Friday, April 3, 2015

እራት ሳይኖር መብራት ምን ይሠራል?

የታላቁ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ሕዳሴ ግድብ
ብዙዎች እንደተለመደው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ እያሉ ይጠሩታል፡፡ ውስጥ አወቅ የሆኑ ጋዜጠኞች ግን በታላቁ እና ሕዳሴ መካከል ኤሌክትሪክ ማመንጫ የሚል ሀረግ በመጨመር ላይ ናቸው፡፡

‘ድሮ ውኃ ይጠጣ ነበር፤ አሁን ግን ልንበላው ነው፡፡’ የሚለው ተስፋ በተስፋነት ቀረ ማለት ነው፡፡ መቸም ኤሌክትሪክ አይበላም፡፡
አባቶቻችን ሲመርቁም ‘እራት እና መብራት አይንሳችሁ!’ ነበር የሚሉት፡፡ እኛም . . . .
መብራቱስ ግድ የለም፣ ከጨረቃ ጋራ ይገፋል ሌሊቱ
እኛን የከበደን፣ ያልበላ አንጀት ሲጮህ ማዳመጥ-መስማቱ፡፡
በማለት የአባቶቻችን ምርቃት እራትን ከመብራት እንዲያስቀድም አሳሰብነ፡፡ ከሰሞኑ የመርሁ ስምምነት ላይ የግብፁ መሪ( Al SISI የፕሬዜዳንቱ ስም ሲገለበጥ ISIS ይሆናል) እና ምን አሉ . . . ‘የኢትዮጵያ ልጆች በብርሃን የሚማሩበት፤ የግብፅ ልጆችም በልተው የሚያድሩበት . . .’ ዓይነት ንግግር ተናግረዋል፡፡ እኛ ኤሌክትሪክ እነሱ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሆነ ነገሩ፡፡ . . . . . የአባይን ውኃ ልንበላው ነው ስንል ልታዩት ነው/ኤሌክትሪክ ነው/ ተባልነ፡፡ እራት ሳይኖር መብራት ምን ይሠራል? እሳቱ

No comments:

Post a Comment