Thursday, June 6, 2013

የፌስቡክ አብዮተኞች ከየት?


ይኸውላችሁ መንግስታችን ስጋት ላይ ነውበፍጹም አትስጋ! ኢትዮጵያውን በፌስቡክ
አብዮት ያነሳሉ፣ ጐዳናውን በአመጽ ያሸብሩታል ብለህ በአስቂኝ የቀትር ብርድ እራስህን አትምታ፡፡አብዛኛውየፌስቡክ ተጠቃሚ ኢትዮጵያዊ ያንተ ቢጤ ነው። የፌስቡክን ጥቅም በቅጡ አልተረዳም፡፡
ምናልባትም የጅንጀና አብዮት፣ የሽሙጥ አብዮት፣ የወሲብ አብዮት፣ 
የስድብ አብዮት ወዘተ ከቀሰቀሰ እንጂ የፖለቲካውንስ ነገር ተወው!
(ያውም የኢትዮጵያ?)

ኢህአዴግየምሬን ነው የምነግርህ፡፡ ከፈለግህ እገሌ እባላለሁ ብለህ
ቆንጅዬየአራዳ ስም ለራስህ ስጥና (ዴቭ፣ ናሂ፣ ኤቢ፣ ጃ፣ . . 

ምናምል ልትለው ትችላለህ) ካውንት ክፈት። ከዚያም የአንድ ሸበላ 
ጐረምሳ (ፀጉሩን ፈረዝረዝ ያደረገ) ፎቶ ፈላልግናኘሮፋይል 
ፒክቸር.. አድርገው፡፡ ከዚያ ቢያንስ 1000 ለሚሆኑ የሃገርህ 
የፌስቡክ ተጠቃሚዎች .. “ፍሬንድ ሪኩዌስትላክላቸው፡፡ ያው
ያልተፃፈው የሃገራችን የፌስቡክ ህግና ደንብ እንደሚያዘው፤ አንድ
እንደ አንተ ያለ ሸበላ ኢትዮጵያዊ የፌስቡክ ተጠቃሚ፤ 90 በመቶ
ጓደኞቹ ሴቶች መሆን አለባቸው፡፡ እናምፍሬንድ 
ሪኩዌስትከምትልክላቸው 1000 ሰዎች 900ዎቹ ሴቶች 
እንደሚሆኑ አትጠራጠር፡፡ መቶ ወንድ አይበቃህም? 
(
ያውም ከተገኘ ነው) ከዚያ በኋላ በቃ ቻትህን ማጧጧፍ ነው።

በተአምረኛው የፌስቡክ 
መስኮት በኩል 20 እና 30 የሃገርህ ልጃገረዶች ጋር በአማር-ላቲኖ
(
በላቲን በሚፃፍ አማርኛ) አሊያም በዝርክርክ እንግሊዝኛ
ጨዋታህን ማድራት ነው፡፡ ስልክ ቁጥር መለዋወጥ፣ ኬክ ቤት መቀጣጠር በሃሜት መቦጫጨቅ፣ ተረብ መወራወር፡፡
ደሞም አትርሳ በሞቀው የቻት ወግህ ከልጃገረዶቹ ጐን ለጐን በሰፊው
ዎል ላይ ልጆች የሚያስቁ ፎቶዎችን በብዛት ፖስት አድርግ፡፡
ወዲያው መአት ኮሜንቶች ይጐርፉልሃል፡፡ ትደነቃለህ፣ ትሞገሳለህ፡፡
ፖስት ያደረካቸው ፎቶዎች እኮ ምን አይነት መሰሉህየአርሰናሉ
አሰልጣኝ የሙሽሪትን ቬሎ ለብሰው፣ የማንቼው ደግሞ በሙሉ ሱፍ
አጊጠው በሰርግ ሲጋቡ፣ ሮኒ ቫንበርሲን እንደህፃን አዝሎት፣ 
ቴዲ አፍሮ እጮኛውን ቀና ብሎ ሲያያት ወዘተአይነት ናቸው፡፡
ኢህአዴግ ሆይይሄ ትውልድ የትኛውን መንበርህን ይሆን
በአብዮት የሚያንቀጠቅጠው?
ግድየለህም ኢህአዴግ እመነኝ አብዛኛው የሃገርህ የፌስቡክ
ተጠቃሚ ..አብዮተኛ.. የሚባል ከባድ ስም የሚሰጠው አይነት
አይደለም፡፡ ዘርፈ ብዙውን የፌስቡክ ቴክኖሎጂ፣ ሁነኛ የመረጃ እና
የእውቀት ማእድ የሆነውን ገበታ፣ ኢትዮጵያውያን ደንበኞቹ 
እንደ ጉድ እያሰቃዩት ነው፡፡አቢዩዝእያደረጉት ነው፡፡
ግን ልብ በል ወያኔ!
እስከአሁን የሰነዘርኩት ወቀሳ አብዛኞቹን እንጂ ሁሉንም 
ኢትዮጵያዊ የፌስቡክ ደንበኞች አያጠቃልልም፡፡ በፍፁም!
ጥቂቶች አሉ- ፌስቡክ የገባቸው፡፡ ድንቅ የመረጃ ምንጭ
የሆናቸው፡፡ ለእነዚህ ሰዎች ፌስቡክ እና ሌሎች ማህበራዊ 
ድረ-ገጾች የእውቀት የመረጃ ገበያ ናቸው፡፡ 
ይሰጡባቸዋል። ይቀበሉባቸዋል፡፡ ቁምነገረኛ ወዳጅ
ያፈሩባቸዋል፡፡ የባህል ማስተዋወቂያ፣ የፍልስፍና መሞገቻ፣
የፖለቲካ መከራከሪያ መድረካቸውም ነው፡፡
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment