Tuesday, April 21, 2015

ሀሙስ ሰላማዊ ሰልፍ እናደርጋለን

 በመላው ኢትዬጵያ የስራ ማቆም አድማ ይደረጋል፣ ታክሲዎች በህብረት ስራ ያቆማሉ።
በአዲስአበባ፣ በአዳማ፣ ባህርዳር፣ በጐንደር፣ በአምቦ፣ በወለጋ፣ በደብረብርሃን፣ በደሴ፣ በአርባምንጭ፣ በአዋሳ፣ በሁሉም ቦታዎች።
በዜጐቻችን ላይ በሊቢያ፣ በደቡብ አፍሪካ፣ በየመን፣ በተለያዮ አረብ ሃገራት እየተደረገ ያለውን እናወግዛለን። የቤተክርስቲያን አገልጋዬች መዘምራን፣ ዲያቆናት፣ ቀሳውስት በሙሉ ይመለከተናል የምትሉ በሙሉ ቢቻል የቤተክርስቲያን መዘምራን የዘማሪ ልብሳችሁን ለብሳችሁ ውጡ። ክርስቲያኑ ባጠቃላይ በሁሉም ቤተክርስቲያኖች እና አገልግሎት ቦታዎች ከጠዋቱ 8 ሰአት ይሰባሰብ ከዛ ጉዞ ወደ አደባባይ ይደረጋል።
መሀስሊም እህት እና ወንድሞችም በመስኪድ ይሰባሰባሉ ጉዞ ወደአደባባይ ያደርጋሉ አንድ ሆነን በአንድነት እናወግዛለን። መንግስት ቸልተኝነቱን እንደጀያቆም እንጠይቃን። የትኛውም የፓለቲካ አመራሮች እና አባላቶች በየተገኙበት ቦታ የማስተባበር ሰራ ይሰራሉ። ለአገራዊ ጉዳይ ፍቃድ ከመንግስት መጠየቅም አያስፈልገንም። እንደውም ይህንን ሰላማዊ ሰልፍ መንግስት መጥራት እና ማስተባበር ይገባው ነበር።
ሼር አድርጉት እና ለሁሉ ይዳረስ፣ ድምፃችን ይሰማ።

No comments:

Post a Comment