Tuesday, April 21, 2015

ሰበር ዜና! ሰልፉ አዲስ አበባን ሲዞር ሊውል ነው! የኢቲቪ ጋዜጠኞች ተደበደቡ


rally-ethiopia
መንግስት ያሳየውን ቸልተኛነት ለመቃወም በአዲስ አበባ ህዝቡ ነቅሎ አደባባይ ወጥቷል።
‹‹ኢህአዴግ ሌባ ሌባ፣ ኢህአዴግ ሌባ ሌባ!››
‹‹ይለያል ዘንድሮ የኢህአዴግ ኑሮ! ይለያል ዘንድሮ የኢህአዴግ ኑሮ!..
ይለያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ!››
እያለ መፈክር እያሰማ ነው!
ከደቂቃዎች በፊት የኢቲቪ/ ኢብኮ ጋዜጠኞች በለቀስተኞች መደብደባቸው ተሰምቷል፡፡ የኢትቪ /ኢብኮ ጋዜጠኞች ለቅሶ ቤት ውስጥ ቀረጻ አድርገው ሲመለሱ ‹‹ሌቦች እናንተ ልታስተላልፉት አይደለም፡፡ ስለ እኛ ምን አገባችሁ?›› ተብለው እንደተደበደቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡

አሁን የደረሰን ዜና እንደሚያመለክተው ከተማ ውስጥ ማን እንደበተነው ያልታወቀ ነገ የስራ ማቆም አድማ እና ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ የሚጠይቅ ወረቀት ተበትኗል የሚል ወሬ እየተነገረ ነው፡፡ በየታክሲውና ከተማ ውስጥም መነጋገሪያ እንደሆነ ታውቋል!
ቀጥታ ዘገባውን ነገረ ኢትዮጵያ ፌስቡክ ይከታተሉ 
ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia

No comments:

Post a Comment