Tuesday, April 7, 2015

በምስራቅ ጎጃም ዞን የምረጡን ቅስቀሳውን ይዞ የቀረበው የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጠመው


በምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ አማኑኤል ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የመምህራን ስብሰባ ላይ የምረጡን ቅስቀሳውን ይዞ የቀረበው የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጠመው፣
በደረሰን መረጃ መሰረት የማቻከል ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የኔነህ እና የወረዳው የትምህርት ዝሕፈት ቤት ሃላፊው አዲሱ የተባሉት በወረዳው እየተካሄደ በነበረው የመምህራን የርዕሳነ መምህራንና የሱፐርቫዘሮች ስብሰባ ላይ በአጀንዳነት የቀረበውን የትምህርት ጥራትና የውጤት ተኮር ግምገማ በመቀየር ወቅታዊ በሆነው ምርጫ ዙሪያ ላይነው መወያየት ያለብን በማለት እንዲቀየር ያቀረቡትን አዲስ አጀንዳ በመቃወም ከትምህርት ጽህፈት ቤት ሃላፊው በስተቀር የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አጀንዳውን ይዞ እንዲወጣ መደረጉን አስረድቷል፣


መምህራኑ አክለውም በወረዳችን በተደጋጋሚ የሚታየው የሰው ሞትን ያስከተለ መፈናቀል የመልካም አስተዳድር ችግር በመሆኑ መጀመሪያ አካሄድህን አስተካክል በአቅራቢያችን ከቤተሰቦቻችን በኢንቨስትመንት ስም የተነጠቀው የእርሻ መሬት መመልስ አለበት በማለት መቃወማቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል፣

No comments:

Post a Comment