Saturday, June 8, 2013

በሞልዴ የኢሳት ገቢ ማሰባሰብያ ተደረገ ።

 በሞልዴ ኖርዌይ ለ ኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ ተደረገ


በኖርዌይ ሞልዴና በቪስትነስ የሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የተሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ ተደርጎ በመልካም ተጠናቀቀ።በሞልዴና በቪስትነስ የሚኖሩ ስደተኞች የኢሳት ገቢ  ማሰባሰቢያ በማዘጋጀት ያደረጉት ዝግጅት ላይ ከኦታ ፣ ከስቴንሻዬር  እንዲሁም ከተለያዩ ቦታዎች የተለያዩ ዜግነት ያላቸው ሰዎች የተገኙበት ሲሆን ከቀኑ 1ሰዓት30 ላይ ፕሮግራሙ የተጀመረ ሲሆን የተለያዩ ፕሮግራሞች የተደረጉ ሲሆን ከብሮግራሙ መካከል በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሚዲያ አፈና በተምነለከተ የተለያየ በመረጃ የተደገፈ ጹፎችን በማቅረብ ለታዳሚዎቹ አቅርበዋል። ከዛ በመቀጠልም የሃገራችንን ባህላዊ ምግቦች ለታዳሚዎች በማቅረብ እና የተለያዩ የሎተሪ ሺያጮችን በማድረግ የሳካ የኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ በደመቀ ሁኔታ እንዲካሄድ የበኩላቸውን አድርገዋል ። በፕሮግራሙ ላይ  ጋዜጠኛ አፍወርቅ አግደው በስካይፒ በቀጥታ ለታዳሚዎች በሃገራችንን ስላለው የሚዲያ አፈና ብሎ የነጻ ሚዲያ አስፈላጊነትን በማራኪ ሁኔታ አስተላልፈዋ። ከስፍራው የተገኙ ግለሰቦች ለኢሳት ያላቸውን አሌንታነት ደስ በሚል  ስሜት ገልጸዋል ። ከዚህ በተጨማሪ ብዙም የኢትዮጵያ ዜጎች በለሉበት የአለማችን ክፍሎች የገቢ ማሰባሰቢያ ማድረግ እንደሚችሉ አሳይተዋል ። ሙሉ ዘገባውን እንደደረሰን በሰፊው እናቀርባለን ።



No comments:

Post a Comment