Tuesday, June 11, 2013

«ኢትዮጵያ በዐባይ ወንዝ ላይ ግድብ፣ የሠራችው በማንአለብኝነት ነው ፣ ግብፅ አንድ ጠብታ ውሃ እንዲቀርባት አትፈልግም » – ጠ/ሚንስትር ሄሻም ከንዲል

ካይሮ፤ ግብጽና በማነጋገር ላይ ያለው የዐባይ ውሃ ጉዳይ

ካይሮ፤ ግብጽና በማነጋገር ላይ ያለው የዐባይ ውሃ ጉዳይ
የግብፅ ጠ/ሚንስትር ሄሻም ከንዲል ፤ ዛሬ ለሽግግሩ ፓርላማ ባሰሙት ንግግር፤ ኢትዮጵያ በዐባይ ወንዝ ላይ ግድብ፣ የሠራችው በማንአለብኝነት ነው ፣ ግብፅ አንድ ጠብታ ውሃ እንዲቀርባት አትፈልግም ማለታቸውን AP ዜና አገልግሎት አስታወቀ። ጠ/ሚንስትሩ ከዚህ ጋር በማያያዝ፤ በዲፕሎማሲ፤ በህግ በቴክኒካዊ ጉዳዮች ፣ ግድቡን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ጋር ለመደራደር ትጥራለች ማለታቸውም ተጠቅሷል።

AP ጠበብት ያላቸው ባለሙያዎች ፤ ኢትዮጵያ ግዙፉ ግድብ በሚመጡት 3 እስከ 5 ዓመታት ውሃ እንዲሞላ እስክታደርግ ድረስ ግብፅ 20 ከመቶ ያህል ውሃ ይጓደልባታል ማለታቸው ተጠቅሷል። ባለፈው ሳምንት ፣ የግብፅ ፖለቲከኞች፣ በቀጥታም ሆነ አማጽያንን በመደግፍ ግድቡን በአሻጥር ከጥቅም ውጭ ማድረግ የሚል ቃል በይፋ መናገራቸው ቁጣንን ያስከተለ ሲሆን ፤ ኢትዮጵያ ይፋ ማባራሪያ እንዲሰጣት መጠየቋ የሚታወስ ነው።
በሌላም በኩል ፣ የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሙሐመድ ከማል አምር፣
ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ የካይሮ መንግሥትን ተቃውሞ ችላ በማለት ኢትዮጵያ ገንብታዋለች ባሉት ግዙፍ ግድብ ላይ እንደሚነጋገሩ መግለጣቸውን ሮይተርስ ዜና አገልግሎት አስታወቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ 6,000 ሜጋዋት ኤልክትሪክ እንደሚያመነጭ የሚጠበቀውና ኢትዮጵያን በአፍሪቃ መሪ የኤልክትሪክ ኃይል ምንጭ አቅራቢ ሀገር እንድትሆን ያበቃል የተባለውን ግድብ ሥራ ፤ የኢትዮጵያና የግብፅ አዋሳኝ ሀገር ሱዳን የምትደግፍ መሆኗን አስታውቃለች። የሱዳን የማስታወቂያ ሚንስትር አህመድ ቤላል ኦስማን ካርቱም ውስጥ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ «ታላቁ የተሃድሶ ግድብ ለእኛ ሰፊ ጥቅም የሚሰጥ በረከት ነው »ማለታቸው ተጠቅሷል።
source DW.DE

No comments:

Post a Comment