Saturday, June 8, 2013

የሕዝብ ድሎች ሲመዘገቡ-ሲጣጣሙ፤

በቅድሚያ ድል ሲባል ምን አይነት ድሎች አሉ ብሎ ማስተዋሉ ተገቢ ነው። በመሰረቱ በትእግስት፤በመቻል፤በሰላም፤በዝምታ
የሚገኙ ድሎች አሉ። በትእግስት ዝም ብሎ ማስጨረስ ማሸነፍ ማለት ነው። ቀጥሎም ታግለው፤በሁለገብ አይነቱ ማለት ነው፤
የሚገኙ ድሎች አሉ። ከዚህም ባሻገር እነዚህ መንገዶች አላስኬድ ሲሉ በግፊት የሚመጡ በጦር የሚገኙ ድሎች አሉ። በየአይነቱም
አሽንፎ ማሸነፍ፤ተሸንፎም ማሸነፍ አለ። በተስተካከለ የትግል መስክ ማሸነፍና መሸነፍ፤ድል መንሳትና መነሳት አለ፤ባልተስተካከለ
መስክ ደግሞ አሸንፎ ማሸነፍ ተሸንፎ ማሸነፍም አለ።
እነዚህን መግቢያ ሓሳቦች ካስቀመጥን፤የኢትዮጵአ ሕዝብ ያለው የት ነው? የትኛው ምእራፍ ለይ ደርሷል? ድሎቹስ ምን ይመስላሉ
ብሎ ማስተዋልና መመርመር ለሚቀጥለው እርምጃ የሚበጅ ይሆናል።
የኢትዮጵአ ሕዝብ ታጋሽ ነው ሲባል በተግባር እንዳስመሰከረ የሓያ ሁለት አማታትን ውጣውረድ በትእግስት፤በመቻል፤በሰላም
በዝምታ መወጣቱና መዝለቁ በቂ ምስክር ነው። ይህን አስተዋይና አዋቂ ሕዝም የተገላቢጦሽ ትእግስቱን እንደ ፍረሀት፤አስተዋይነቱን
እደደሞኝነት፤ብስለቱን እነደድክመት ቆጥረቅ ለዘመናት መካራ ሲየዘንቡበት የቆዩትን ስርአት አንዳስቆጠረና አሁንም እየተደገሙ
ናቸው። እዚህ ላይ ሕዝቡ ባሳያቸው አስተዋይነትና ትእግስት በታሪክ ምእራፍ ቅድሚያ ቦታ ይዞ መጠቀስ ያለበት አይነተኛ ድል
ለመሆኑ አጠያያቂ አይሆንም። ባጭሩ ሕዝቡ በትእግስቱ በሰላማዊነቱና በአስተዋይነቱ ብዙ ድሎችን አስመዝግቧል። በወቅቱ-አሁንም።
“እሰኪ እንያቸው” አለ እንጂ-ለዘመናት ተከመሩብን አላለም። አሁን መከራው ትእግስቱን አሟጧታል። ትእግስቱም መጠን
ነበረውና።

በተለያየ ወቅት ህግ በፈቀደለት መንገድም ሆነ አመቺ ሁሊታዎች ሲፈጠሩ ባደረጋቸው ሁለገብ ትግሎች፤የሞቀ የቀዘቀዘ፤የጋለ
የተፋፋማ የለዘ በመሰለና የተለያዩ ሁሌታዎችን ባካተተ መልኩ ታግሏል እየታገለም ነው። የመብት ገደቡ እየተሸረሸረ፤መሰረታዊ
መብትና ነጻነለቱ በአጣብቂኝ ሕጎች አየተሻሩ ውጥረት ውስጥ ቢገባም ባመቸውና በተገኘው ቀዳዳ እየተጠቀመ ብዙ ምእራፎችን
አልፋል ተጉዟል። በዚህ ረገድ ድሎች ነበሩ? በእርግት ብዙና አይተኛ አንጸባራቂ የሚባሉ ድሎች ተመዝግበዋል። ማስተዋል
ሲታከልበት፤ የሕዝቡ ድሎች ድሎቹ፤የስርአቱ ሽንፈት ድሎቹ ናቸው። በየት በኩል አሸነፈ በየት በኩል በስርአቱ ድክመትና ሽነፍት
አሸነፈ የሚለውን ቀጥለን የምንመለከተው ይሆናል::
ለመጥቀስ የክል፤የጦር ድል በሶስተኛ ረድፍ የተጠቀሰው ትንሽ የተሸፋፈኑትን ሀቆች መገላለት ያስፈልገዋል። የጦር ድል ሲባል
የሚዋደቀው መስዋእትነቱን የሚከፍለውና እስከዛሬ የያይነቱን መስዋእትነት እየከፈለ ያለው ሕዝብ ነው ብለን ስናስቀምጥ ጉዳዩ
ይቀላል። ከጥንት ታሪኩ የውጭንም የውስጥንም ጠላት ያንበረከከ፤አሳፍሮና ድባቅ የመታ ሕዝብ እንጂ እከሌ አይደለም። እከሌ
በነበረበት እከሌ ጦሩን እየመራ በሌለበትም በራሱ የጎበዝ አለቃ ተደራጅቶ ማንነቱን ያስመሰከረ ሕዝብ ነው። መቸውም ጊዜ ቢሆን
ይጦር ባለድል ከበደ አበበ እከሌ ወይም ቡድን ሳይሆን ሕዝብ ነው። ሕዝብ አገር፤ህዝብ ጦር፤ሕዝብ መሪ፤ሕዘብ ሰራተኛ መሆኑን
ከተገነዘብን እስካሁን ለተገኙ ማንኛቸውም አይነት ድሎች ባለድሉ ህዝብ ነበረ፤አሁንም ነው። ደርግንም የጣለው ሕዝብ እንጂ፤
የወደቀው የተዋደቀው ሕዝብ የሕዝቡ ልጆች እንጂ አሁን እደሚለፈፈው በብልጣብልጥነት አኛ ብቻ የሚለው የተሳሳተ የተዛባን
የነጣቂ ቋዋንቋ ከቦታው ማስቀመጥ ተገቢ ነው። ጥያቄ አለ? አይመስልም። ድረጊቱም ቃላቱም ታሪክም ግልጽ ምስክር ናቸውና።
በዚህም ረገድ አሁን ፍልሚያን ማንሳት የዚህ ቀመር አላማ ባይሆንም ሕዝቡም ጦር፤የታጠቀውም ሕዝብ-የሕዝብ ልጆች ናቸው።
የቁጥር ነገር ሲነሳ ለኛኛው መደንበሪያ ነውና-አያምጣው ከመጠም የህዝብን ማንነት መገንዘብ ከከንቱ ቅዠት ያድናልና የህዝብን
በለድልነት በቦታው አንክሮ ማስቀመጡ ተገቢ ነው። ካያያዝ ይቀደዳለ ካነጋገር ይፈረዳል-ባግባቡ።የፖለቲካ ድሎች፤ 
በአገራችን ሁሉም ፖለቲከኛ ነው። ለምን ቢባል-ወዶም አይደል። ከሰላማዊ ኑሮው እያወኩ ወደ አምበጓሮ የሚያመሩት ስንኩል
መሪዎቹ ገፍተው ገፋፍተውት እንጂ ሕዝብ ሰላሙን እድገቱን የእለት ተእለት ኑሮውን ይሻል፤ካገኘም ፖለቲካውን ባላተኮረበት።
ሁሉም ፖለቲከኛ ቢሆን ሉሮውን የሚኖረው እርሱ፤በደልን የሚቀበል እርሱ፤ፈታና ውስጥ የገባ እርሱ። ፖለቲካ ኑሮ ነች፤ኑሮም
ፖለቲካን አመጣች፤ከሚኖረው ሕዝብ የበለጠ የሚያውቃት የለም-ስለዚሕም ፖለቲካውም ፖለቲከኛም መፍትሔውም ባለቤቱም
ሕአዝብ ነው። በዚህም ቢሉት በዚያም ሕዝብ የሌለበት ፖለቲካ የጥቅም ፖለቲካ ነው። ሕስብ ያልመራው ፖለቲካ የስልጣን ፖለቲካ
ነው። ሕዝብን ያላሳተፍ ፖለቲካ አላማ ቢስ ከንቱና ባዶ ፖለቲካ ነው።
ፖለቲካ የሕስብ አመራር ከሕዝብ በሕዝብ ለሕዝብ ነው-ዲሞክራሲ፤ማልካም አስተዳዳር። የቺ የፈረደባት ዲሞክራሲ እንደማናቸውም
በማንም በዘፈቀደ ተጠምዝዛና ቀለም ተቀብታ ብትመጣም ንጹህ መፍትሔ አይደለችም። እንኳን ተቀብታ ተቀባብታ ባትቀባም ንጹህ
መፍትሄ አልነበረችም አይደለችም። የ51ለ49 ዲሞክራሲ ማለት ነው። የቢቸግር ዲሞክራሲ። ሌላ የተሻለ ጠፍቶ። ለዚያውም 51ዱ
የጠማማው ሊሆን የሚችልበት ዲሞክራሲ። እንደእውነቱ እውነተኛ ዲሞገራሲ ሳትሸራረፍ ከላይ የተሰጠችው ሙሉዋ ነች። ሕግ-
ዲሞከራሲን መብትን ነጻነትንና ሰብእናን ይገድባል እንጂ፤ከሙሉው ያጎድላል እንጂ አይጨምርም። ሕግ ማሰሪያ ነው-በተለይ ደግሞ
ባልሆነ እጅ ሲገባ መቀፍደጃ ነው። ሕግን በሕግ ሽሮ ስርአተ አልበኝነት-ሌላ ምን ሊባል?
ሕዝብ መብቱን ለማስከበር ሕግ በፈቀደለት፤ተቆንጥሮ ተሰጠው ወይም በገፍ በምርጫ በተደጋጋሚ ተሳትፋል። ምንም ጥያቄ
በሌለበትና በማያወላዳ ሁኔታ በተደጋጋሚ ማንነነቱን አስመስክሯል አሸንፏል ድል ነስቷል። አጠበቡበትም ቀዳዳ ተገኘ በምርጫዎች
ድል ተጎናጽፏል። 2005 ትልቅ ድል። በ2010 99.6% ድል። ከላይ የስርአቱ ሽንፈት የሕዝቡ ድል ብለናልና። ተሳትፎም
ዝምብሎም አሸነፈ ድል ነሳ ነው። ስርአቱም ምርጫ የማያዋጣው መንገድ መሆኑን ተረድቷል፤ሕዝብም በሲህ ስርአት ከምርጫ
ምንም እንደማይጠብቅ 2010 አመዝግቧል። 
የዲሞከራሲና ሰብአዊ መብት፤ 
የኢትዮጵያ ሕዝብ መብት አለው ነጻነት አለው፤የዶሞክራሲና ሰብአዊ በብቱ ተከበረለት የሚል ቅዠት ውስጥ ማንም አይገባም።
የመብቱ መረገጥ መታሰሩ መሳደዱ መገደሉ መመዝበሩ ስርአቱ የሳያቸው ውድቀቶች ናቸው። ይህ የስርአቱ ውድቀት ሕዝብ ደግሞ
ባንጻሩ ስርቱን ወግድ ያለበት፤የአንዱ ውድቀት የአንዱ ድል ነውና የስርአቱን ተሸናፊነት በማያወላዳ መልኩ ያሳየበት ነው። ባጭሩ
ብቃት የለህም ልትመራን ልታስተዳድረን አልቻልክም በቃህ ያለበት መስክ ነው። ሥራህን አልሰራህም፤ሀላፊነትህን አልተወጣህም፤
ካላግባቡ ካለቦታህ በማይመጥንልህ በእብሪት ተኮፍሰሓል ነው የሚለው ሕዝቡ። በቀላሉ ተሸናፊነቱን አረጋጋጠለት። VerdictDemocracy, Human right not delivered
የኢኮኖሚ እድገትና ብልጽግና፤
አንድ አጎት የምንሆነው ሞገስ የሚባል ትንሽ ልጅ ጋዜጣውን ገልብጦ የነብ ነበረ። ያነበዋል! ባግራሞት ተመልክተን ሞገስ እንዴት
ነው የምታነበው ስንለው ገልብጦ ማንብብ እንደሚችል የሔደበት መሆኑን በተግባር አሳየን፤ገና ጠዋት ነበርና አቀናነው። ነፍሱን
ይማር በወጣትነቱ እርሱንም ተባራሪ ጥይት በላው። አሁንም እንደልጅ ሞገስ ገልብጠን ማየቱ የዚያኛውን ሽንፍተ ድል አድርጎ
መውሰዱ የትግሉ ውጤት፤በተግባርም ስርአቱን ለቦታው ተገቢ አይደነህም ለማለት የተወሰደ መሳሪያ ነው።የሙግት ነጥብ። ከዚህም
በመቀጠል ሞገስ ስንልም ይህንኑ ለማመልከት ነው።
በኢኮኖሚው፤የተባለው የእድገት አሓዝ፤የሕዝብን ኑሮ፤የአገርን ሕዝብ የአድገት ደረጃ አስመልክቶ ብዙ ተብሏል። መሰለቻቸት
አያስፈልግም። በዚህ ረገድ የእድገት መንግሥት ተብሎ ኪራይ ሰብሳቢነቱን ከዚህም አልፎ ድጥ መግባቱን ከራሳቸው አንደበትስንሰማ፤የሕዝብም ኑሮ በየእለቱ ሲያሽቅለቁልና መከራውን ሲዝቅ በአንጻሩ ተዝናነተው ሀብት አካብተው በድሎት የሚቀናጡት
ማንነት በግልጽ ሲታይ ለማና ለምን እንደቆሙ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ፋሲካም፤ሚሊኒየሙም በሕዝቡ አንደበት ምንም የለም-
ሲባል የሕዝብን አስተዋይነትንና የስርአቱን አባያነት የሳያል። አሁንም ሞገሥ እንደገለበጠው፤እኛም ድላችንን ገልብጠን ለማንበብ
እንገደዳለን። አይነተኛ የስርአቱ ሽንፈት። Verdict-Economic Development not delivered
ሙስናና ስርአቱ፤ 
የኢኮኖሚ እድገት ሲባል ማን አንዴት እንዳደገ፤የፍስፍና ለውጥ ተብሎ የርእዮተ አለም አመለካከት ለውጥ ተብሎ ካፒታሊዝምን
እንመሰርታተለን ተብሎ ማን ካፒታሊሰት እንደሆነ፤እኛ የምንለቀው ካፒታሊዝም ሲጠወልግ ነውም አንደተባለ-ወይ ጉድ፤ታዝበናል
ተገንዝበናል።
ለሰርአቱ ስሙ ተግባሩ ነው፤ብዙ ስሞች አሉት፤በመሆኑም ከራስ የበለጠ ምስክር የለምና የሙሰኛ ስርአት ሌላ ስም ሆኖት መገኝት
አይነተና ሽንፈት -የሕዝብን ድል ገልብጠን ለማንበብ እንገደዳለን። ሽንፈት የሽንፈት ሽንፈት። ሙሰኛ፤ወንጃይ፤አሳሪ፤ፈራጅ-ዳኛ፤
ፍርድ አስፈጻሚ ሆኖ ይዘልቃል? አያስኬድም አያዋጣም። በነገራችን ላይ ማን ተነክቶ ማን ሊቀር። ትልቁ አሳ ትንንሾቹን በልቶ
ሲጨርስ ሕዝቡ ትልቁንም የተረፉትንም። ትንንሾቹ አሳዎች ሲያልቁ ትልቁም አሳ የሚበላው ያጣል። እርቃንን ይቀራል። ይችም 
በአባይ አጀንዳ ተዋጠች በሉ። 
ይህ ሽንፈት ብቻ አይደለም፤የቆመበትን መሰረት ከመናድ ባሻገር ውርደት፤ቅሌት ያውም በሕዝብ በቴሌቪዥን ለዓለም። የትልልቁን
አሳ ጉድም ጊዜ ታሳየናለች። Verdict-System Corrupt.
የአገር ደህንነተና ሉአላዊነት፤
በእኛ አገር ያገር ሉአላዊነትና የህዝብ ደህንንት የሚመነዘረው በፖለቲካ ኪሳራ ወቅት ነው። የተነሱ ጦርነቶች አውዳሚ እልቂቶች
ወረራዎች ሁሉ የሕዘብን ደህንነት፤የአጋርን ሉአላዊነት ለማስከበርና ለመጠበቅ ሳይሆን በየወቅቱ ይነሱ የነበሩት የፒልቲካ ኪሳራዎችን
መሸፋኛ ማዳፈኛ ብሎም ማድበስበሻ ማፈኛና ማዘናጊያ ለጊዜው ለማምለጫ ተብለው የተቀየሱ እንጂ በቅን ለሕዝብ ላገር የታስቡ
አልነበሩም። በአብዛኛው ስርአቱ የፈለፈላቸው፤በሌላውም ተነድቶ እንደነበረ ስናስተውን ላገር ለሕዝብ የቆመ ስርአት አለመሆኑን
በውል እንገነዘባለን።
በሕዝብ ደህንነት ስም እልቂትና ኪሳራ፤ባገር ሉአላዊነትና ደህነት ፈንታ አገርን በይበልጥ አደጋ ውስጥ የሚጥሉ እርምጃዎች ሲወሰዱ
አዳጋውም በየእለቱ የባሰ እየናረ መምጣቱና አገር ሕዝብ ስጋት ውስጥ መግባቱ አሌ አይባልም። ይህም ትልቅ ሽንፈት-ሰርአቱ
ተረታ፤የሕዝብን ደህንነት ያገርን ሉአላዊነት ሊያመጣ ሊያስከብረ አልቻለም አደጋዎችን ጋበዘ እንጂ። የሞገስን ምሳሌ ለአንባቢው
ትተናል። Verdict-National security, Integrity-Not delivered
የሐር የሕዝብ አንድነት፤
እስከዘሬ በስርአቱ ደባ ሐዝብን አገርን በቋንቓ፤በዘር፤በእምነት በአካባቢና ባመችው ሁሉ እየከፋፋለ እያናቆረ ሲበትን የነበረውን ሴራ
ጥሶ ሕዝብ በበሰለ አመለካከት አንድነቱን መጠበቆ ማስከበሩ ትልቁ ድል ተብሎ መጠቀስ ያለበት ሀቅ ነው። ምንም እንኳ በተወሰነ
ደረጃ ይህ የመሰሪ አከሄድ አገርን ወደብ አልባ የእልቂትና የመታመሰ ብሎም ሕዝብን አደንቁሮ ሁዋለ ቀር ማድረጉ ቢሳካለትም-
እነደ መሰሪ አካሄዱ አገር አልነበረችም ሕዝብም በአንድንተ ተከባብሮ አብሮ በሰላም፤ባንጻሩ፤ አይኖርም ነበር። ሕዝብ አንድነቱን
ማስከበር በፍቅር መቻቻል መጽናት ብቻ ሳይሆን ባደባባይ የጥፋት ሂደቱን “አንለያይም” ብሎ በአደባባይ መልእክቱን ለጠላትም
ለወዳጅም አስተላልፏል። በመሰሪነት ላይ የተገኘ አይነተኛ ድል።ሕገ መንግሥትና መብቶች፤
የአገራችን ሕዝብ ሲተርት፤ባለቤት ያቀለለውን አሞሌ ባለዳ አይቀበለውም ይላል። ሕገመንግሥት የሚቀረጸው የሁሉም የበላይ ሆኖ
ሁሉም በሕግ ፊት እኩል የሚሆንበትን ስርአተ መስተዳድር ለማስመር ነው። ሕጉን ያወጣው ካላከበረው ሕዝብ ምን እዳ ግድ አለበት?
እኔ ባለስልጣን አንተን ልሰልጥንብህ ማለት ከንጉሥ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ የቅርብ ሩቅ ጊዜ ትዝታ ልዩለቱ ምኑ ላይ ነው?
በእርግጥ ሕግ ላወጣው ይበጃል የሚባለው ለሕዝብ ላልቆመ ስርአት ብቻ ነው። የዲሞከራሲ የሰብአዊና ሌሎችም መብቶች በአግባቡ
ተቀምጠውበታል በሚባል ሰርአት ሕግን የማያከብር ወንጀለኛ ነው። ስርአቱ ከተጀመረ ጀምሮ ሕግ ሲጥስ፤የጣሰውን ሕግ ሕዝቡን
አክብሩ ብሎ ሲወነጅል ሲየስር ሲፈታ ሲገል ሲየሳድድ መክረሙ ወንጀለኛ ያደርገዋል። የሕዝብ ቋንቋ-መጀመሪያ አንተ በመልካም
አርአያነት ሕጉን አክብርና ለሕገመንግሥቱ ታማኝነትህን አሳየን፤ከዚያ እኛም እናከብራለን ነው። የተገላቢጦሽ አንተ ያላከበርከውን
ሕግ አኛን አክብሩ ለማለት ቀድሞ አንተስ ማነህ? የህንንስ ከሕግ በላይ መሆን ስልጣን ማን ሰጠህ-ወግድ ነው። በምግባሩ
የሚያስተምር ሕዝብ ይህ ነው። ድሉም ይመዝገብለት። Verdict-Respect for the constitution and the law--Not 
delivered 
ወደፊት እርምጃና ትልም፤ 
እድገት ብሎ ገዳማትን መገልበጥ፤ልማት ብሎ አገርን ለአመታት ውል በነጻ ማስረከብ፤ለፖሊቲካ ትረፍ ተብሎ ያገሪቱን ለም መሬት
ለባእድ ለጎረቤት አገር ማስረከብ፤አሁን ደግሞ መዘዘዙ የሰፋ የከፋ የግድብ ሙግት ምን ላይ እንደደረሰ ስናስተውል፤ህልምና ቅዠት
ተደባልቆ፤መልከም ካጥፊ ሂደት ተመሰቃቅሎ ሕዝብን ውዥንብር ውስጥ መክትተ አደገኛ አረማማድ ብቻ ሳይሆን ጤነኛ
አስተሳሳብም አይደለም። ይህ ለስርአቱ ትልቅ ሽንፈት ነው።ሞገስ።
በዚህ አይነት ነገ ምን ይዘ ትመጣለች ቢባል-አዳጋ። ሌላ ተአምር መጠበቅ ሞኝነት ነው። እንኳን ሕዝብን አገርን የሚያክል አብይ
ጉዳይ ቀርቶ ከበሮ እንኳን ካለተገቢዋ አትደለቅም። በአንዲት የተለመደች የጥንት መስተዋት አይነት ግጥም እናጠቃል፦
ድል ነው እንዳይሉ ድል የለ በጃቸው፤
እንግዛ እንዳይሉ ሕዝብ አንቢኝ አላቸው፤
ሕዝብ አመጸባቸው፤
እንምራ እንዳይሉ ጥበብ ጎደላቸው፤
እድገት እንዳይሉ ሙስና በላቸው፤
ከንግዲህ ሰዎቹ እረ ምን በጃቸው፤
ምን ይናገር ይሆን ያ-አንደበታቸው፤
ወንበሩን ይለቀቁ አለቀ ጊዜአቸው፤
በጌዜ በጊዜ ሳይበዛ ፍዳቸው፤
ሕዝብ ተቆጥቷል እሳት ሳይበላቸው።ሕዝብ በከንቱ አልታገሰም፤ለከንቱ አልታገለም፤ካሁን በፊት በተለያየ ወቅት በተለያዩ አገላለጾች፤እንደሞገስም ገልብጦ በማንብበ
ብቻም ሳይሆን በተገቢው የሕዝብን በትእግስት ማስጨረስ፤ታግሎ ማሸነፉን የስርአቱን መሸነፍና መፈናፈኛ ማጣት፤ስርአቱን -ጊዜም
ሁኔታዎችም ሕዝብም ዓለምም እየከዱት መሆኑ ተዘግበዋል። እንደታሰበውም እውን የተባለው ሁኑ ሰምሮ ሕዝብ ፍላጎቶቹ ቢሟሉ፤
ቢያድግ፤አገር ብትበለጽግ፤ሰለም ነጻነት ፍትህና መብቱ ተከብሮ ሁሉም ኑሮውን ደስ ብሎት ቢኖር የህዝብ ድን ድል፤የስርአቱ
ሽንፈት የሕዝብ ድል ተብሎ የሚወሰድበት ደራጃም ባልተደረስን ነበር። ብዙ መስዋእትነት ተከፍሏል ሰለዚህ በተገኙት ድሎች 
እንጸናለን።
በሕዝብ ልጀች ረገድም ያደረጃጀት ስልቶች እየተጠናከሩ፤በየመስኩ በመገናኛ የሕዝብ አይናና ጆሮ ሆነው ትክክለኛ ሚዛናዊ ሀቀኛ
ዜናና መራጃዎችን በመቅረብ በተለያዩ አውታሮብ በበሰለ አመለካከት እየታገሉ ለአመራር ብቃት አንዳላቸው ያስመሰከሯችው፤
ያከሸፏቸው የስርአቱ መሰሪ ሴራዎች በራሳቸው ሰፋ ያለ መድረክ የሚጠይቁ ድሎች ናችው።
አንድ ነገር እውነትና ግልጽ ሆኖ እየመጣ መሆኑ ይጤናል። ሕዝቡ ይህን ሁሉ ድል አስመዝግቦ፤ስርአቱም ይህን ሁሉ ሽንፈትና ጉድ
ታቅፍ መንበረ ስልጣን የሙጥን ማለት መልእክቱ አንደና አንድ ነው። ባንክሮ-የጥቅም ጉዳይ፤የህልውና ጉዳይ ሆኖ ወንበር በለስላሴ
አንደማትረካካብ ግፊት ጫና የመረረ የተባበረ ቀጣይነት ያለው ትግል-በያይነቱ እንደሚያስፈልግና ለዚህም መተባባር አይነተኛ
መፍትሄ መሆኑን ነው። የቀረው መንበራ ስልጣን ብቻ-በዋዛም እንዳልሆነች ያሰተውሏል። ድሎች በያይነቱ ተጠናቀዋል።
መደማመጥ፤የአንዱ በደል የሁሉም፤የአንዱ ጩኸት የሁሉም ሲሆን የፈጠነ የመጨራሻ ድል ይገኛል የሕዝብም የመከራ ጊዜ
ያጥራል።
ድል ምንጊዜም የሕዝብ ነው!
ኢትዮጵያ በጠንካራ ታጋሽ ሕዝቧና በእግዚአብሔት ተጠብቃ ለዘላለም ትኑር።
ፍ.አ
06/07/ 20013

No comments:

Post a Comment