Friday, February 8, 2013

የኢህአዴግ መንግስት በሳኡዲ አረቢያ-ሪያድ ለ ዓባይ ግድብ ቦንድ ግዥ የጠራው ስብሰባ ወደ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀይሮ በተቃውሞ ተጠናቀቀ




በሳውዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ለ አባይ ግድብ ማሰሪያ የሚውል የቦንድ ግዥ የሚካሄድበትን ፕሮግራም የያዘው ከሳምንታት በፊት ነው።የካቲት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
በፕሮግራሙ መሰረት ትናንት ሐሙስ ከወትሮው በተለዬ መልኩ በሪያድና አካባቢው የሞኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን በስፍራው በመገኘት የኮሙኒቲውን አዳራሽ ከ አፍ እስከ ገደፉ ይሞሉታል።

የቦንድ ግዥውን ፕሮግራም ለመምራት ወደዚያው ያቀኑት የኢህአዴግ ባለስልጣናትም  በስብሰባው ከተገኘው በርካታ ሰውደጎስ ያለ ገንዘብ እንደሚያሰባስቡ ተስፋ  ያደረጉ።
ሆኖም  ሰሞኑን<<ጂሀዳዊ ሀረካት”በሚል ርዕስ መንግስት  በ እስር ላይ  ያሉትን የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች አስመልክቶ  በቴሌቪዥኑ  በለቀቀው ፊልም ቁጣቸው እየተቀጣጠለ በ አዳራሹ የተገኙት ሙስሊሞች  የቦንድ ግዥውን ስብሰባ ወደ ከፍተኛ የተቃውሞ ትዕይንት ቀይረውታል።
“ግድቡ ከመሪዎቻችን መፈታትና ከሰላማችን በሁዋላ ይደርሳል”በማለት ቅሬታቸውን መግለጽ የጀመሩት በሪያድ የሚኖሩ ሙስሊሞች፤ <<ኢቲቪ ሌባ!ኢቲቪ አሸባሪ!መጂሊስ ይውረድ! መሪዎቻችን ይፈቱ!ድምፃችን ይሰማ!>>በማለት አዳራሹንና አካባቢውን በከፍተኛ ጩኸት አናውጠውታል።
ገንዘብ ለማሰባሰብ ወደ ፕሮግራሙ የመጡት የ ኢህአዴግ ባለስጣናትም ሁኔታቸው ከቁጥጥር ውጪ በመሆኑ በከፍተኛ ድንጋጤ በመጡበት አኳሁዋን መመለሳቸው ታውቋል።
በ ሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በቅርቡ መንግስት በህዝበ ሙስሊሙ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍ እና በደል በመቃወም ለመንግስት ተደጋጋሚ የተቃውሞ ደብዳቤ ማስገባታቸው ይታወሳል።
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment