Monday, April 27, 2015

“ልጄ! እንኳን አንተ፤ እኔም ባልተወለድኩ!” – የንጎቻው

…. ስሙን ሞት ይጥራውና እንኳን በአንደበቴ በህሊናዬ ሲንከላወስ እጅጉን የሚኰሰኩሰኝ ያ! መናጢ፤አናጢ፤ ግምበኛ፤አትክልተኛ ነኝ’ ባይ ‘መጤ’ ‘የቀን ሠራተኛ’ ለካስ ዋናው ሙያው ‘የጨለማ ሠራተኛ’ ኖሮ ወያኔዎች ኢትዮጵያን ወረው መዲናንችንን ሲቆርጣጠሩ ይኸ ‘እንግዳ ሰው’ ከምንጊዜው እንደ እስስት ተቀያይሮ፤ የቀን ቱታውን አውልቆ፤ዪኒፎርሙን ጠርንቆ፤መትረየሱን ታጥቆ ሰፈራችንን ፊታውራሪ ሆኖ ሲያምሰን፤ ሲያተራምሰን ከረመ። አይ እኛ! ምንኛ ተላላዎች፤ሰው አማኞች፤ የዋሆችም ኖረናል።

ይባስ ብሎ ለሥራ ክብር ባላቸው የተከበሩ ጎረቤቶቻችንና የሰፈራችን አረጋዊያን፤ አባ ምንተስኖትና እማማ ገላኒ በትልቁ ግቢያቸው አስጠግተው እንዳቅሙ መጠነኛ ክፍል አከራይተው ቡናና፤ጠላ አብረው እየጠጡ፤ወሬ እየለጠጡ፤ዓመት ባል፤አውዳ ዓመት እንደ ዘመድ፤እንደ ሃገር ሰው የተገኘውን ሁሉ እኩል ተካፍለው፤ አክብረው ቢያኖሩት ‘ባለቀን’ ሆነና ለውለታቸው ምላሽ ግቢያቸውን በሙሉ ወርሶ እነርሱን ከከተማ ዳርቻ አልባሌ ቦታ ቀበሌ ቤት ጣላቸው። በዘመኑ ሰዎች ቋንቋ አፍ መፍታቱን ሲያስረግጠን ከጆሯችን አልፎ በአናታችን የገደል ማሚቶ እስኪያስተጋባ ያምቧርቅብን ጀመር። -[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—

No comments:

Post a Comment