Tuesday, April 7, 2015

የአማራ አርሶ አደሮች ገንዘባችንን ተቀማን አሉ

 ፎቶ ከማህደር
በአማራ ክልል በባህር ዳር ከተማ በብአዴን አመራሮች እና በግንባር ቀደም አርሶ አደሮቸ ላለፉት አምስት አመታት የወረቀት ፈብሪካ ለመገንባት በሚል ከተሸላሚ አርሶ አደሮች የተሰበሰበው በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ የት እንደገማ እንደማይታወቅ አርሶ አደሮች ተናግረዋል። ገንዘባቸው እንዲመለስልቸው ቢወተውቱም ምላሽ ማጣታቸውን ተናግረዋል።

በሰባተኛው የአርሶአደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች ስብሰባ ላይ የተገኘው ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው አርሶ አዶሮች “ከአምስት አመታት በፊት በሁለተኛው እና በሶስተኛው የአርሶ አደሮች በዓል ላይ በክልሉ ካቢኔ ጎትጓችነት የኢንዱስትሪ አክሲዩን ባለቤት ትሆናላችሁ በሚል ጥሪታችንን አሟጠን፣ ከ70ሺ ብር ጀምሮ በየአመቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ብናዋጣም እስካሁን ምንም ነገር ለማየት አልቻልም” ብለዋል።
ከስራ አሰፈፃሚው አቶ አለምነው መኮንን በተገኝ መረጃ መሰረት የአማራ ፐልፕ የወረቀት ፋብሪካን ለመገነባት ሙሉ በሙሉ ከተሸላሚ አርሶ አደሮቸ አክሲዩን እንዲዋጣ ተደርጎ ከ 21 ሚልዩን ብር በላይ ተሰብስቧል።

No comments:

Post a Comment