎ ማግኘት እንደማይቻልና ፎቷቸው በሁሉም ስፍራ እንዳለ በመጥቀስ፦<<አሁን ግን ይብቃ! ፎቶዎቹና ፖስተሮቹ ይነሱእንላለን>> ብሏል።
ፖስተሮቹ ዘላለማዊ ተደርገው መወሰድ እንደሌለባቸውም ጋዜጣው አቋሙን ገልጿል።

<<በፖስተሮቹና በፎቶግራፎቹ መሰቀል ለመነገድ፣ ለማስመሰልና ለማጭበርበር የሚፈልግ ሰው ካለም በቃህ ሊባል ይገባል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ስም አትነግድ፣ አታጭበርብር፣ አታታል ሊባል ይገባዋል፡፡>>ሲልም የአቶ መለስ ስም መነገጃ እየሆነ መምጣቱን ጠቁሟል።

ጋዜጣው በዚሁ ርዕሰ አንቀጹ፦<<ቃላትም ትርጉም ይኑራቸው፡፡ በቃላት ድርደራ ብቻ ‹‹ራዕይ›› እና ‹‹ሌጋሲ›› እያልን እየለፈለፍን በተግባር ግን ራዕዩንና ሌጋሲውን የሚፃረር ሥራ የምንሠራ ከሆነ ያስተዛዝባል፤የእሳቸውን ስምና ሥራ መነገጃና መደለያ የምናደርገው ከሆነ ከሞራል አንፃር ያስወቅሰናል ብቻ ሳይሆን በታሪክም እንጠየቅበታለን>>ብሏል።

               ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
                              ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment