አንድ ሰው የአፄ ቴወድሮስን ታሪካዊ ጀግንነትና ራዕይ ለመዘከር የግድ ጎንደር መወለድ የለበትም፥ አፄ ዮሐንስ ለሀገራቸዉ የከፈሉትን መስዋትነት ለማመን የግድ ትግራይ መወለድ የለበትም ፣የአፄ ምንሊክን የአድዋ ጀግነነት ለመመስከር ሽዋ መወለድ የግድ አይልም፣ የአብዲሳ አጋን ከኢትዮጵያ እስከ አዉሮጳ የዘለቀ አርበኝነት ለመቀበል ወለጋ መወለድ ወይም ኦሮሞ መሆን አያሻም:: የነበላይ ዘለቀ፣ አሉላ አባነጋ እና የሌሎችን ኢትዮጵያዉያን ጀግኖችን ታሪክ ለመቀበል የግድ እነሱ ከተገኙበት አካባቢ መወለድ አያስፈልግም ኢትዮጵያዊ መሆን በቂ ነው፤ ምክንያቱም እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ እና ያልተጠቀሱ ጀግኖች መስዋትነት የከፈሉት እና የተዋጉት ለሀገራቸው እንጂ ለአካባብያቸዉ እና ለብሄራቸዉ ነው የሚል የታሪክ ድርሳን እስካሁን አላየሁም ነገር ግን በዘመናችን የተንሸዋረረ የፖለቲካ መነፅር እያዩ እንደዚህ የሚያወሩና የሚያስቡ ሠወች ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም:: ከዚህ ላይ ታሪካዊ ሰዎች በተለይ መሪዎች ሰዉ እንደመሆናቸው መጠን በዘመናቸው የሰሩት ጥፋት ይኖራል ስለዚህ ጥንካሬአቸውን ማድነቅና መውሰድ ከድክመታቸውም መማር እንጅ በጎጠኝነት አስተሳሰብ ታጥሮ የጎጣችን እና የብሄራችን የሆነዉን ፍፁም እንደሆነ አድርጎ ማሞገስ የሌላዉን ምንም ቁም ነገር እንዳልሰራ ጥፋቱን እያጋነኑ ማራከስ እኛን ቢያስገምተን እንጂ እነሱ የሰሩትን ታሪክ አይቀይረዉም ::
ከሰብኣዊ
ከሰብኣዊ
No comments:
Post a Comment