Saturday, June 22, 2013

ኢትዮጵያ ዉስጥ ለምን ጠንካራ ተቋማት የሉንም?

ከማስተዋል
የአንድን ሀገር እድገትና ጥንካሬ የሚወስነው በሀገሪቱ ተቋማት ጥንካሬ ነው ለምሳሌ አሜሪካ ጠንካራ ሀገር ናት ስንል የሀገሪቱ ተቋማትን ጥንካሬ እየገለፅን ነው፤ የአፍሪካ ሃገራት ደካማ ናቸው ስንልም የተቋማቶቻቸዉን ደካማነት ነው :: ተቋም ማለት ደግሞ ህንፃዉና በዉስጡ ያለው ቁሳቁስ ብቻ ማለት አይደለም እንዲያዉም በዋናነት በተቋማቱ ዉስጥ የሚሰሩት ሰወች ብቃት እና ችሎታ ነው:: 
አለመታደል ሁኖ ሀገራችን ኢትዮጵያ ጠንካራ ተቁአማት የሏትም ለወደፊቱ እንዲኖረንም ከአሁኑ እየሰራን አይደለም :: ሌላዉ ቢቀር ባለፉት ዓመታት አስመዝግበነዋል እያልን የምንመፃደቅበት የኢኮኖሚ እድገት እንኩአን ባብዛኛዉ በኢትዮጵያውያን የተሰራ ሳይሆን በቻይና እና በሌሎች ሃገራት ተቁአማት የተገነባ ነው፤ ለምሳሌ አብዛኞቹ መንገዶች በቻይና ሁሉም የዉሃ ኃይል ማመንጫወቻችን በጣልያኑሳልኒ አዲሱ የዓባይ ድልድይ በጃፓን የተሰሩ ናቸው:: 

ኢትዮጵያ ጠንካራ ተቁአማት እንዳይኖሯት ያደረጉአት ኢትዮጵያዉያን በተፈጥሮአችን ደካማ ስለሆን አይደለም ነገር ግን ገዥወቻችን ተቁአማት እንዲመሩ የሚያደርጉትና በተቁአማቱ እንዲሰሩ የሚቀጠሩት ሰወች ባብዛኛዉ ችሎታ እና አቅም ያላቸው ሰወች ሳይሆን ለእነሱ ታማኝ የሆኑ አገልጋዮችን መሆኑ ነው:: ይህ ችግር ትናነት የነበረ ቢሆንም አሳዛኝ የሚያደርገው ዛሬም ይህ ችግር ተባብሶ መቀጠሉ ነው::
ኢትዮጵያ ዉስጥ በአሁኑ ስዓት አንድ ሰው ምን እንድሚሆን እና ምን እንደሚሰራ የሚወስነው ከችሎታዉ እና ከተማረው ትምህርት ይልቅ የዘር ሐረጉ እና አብዮታዊ ዲሞክራሲን አቀባበሉ ነው:: ለምን ከሃርቨርድ በከፍተኛ ማዕረግ አይመረቅም የተገኘበት አካባቢ እና የዘር ሐረጉእንደሚፈለገውካልሆነና አብዮታዊ ዲሞክራሲን ካልተጠመቀ በእርቀት ትምህርት 'አሳይመንት' ለሰው እያሰራ የዲግሪ እዉቀት የቀሰመ ሳይሆን የዲግሪ ወረቀት የተቀበለዉን አምጥተው አለቃው አድርገው አስስቀምጠውያስመሩታል ያስመርሩታል ጉዳዩን ሳስተዉለው አይናማን በእዉር መንገድ እንደማስመራት ነው:: የሀገሪቱ ሲቪል ሰርቪስ ተቁአማት አር(BPR) ቢባል ኤስ (BSC) መሻሻል የተሳናቸው አንዱና ዋናዉ ምክንያት ይሄ ነው "የአሳ ግማቱ ካናቱ" እንዲሉ :: ሌላዉ ቀርቶ በአሁኑ ስዓት የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ርዕሰ መምህር ለመሆን እና ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ አስተማሪ ሁኖ ለመቀጠር እንኩአን የፖለቲካ አመለካከት ዋናዉ መመዘኛ ሁኗል ( የመሐመድ ሳልማንየገጠር ዩኒቨርሲቲ መምህር ነኝአንብቧት እስኪ ) :: ታዲያ በዚህ ሁኔታ ምን አይነት ጠንካራ ተቁአም ልንገነባ እንችላለን
በችሎታ እና በብቃት የሚያምን መንግስት እስኪኖረን ድረስ በዚህ አያያዛችን አርባ እና ሃምሳ ዓመት በሁአላም መንገዶቻችን፣ የኃይል ማመንጫወቻችን፣ ድልድዮቻችን እና ሌሎችም ነጎሮች የሚገነቡት በራሳችን ስወችና ተቁአማት ሳይሆን በሌሎች ሃገራት እንደሚሆን ለመተንበይ ነብይ መሆን አያስፈልግም::

No comments:

Post a Comment