Tuesday, April 7, 2015

መስማት የተሳነው ኢትዮጵያዊ በቨርጂኒያ ፖሊስ ታሰረ



በቨርጂኒያ ሀገረ ግዛት ፣ በሬገን ብሄራዊ የአየር ማረፊያ ተርሚናል ውስጥ አብርሀም ዘመድአገኘሁ የተባለ፣ መስማት የተሳነው እና የጎዳና ተዳደሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ወንድማችን ምንም በማያውቀው እና ባልፈፀመው ወንጀል አይፓድ ሰርቀሀል በሚል በፖሊስ ተይዞ ለስድስ ሳምንታት በወይህኒ ቤት አሳልፏል።
አብርሀም ከተያዘበት ሰአት ጀምሮ ለሀያ አራት ሰዓታት በምን ምክንያት እንደታሰረ ካለማወቁም በተጨማሪ ያረፈበት የእስር ቦታ ( jail ) መስማት ለተሳናቸው የተዘጋጀ ባለመሆኑ ምክንያት በእስር ቤቱ ውስጥ ለእስረኞች ያዘጋጀውን የምግብ ሰአት መጠቆሚያ ደውል መስማት ባለመቻሉ በማረፊያ ቤት ውስጥ ምግብ በአግባቡ አለመብላቱ እና ለመብቱ ለመከራከር ጠበቃ ለማናገር እድል ማጣቱ ተጠቁሟል። ይህም አነጋጋሪ ክስተት ሆኖ ሰንብቷል። ምን ትላላችሁ ወገኖች?

No comments:

Post a Comment