Friday, February 8, 2013

አሸባሪ አይደለውም !! ግን አሸባሪ መንግስት አለኝ!!!


             
ምን አይነት ስብእና ቢኖራቸው ነው የዚህ መንግስት ደጋፊዎች ሁሌ እየተዋረዱ፣ እየተሸማቀቁ ይህን የሽፍታ ስብስብ "መንግስት ነው" ብለው የሚደግፉት? በቃ ገና ለገና ገዢው ሰውየ ከትግራይ ከሆነ ትግሬ በሞላ፣ ገዢው አማራ ከሆነ አማራ በሞላ፣ ገዢው ኦሮሞ ከሆነ ኦሮሞ በሞላ አጥንቱን እየቆጠረ ከራሱ "የዘር ግንድ" ለመጣው ገዢ ሁሉ ድጋፉን መስጠት አለበት? እንዴ! መማራችን ከአጥንት ቆጠራ ካላላቀቀን፣ ምኑን ተማርነው? በዘር ማጥፋት ወንጀል  ተከሰው የነበሩ የትግራይ ልጆች በእስር ቤት ያዩትን ነገር ሁሉ ረስተውት ዛሬ ይህን ዘረኛ መንግስት ለምን  " ዘረኛ አላችሁት" ብለው ሊሞግቱን ሲደፍሩ ስመለከት ግርም ይለኛል። እንዴ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ዘረኝነት እንኳን ሰው አይደል ወፉ አይናገረውም! በቃሊቲ ብትሉ በማእከላዊ ብትሉ በመከላከያ የወታደሩ የስራ ቋንቋ ምን ሆነና ነው? እን ዝም ብለን ስንመለከት ፈሪ አደረጉን እንዴ!  እንደግፍ ከተባለማ ወደ ዘመነ መሳፍን ኢትዮጵያ ተመለስን ማለት ነው። 

የመንግስት ደጋፊዎች ዛሬም፣ ፍርድ ቤት ራቁቱን ሲቀር እያዩ፣ መንግስትን ለመደገፍ ሲነሱ አያፍሩም። ዛሬም ኢትዮጵያን አሽመድምዷት የሄደውን ወንጀለኛ ዘረኛና መርዛም የታሪክ አተላ " ባለራእይ" እያሉ ሲጠሩት አይሸማቀቁም። 
ሽፍታ ለአንድ ቀን የበላይነት እስከተሰማው ድረስ ለነገ አያስብም፤ በስልጣን ላይ ያሉት የኢትዮጵያ ሽፍቶች ዛሬ ክርስቲያኑ ከሙስሊሙ ቢጫረስ፣ አገር ቢፈርስ፣ ታሪክ ቢበረዝ ግድ የላቸውም። እነዚህ ሽፍቶች ክርስቲያኑንና ሙስሊሙን ለማጫረስ የጠነሰሱት ተንኮል ጣሊያን በዘመኑ ካደረገው ጋር አንድ ነው። ልዩነቱ እነዚህ ተንኮለኞች ከኢትዮጵያ ምድር የበቀሉ መሆናቸው ብቻ ነው። ደግነቱ ጣሊያን እንዳልተሳካለት ሁሉ፣ እነዚህ ፋሽስቶችም አይሳካላቸውም። አካፋን አካፋ ማያው ጊዜ አሁን ነው!

አሸባሪው መንግስት ከዚህ ቀደም አኬልዳማ ፣ አሁን ደግሞ የጅሀድ ሀረካት ዶክመንተሪ ፊልም እያለ የሀገርን ታሪክ አበላሽቶ ክርስቲያኑ ከሙስሊሙ ለማጣላት የሚያደርገው እንቅስቃሴ ከመቼውም ግዜ  በላይ ሕዝቡ ነቅቶ ደርሶበታል።ነገ ደግሞ አክራሪ፣ ጽንፈኛ የሐይማኖት አባቶች ተነሱ ብሎ ዶክመንተሪ ፊልም አዘጋጅቶ አሸባሪ ለማለት የዳዳ መንግስት መሆኑን እናውቃለን!
 

የነጻነት ጉዞ መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ የለውም

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!
               ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment