Friday, April 17, 2015

“ልማትን» የሚደግፉ, ቦንድ እንዲገዛ የሚቀሰቅሱም ሽብርተኛ እየተባሉ ነው – ግርማ ካሳ


“ሕግን» በመጥቀስ, ሕግን እንደ ዱላ በመጠቀም ዜጎች ላይ ግፍ እየተፈጸመ ነው. በፍትህ ስም, የሚፈጸም ግፍ ደግሞ ሞቴንስኪዮ የሕግ መንፈስ በሚል መጽሐፉ እንደጻፈው, የግፎች ሁሉ ግፍ ነው. ሞቴንስኪዮ “There is no greater tyranny than That wooden perpetrated under the shield of the law and in the name of justice.” ሲል ነበር የጻፈው.
ኢሕአዴግ በዋናነት ዜጎችን ለማሰር እየተጠቀመበት ያለው ሕግ የጸረ-ሽብርተኝነት ሕግ ተብሎ የሚጠቀሰው ሕግ ነው. በዚህ ሕግ መሰረት በሌሎች አገራት እንደምናየው በሕዝብ ላይ በተግባር ጥፋት የፈጸሙ, ወይንም ሊፈጸሙ ሲሉ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሽብርተኞ የታሰሩበት ሁኔታ የለም. ይህ ሕግ ሽብርተኞችን ለመወጋት ያለመ ሳይሆን, ሰላማዊ ዜጎች ላይ ያነጣጠረ ሕግ ነው. በዚህ ሕግ መሰረት ማንኛውም ዜጋ ማንኛውንም ነገር ካደረገ “ሽብርተኛ» ተብሎ ወደ ወህኒ መወርወር ይችላል. የታሰሩ ሰላማዊ ዜጎችን ማንነት, ምን ይሰሩ እንደነበረ በመመልከት ብቻ, የጸረ-ሽብርትኝነት ሕጉ መስመር እንደሳተ ማንም በቀላሉ ሊደመድም ይችላል.

አንድ ወጣት ኢትዮጵያያዊ በልማቱ ዙሪያ ከኢሕአዴግ ጎን የቆመ ነበር. የፖለቲካ ልዩነቶች እንደተጠበቁ, የኢሕአዴግ የልማት እንቅስቃሴዎች መደገፍ እንዳለባቸው መከራከር ጀመረ. በጸረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ከተከሰሱት ዉስጥ, በዉጭ ያለች ኢትዮጵያዊት, ሶሊያና ሽመለስ, ስለዚህ ወጣት ስታስታወስ “አሁን ያለው የኢኮኖሚ ፓሊሲ (የኢሕአዴግ) መካከለኛ ገቢ ያላቸው ዜጎችን ለመፍጠን በጣም ጥሩ መፍትሄ አንደሆነ እና እነዚህ ዜጎች በራሳቸው ጊዜ የዴሞክራሲን ጥያቄ ያነሳሉ ሲለኝ በንዴት አንዴት የመንግሰትን የኢኮኖሚ ፓሊሲ አፉን ሞልቶ እየደገፈ በዛው መጣን የመንግስት ተቺ ነኝ ይላል በሚል ግርምት ነበር የማየው »ስትል ጽፋለች. በአባይ ዙሪያ, ይህ ወጣት ዋና “የአባይ ቦንድ ግዢ እንቅስቃሴ አዝማች እንደነበረ, ሶሊያና ትናገራለች.
ይህ ወጣት ናትናኤል ፈለቀ ይባላል. ሽብርተኛ ተብሎ ከሌሎች ዞን ዘጠኞችና ከብዙዎች ሰላማዊ ዜጎችን ጋር በወህኒ እየማቀቀ ነው. አመት ሆነው. “ለኢህአዴግ የኢኮኖሚ ፓሊሲ እድል ሊሰጠው ይገባል ባዮ ናቲ, የአባይ ግድብን መዋጮን በፍቃደኝነት በፍቅር የሚያወራው ናቲ, ያለምንም ጥላቻ ትዊተር ላይ ከቴድሮስ አድሃኖም ጋር የሚወያየው ናቲ, ዛሬ በሽብር ህግ ፍርድ ቤት መዋል ከጀመረ እንድ አመት ሊሞላው ነው» ስትል ነው ሶሊያና በምሬትና በሐዘን በሰላማዊ ዜጎችን ላይ በፍትህ ስም የሚደረሰው ግፍ ያጋለጠችው.
ይሄንን የምጽፈው በአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የሚኖሩ በተለይም ኢሕአዴግን የሚደገፉ ሰዎች ልብ እንዲሉ ነው. በአገሪቷ የሚደረጉ የልማት እንቅስቃሴዎችን የሚደገፉ ሁሉ ሽብርተኛ ከተባሉ ታዲያ ማን ቀረ?
ጓደኞቹ እንደሚናገሩት ናትናኤል መኮንን ያመነበት ከመናገርና ከመጻፍ ወደ ኋላ የማይል ኢትዮጵያዊ ነው.ከጥላቻ ፖለቲካ የጸዳ, ዜጎችን, ድርጅቶችን በስራቸው የሚመዝን. ለኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን ዘመናዊና ምክንያታዊ ፖለቲካን የሚያራምድ. ሆኖም የዛሬይቱ የኢሕአዴግ ኢትዮጵያ ለነ ናትናኤል ፈለቀም ቦታ የላትም. አለ የሚባለው ሕግ, እነ ናትናኤል መኮንን መጠበቅ አልቻለም. የጸረ ሽብርተኝነት ሕጉ ቦምብ በእጃቸውይዘው, በደረታቸው ታጥቀው የሚዞሩትን ሳይሆን, እነ ናትናኤል ፈለቀን ነው እያደነ ያለው. ታዲያ እነ ናትናኤል ፈለቀን ወደ ወህኒ በወረወር ሥርዓት ማን ነው በሰላም የሚኖረው? አንድ ባለስልጣን በፈለገ ጊዜ, በቀጭን ትእዛዝ, መልካችንን አይቶ ስላልወደደ ብቻ ሊያሳስረን በሚችልባት አገር, ለቢስነሳች, ለቤታችን, ለስራችን ምንም አይነት የሕግ ዋስትና ማግኘት በማይቻልባት አገር, በዛሬይቷ የኢሕአዴግ ኢትዮጵያ እንዴት መኖር ይችላል?
እንግዲህ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ይችን ትመስላለች. ሕግ የሌለበት, ዳኛ የሌለባትት, ሕግ መንግስቱ የተረሳባት, አቤት የሚባልበት ቦታ የሌለባት አገር.
ናትናኤል ፈለቀ በፍርድ ቤት ወቅት “ሽብርተኛ ነህ ወይስ አይደለህም? »ትብሎ ጥፋተኛ መሆኑን ሲጠየቅ” ሽብርተኞቹ አሳሪዎቼ ናቸው »የሚል ምላሽ ነበር የሰጠው. ትክክል ተናገረ.
ኢሕአዴግ ዉስጥ ከመቶ የማይበልጡ, ከበስተጀርባ ያሉ “ማጅራት መችዎች» ናቸው አገሪቷን እያተራመሱ ያሉት. በኢሕአዴግ ዉስጥ ያሉ ሞደሬቶች በድርጅታቸው ስም እየተፈጸመ ያለውን አይን ያፈጠጠ ግፍና ሽብር በቶሎ ማስቆም ካልቻሉ, አገሪቷ ወደ ከፋ ደረጃ ነው የምትወድቀው. ኢሕአዴግ እየመሸበት ነው.የጸረ-ሽብርተኝነቱ ሕግ እስኪሻሻል ድረስ ሰስፔንድ (በሕግ ተግባራዊ እንዳይሆን) መደረግ አለበት.ፓርላማው ሕጉን ሰስፔንድ ካደረገ, ከነ እስክንደር ነጋ ጀምሮ በዚያ ሕግ የታሰሩ ሁሉ ወዲያዉኑ ይፈታሉ.የፖለቲካ መካረሩን የሚለዝብበት ሁኔታ ይፈጠራል. ምናልባት ሁላችንም እንደ ሕዝብ በጋራ ተያይዘን የምንቀጥልበት እድል ሊኖርም ይችላል.
ያ ካልሆነ ግን, የሚመጣውን ቀዉስ በማሰብ, “እግዚኦ» ከማለት ዉጭ የምለው አይኖረኝም.

No comments:

Post a Comment