Sunday, June 2, 2013

“አንለያይም አንለያይም… መቼም አንለያይም አንለያይም!”ሰላማዊ ሰልፉን በርካቶች እየተቀላቀሉት ጉዞው ቀጥሏል፡፡


መንግስታችን ይህንን ሰልፍ ዕውቅና የሰጠው ሰማያዊዎቹ በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ እንደዛቱት ያደርጉትና አልተኩስ ነገር እንግዳ አለ አላስር ነገር ስንቱን አስሬ ብሎ ሰግቶ መሆኑ ይጠረጠራል፡፡
የሆነ ሆኖ ዛሬ በመንግስት ዕውቅና ያገኘ የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡ ከቀበና አራትኪሎ ከአራት ኪሎ ደግሞ ፒያሳ የተሰላፊው ቁጥር እየጨመረ ወደ ኩባ አደባባይ እየተጓዙ ይገኛሉ፡፡
አንድ ወዳጄ እንዳወጋኝ መንግስት እስከዛሬ ድረስ በሚያደርጋቸው ሰልፎች ላይ ተማሪዎችን ከትምህርት ቤት አስወጥቶ ወደ ሰልፉ ያሰማራቸው ነበር፡፡ እንዳይቀሩም የስም ጥሪ እና ቁጥጥር ይደረጋል የቀረ ተማሪም ማርክ ይቀነስበታል፡፡
ዛሬ ሰማያዊ ፓርቲ ደግሞ ሰላማዊ ሰልፍ ሲጠራ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን በተለምዶሜካፕ ክላስእንደሚባለው በሰንበቱ ለትምህርት ጠርተዋቸዋል፡፡ ተማሪዎቹ እንዳቀሩም ሃምሳ ማርክ እንደሚሰጣቸው ተነግሯቸዋል፡፡
አንድ ጊዜ መንግስት የሆነ ሰልፍ ጠርቶ እኔም ስታድም ተገንቼ ነበር፡፡ በሰልፉ ላይ አንዲት ሴትዮን እናቴ የዚህ ሰልፍ አላማ ምንድነው ስላቸውእንጃ ልጄ አበሏ ትጠቅመኛለች ብዬ ነው ወጣሁት ስምጠሪው አንዴ ቢየኝ ወደቤቴ እመለስ ነበር ብለውኛል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ አበልም የለም ማርክም የለም፡፡ ሰዉ ግን አሁንም እየጎረፈ ነው፡፡
በዚህ ሰልፍ ላይ ጎልቶ ከወጣው ዜማ መካከል ሙስሊሙ ህብረተሰብ እና ሌላው በአንድ ድምፅአንለያይም አንለያይምመቼም አንለያይም አንለያይም!” እያሉ ያዜሙበት ይገኛል፡፡


No comments:

Post a Comment