የጋዜጠኛና ደራሲው አሳዛኝ ሕይወት
እውቁ ጋዜጠኛና ደራሲ ሰሎሞን ሙሉ ታፈሰ፥ ያገለገላት አገሩ፣ የተገለገሉበት <የዛሬ ታዋቂ> አርቲስቶችና የፊልም ባለሙያዎች …ብቻ ሁሉም ፊት ነስተውታል። አንገቴን አቀርቅሬ ከልብ ከማለቅስላቸው ውድ የኢትዮጲያ ልጆች አንዱ ሰሎሞን ነው!! በእርሱ ድንቅ የጥበብ ጭንቅላት በጣም በርካቶች የናጠጡ ሃብታም ሆነዋል። በጣም በርካታ የጋዜጣና የቴሌቪዥን ድራማዎች ሰርቶዋል።
ዛሬ ግን የጎዳና ተዳዳሪ ነው፤ ይህን አስከፊ ሕይወት ከተላመደው አምስት አመት ገደማ ሆነው። …ስለዚህ ታላቅ ሰው የቱን ተናግሬ የቱን እንደምተው ይቸግረኛል!.. በ <m> ፊደል ስማቸው የሚጀምር የአለም መሪዎችን በተመለከተ ከ17ዓመት በፊት የፃፈውና ፥ « ሙባረክ፣ መለስ፣ መንግስቱ፣ ሙጋቤ፣ ሙአመድ ጋዳፊ፣ ሚሎሶቪች፣ …ወዘተ» ጠቅሶ ስለ ባህሪያቸውና ስለአቋማቸው (ተመሳሳይነት) ሰፊ ትንታኔ የሰጠበትና አስደናቂ ፀሃፊነቱን (ነብይ ጭምር) የተባለበት አይረሳም። በተለይ ስለ መለስ የፃፈው ውሎ አድሮ ብዙ መዘዝ አስከትለውበታል። እንደትንቢት የገለፀው ግን አንድም መሬት ጠብ ያለ ነገር የለም። ሰሎሞን፥ በዚህ ህይወትም ውስጥ ሆኖ ይህን ይላል፥ « የሰው ልጆች የስፕሪት ሃይልን.. መከራ አያውቁትም!» ….
ለድንቅ ደራሲው ፈጥነን የምንደርስ ስንቶች ነን?...ተግባራዊ መልስ እንስጥ!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ከሰብኣዊ

No comments:
Post a Comment