Friday, June 14, 2013

ሕዝብን ለጦረነት አገርን ለጥቃት አሳልፎ ከሚስጥ ጋር መተባባር አገራዊ [ብሔራዊ] ወንጀል ነው።


የአንድ አምባ ገነን ሥራዓት ማንንት ባሕርይም ሆነ ተግባር ሊታይና ሊገመገም የሚገባው ሥራአቱ በአገሪቱና በዜጎች ላይ ከሚፈጽመው ብሔራዊ ወንጀልና ከሚያደርስው አገራዊ ጉዳት አኩያ ነው።
እንደሚታወቅው ወያኔ  ከአፈጣጠሩ ጀምሮ በካሃዲ በጸረ ኢትዮጵያውያን የመንደር ስብስቦች ጥላቻ ተረግዞ፤ በግራ ቀደም ፖለቲካ ስንኩል ትርኪምርኪ አመለካከት ተጠምቆ ወንድሞቹን ሲያርድ ሲያሳረድ የኖረ፤ የአባቶቹን የእናቶቹን የአያቶቹን የወንድሞቹን የልጆቹን የዘመዶቹን በርሃብ ማለቅ ግድ ያላለው፣ የማይለው፣ ስብዓዊነት የማይስማው፣ ለርሃብተኞች የመጣውን እርዳታ ቀምቶ ከሱዳን እስከ ሊቢያ ሲቸረችር የኖረ የኢትዮጵያን ታሪካዊ ማንነቷን ሕልውናዋን ስንደቃላማዋን የካደ፤  አገር አስገንጣይ፤  በኢትዮጵያ ጠላቶች ያደገ የተመነደገ አገርና ሕዝብን ዘርፎ የሚያዘርፍ፤  በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነ ግን አጥፍቶ ጠፊ መሰሪ፤  በፋሽቱ ቪኒቶ ሞሶሎኒ የከፋፍለህ ግዛ አስተምህሮ፤  በሂትለርና በስታሊን የድርጅታዊ የፕሮፓጋንዳና ቅስቀሳ ብሂሎችን እራሱን የካነ፤ እራሱ ደንቁሮ አገርንና ሕዝብን፤ የሚያደነቁር፤ የሃገሪቱን ዋና ዋና መሠረታዊ መንግስታዊ መዋቅሮችን በቁጥጥር ስር አድረጎ በአባሪ ተባባሪዎቹ የሆድ አደር አጋሰስ አጋርነት፤ በባእድ አገር የፖለቲካና የገንዘብ ለጋሲነት እርዳታ ብድር ሰጭነት፤ አማካሪነት እየታገዘ፤ ሕዝብን ሃገርን በንቅዘት በምዝበራ አደህይቶ አገርን ለመበታተን ቆርጦ የተነሳ እኩይ ስብስብ ለመሆኑ፤ ከሆድ አደሮቹ፣ከአባሪ ተባባሪዎቹ በስተቀር ማንም ኢትዮጵያዊ በጥሞና የሚያውቀው ማስረጃዎች በዋቪነት የያዙት፤ በታሪክ መሓደር ተረቆ ያለ የማይታበል ሃቅ ነው


የተዚህ ቀደሙ ወንጀል ሳያንስ ዛሬ ደግሞ ወያኔ በቡኅ ላይ ቆረቆር
 ሆኖ ሕዝብን ለጦርነት፤ ሀገርን ለጥቃት ለማዘጋጀትህዳሴ ግድብ በሚለው ማታለያ፣ በአድርባይ ሆድ አደር ጠርናፊ አስጠርናፊ ስብስብ አቀንቃኝ  ሊቀመኩዋሶች ታዳሚዎች  እየታጀበ
ግብጽን እየተነኮስና እየቀሰቀስ በመቀጠሉየአባይ ውሀ አንድም ጠብታ አይቀነሰብኝም ከምትለው ከስግብግቧ ግብጽ ጋር ጦርነትንእየጋበዘን ነው።

አገራችን ኢትዮጵያና ሌሎች ሀገሮች በነጭና ጥቁር አባይ የመጠቀም መብታቸው የተጠበቀ መሆኑ አያክራክርም ።በአለም አቀፍ ህግ መሰረትም ሌሎች ከወንዞቹ ተጠቃሚ ሀገሮች ውሃ እንዳያገኙ ማድረግ የሚፈቀድ አይደለም። አባይን በተመለከተተንኮለኛው አጋብሶ አደር የእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ሱዳንና ግብጽን ብቻ ይዞ የወሰነው የውሀ ድርሻ/ክፍፍል ትክክለኛ አለመሆኑምአከራራክሪ ኣይደለም-- ግብጽና ሱዳን አሌ ቢሉም። ግብጽ በረሀዋን ልታለማና ሚሊዮኖችን ልታሰፍር በመፈለግ የአባይን ውሀበተጨማሪ ደረጃ መፈለጓና የተፋሰስ ሀገሮችን ጥቅም ከቶም አላዳምጥ ማለቷም የሚደገፍ አይደለም  ወያኔ በአሁኑ ጊዜ ትልቅግድብ በሌለ ገንዘብ እሰራለሁ ብሎ የተነሳው ለኢትዮጵያ አስቦ (ወያኔና የኢትዮጵያ ጥቅም ሆድና ጀርባ ናቸውናሳይሆን የሕዝባዊአመጽ ነፋስ ወደ ሀገራችንም እንዳይነፍስ በሚል የህዝብን እይታ ለማደናገር የሸረበው ተንኮል መሆኑ ክርክርን አይጠይቅም ።በኢትዮጵያ እስከዛሬ የተሰሩት ግድቦችና ገና ያላለቀው ግልገል ጊቤ ቁጥር ሶስትንም ጨምሮ ለሀገሪቷ የመብራት ሀይል ፍጆታ ከበቂበላይ ሆነው ሳለ ዛሬም በብዙ ከተሞች መብራት በፈረቃ እየተሰጠ እንዳለ ሕዝባችን የሚያውቀው ነው። ግዙፍ ግድብ ለመገንባትመነሳትና ይህንንም ግብጽ እንደምትቃወም እየታወቀ በስልት ጉዳዩን በመያዝ ፈንታ ድንፋታና ፕሮፓጋንዳን ማስቀደሙ፤ ቦንድ ብሎሕዝብን ማስጨነቁና ማስገደዱ፤ ሀገር ወዳድ መስሎ ለመቅረብ መፍጨርጨሩ ሕዝብን ሊያደናግር የሚችል አይደለም።የለመዳባቸው የወያኔ የገደል ማሚቴዎችና አደናጋሪዎች --በባድሜ ጦርነት እንዳየነው ሁሉ-- ሀገር ልትጠቃ ነው ኡኡ በሚል ወያኔን በመታገል ፈንታ ሕዝብ እንዲደግፍና ከጎኑ እንዲሰለፍ ለማድረግ ከወዲሁ የተንኮል ቅስቀሳ፤የማደራጀት ስራና ጫጫታ ጀምረዋል።ሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጋ ይህንን በሚገባ ተገንዝቦ ውጉዝ ከመ አርዮስ መባል አለባቸው።

የግብጽ ሕዝብ ጠላታችን አይደለም። አንዋር ሳዳት የአባይ ወንዝ ከተገደበብን ጦርነት የግድ ይሆናል ያለውንምአንረሳውም--ዛሬም የግብጽ መሪ ተመሳሳይ አቅዋም በመውሰድ እሱም በበኩሉ ልክ እንደ ወያኔ ውስጣዊ ውጥረቱን ዘወር ለማድረግይፈልጋል። ተጨባጭ ሁኔታውንና አቅምን ሳያውቁ ሳይመዝኑ ህዳሴ ግድብ ይሰራል ብለው ጫጫታ ላይ ያሉት ክፍሎች ቅዠት ላይናቸው 
ከግብጽ ጋር ጦርነት ቢነሳ ይህ የኢትዮጵያ ሳይሆን የወያኔ ነው። ልክ እንደ ባድሜ። 130  ዜጋ አልቆ ምን ተገኘ ? ወያኔናአጫፋሪዎቹ--አንዳንዶቹ ደግሞ ተቃዋሚ ነን ሊሉም ኢትዮጵያ በአባይ ልትጠቀም ስትነሳ በግብጽ ተጠቃች ወይም ልትጠቃ ነው በሚል ሀገር ወዳድ ሁሉ ተነሳ ለማለትና ለማደናገር አቅደዋል። የሚሞኝላቸው አይኖርም ማለትም አይቻልም። ለነገሩ ግብጽ ኢትዮጵያን ሊወር አይችልም-- አይሮጵላኖች አስነስቶ ግድብ ተብየውን ሊደበድብ ይችላል። የሚያቆመውም አይኖርም ዕድሜ ለወያኔ ስንት ሚሊዮን ብር የፈሰሰበትን አየር ሃይል በትኖ በጀሌዎቹ ሞልቶት ይቀልዳል። መካላከያ ተብየው ሆኖ ሕዝብንም ከፋፍሎና አሽመድምዶ ይገኛል

ኢትዮጵያ መብቷን ለማስከበር አቅም የላትም። ወያኔ የአሜሪካ ሎሌና ተገዢ ነው-- አሜሪካ ደግሞ ግጭት ከተነሳ ግብጽን መቃወም ኣንችልም/ ብላ ለወያኔ አስጠንቅቃለች። የወያኔ አገዛዝ ከድጡ ወደ ማጡ ሊከተን ነው እየጣረ ያለው። ይህን መቃወም ደግሞ ለሀገራችን ደህንነት ወሳኝ ነውና ወያኔና ቅጥረኞቹን ወግዱ እረፉ ማለት ግድ ነው።ዛሬ ባለንበት ሁኔታ ከግብጽ ጋር ግጭቱ ለኢትዮጵያ የሚጠቅማት አይደለም። የኢትዮጵያ መንግሥት የለም አገርም በመንግስት ስም የሚገዙዋት ሕዝብን ለጦረነት አገርን ለጥቃት አሳልፎ የስጠ የሚሰጥ በአገራዊ [በብሔራዊ] ክህደት ወንጀለ የሚጠየቅ የወያኔ ስብስብና ተባባሪዎጩ ናቸው። 

ወያኔ ስልጣን ሲይዝ ከግብጽ ጋር ተፈራርሞ የሀገርን ጥቅም መሽጡንም መርሳት አንችልም። ወያኔ ጫካ ሳለም በግብጽ መረዳቱንና የተከዜ ድልድይን ሊያፈርስ መሞከሩንም የምንረሳው አይደለም። ወያኔ ከስረ መሰረቱ ፀረ ኢትዮጵያዊጥላቻን መስረት በማድረግ ከባንዳ አያቱና፤  አባቱ፤  ዘመድ አዝማዶቹ፤  የባኤላ አሹቅ እየቃመ፤ቂጣ እየገመጠ፤በለስ እየጋጠ፤ ጥሕሎ እየዋጠ፤  እሳት ዳር ተኮልኩሎ፤  በባላባታዊ የስልጣን ትንንቅ አባዜ የወደቁ ለጠላት ያደሩ ቅድመ አያቶቹ፤ አባቶቹ  ያወረሱትን ቂም በቀል የጎሳ ጥላቻ አፈታሪክ አንግቦ፤ በስነልቦና የበታችነት ማንነት በሽታ ተጠምዶ ያደገበትን ማንነት ባሕሪ መሰረት በማድረግ፤ኢትዮጵያ የቅኝ ገዥ አገር ናት፤ ትግሬን ነፃ አገር እናደርጋለን፤ትግሬ ለትግራዊ  የሚል ፋሽታዊ ብሂል አንገቦ ፈጣሪውን ሻቢያን ተገን አድርጎ በባእዳን አገራት አጋርነት አደራጅነት አማካሪነት የፖለቲካና የዲፕሎማቲክ፣ የእርዳታ ገንዘብ ለጋሲነት፤ በወገን ደም ሰክሮ ስልጣንን በመጨበጥ፤ የኢትዮጵያ ታሪክ የመቶ አመት ታሪክ ነው በሚል ጸረ ኢትዮጵያዊነት ቅዥት ውስጥ ተዘፍቆ ፤በመላው ኢትዮጵያውያን አንድነትና ትብብር አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍስሰው አባቶች እናቶች ያቆዩንን ታሪክ፤ የአማራ ገዥዎች የጻፉት ተረት ተረት ነው በሚል ስንኩል ቱሪናፋ ዲስኩር ፕሮፓጋንዳ፤ የሽግግር መንግስት፤ነፃነት ውይንም ባርነት፤ብሔር ብሔረስቦች፤ የብሔር ብሔረስቦች እስከመገንጠል በሚል፤በወንድሞቹ ደም የተጠመቀውን ጠብመንጃ በሕዝብና በአገር ላይ ወድሮ፤ ያላንዳች ሕዝባዊ ውክልና፤አገርን አስገንጥሎ፤ አገርን ያለባሕር በር ያስቀረ፤ ትውልደ ኢትዮጵያን የባእዳን ቅጥረኛ ምሁራንን በፋሽስቱ ቪኒቶ ሞሶሎኒ መርዝ የተለወስ ወያኔያዊ ሕገመንግስት እራሱ አስረቅቆ እራሱ በአምሳሉ በፈጠራቸው የጎሳ አቀንቃኝ ድርጅቶችና ሆድ አደር ስብስቦች በማስወስን፤ አገርን በአስራ አንድ ጎሳንና ቛንቛን መአከል ያደረገ 1928 በፋሽት የኢጣሊያ የአምስት አመቱ ወረራ ጊዜያዊ አገዛዝ ቻርታ የተነደፈውን የቅኝ አገዛዝ ሥነስርዓት አማካኝ ያደረገ፤ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በኋላ ከተቀበረበት ጕድጒድ አውጥቶ የአፍሪቃ የነጻነት ተምሳሌት የሆነችዋን ውድ ሃገራችንን በጎሳ በቋንቋ ተከፍላ በጥቂት ወያኔ ግርቢጦች፣ የውጭ ቅጥረኛ ጎስኞች መዳፍ ውስጥ ገብታ በሃያ አንደኛው ክፍለዘመን፤ አገር የጎሳ ባላባታዊ አንባ ገነን ሥነመንግሥታዊ አገዛዝ ሥር እንድትወድቅ የመከረ ያስመከረ የተገበረ፤ ሕዝብና አገርን የካደ፤ የሃገርና የሕዝብን ጥቀም አሳልፎ የሰጠ የሚሰጥ፤ አጥፊ፣ መስሪ ስብስብ፤ ትላንትም ሆነ ዛሬ ምግባሩ ሥራውም በጥፋት ላይ ጥፋትን ያነጣጠረ መሆኑ ለማንም አገር ወዳድ ግልጽ ነው። ወያኔአገርን ለባዕድ ሻጭ ጸረ ኢትዮጵያ ሀይል ነበረ--አሁንም ነው። ለዚህም ነው ከባዕድ ጋር የፍጥጫን ጎዳና መርጦ ሀገራችንን ለጥቃት ሊያጋልጥ እየተፍጨረጨረ ያለው። በመሆኑም ነው ሕዝብን ለጦረነት አገርን ለጥቃት አሳልፎ ከሚስጥ አገራዊ [ብሔራዊ] ወንጀለኛ፣ አገርና ሕዝብ ገዳይ አንባገነን ስነስርአት ጋር አገራዊ ትብብር ሊኖር የሚያስችል ምንም ጉዳይ የሌለው። በአባይ ስም ሕዝብን በጦርነት ለመማገድ፣  አገርን ለጥቃት አሳልፎ ለመስጠት፣ ከሚያሴሩ ጠርናፊ አስጠርናፊ የወያኔ ቅጥረኞች ተንኮል እራሳችንን አውጥተን፣ ሕዝብና አገርን በጋራ እንታደግ። ለነጻነት ትግል በጋራ በመቆም አምርረን እንነሳ።


ድል ለኢትዮጵያ !!!

No comments:

Post a Comment